በሐሰተኛ ማህተሞች አጭበርብሯል የተባለ ግለሰብ ተፈረደበት

(በታምሩ ጽጌ)

የመንግሥት ማህተሞችን ወደ ሐሰተኛነት በመለወጥና የሕዝብ አገልግሎት ወይም የግል ድርጅቶችን ማህተም ያለአግባብ በመስራትና በመለወጥ ተግባር ላይ በመሰማራት፣ በአገር ደኅንነትና ሰላም፣ በትምህርት ሥርዓቱና በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ከባድ ተፅዕኖ ሊያደርስ ነበር የተባለ ግለሰብ በዘጠኝ ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡