የበሰቃ ሐይቅ ውኃ ሙላት ከመቼውም በላይ ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል

(በታምራት ጌታቸውና በኃያል ዓለማየሁ)

ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መተሐራ ከተማ የበሰቃ ሐይቅ ውኃ ሙላት ከምንጊዜውም በላይ ሥጋት መፍጠሩን በአካባቢው የተገኙት ሪፖርተሮቻችን ለማየት ችለዋል፡፡