ከኤርፖርቶች ድርጅት የተሰረቁ ሁለት የባለሥልጣናት ተሽከርካሪዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ተገኙ

(በኃያል ዓለማየሁ)

ከኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሐምሌ 23 ቀን 2002 ዓ.ም. ተሰርቀው የነበሩት ሁለት የባለሥልጣናት ተሽከርካሪዎች፣ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት መገኘታቸውን የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጋሻው አባተ ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡