ካርታቸው የመከነ የሪል ስቴት አልሚዎች ቅሬታቸውን ለአስተዳደሩ እያቀረቡ ነው

(በውድነህ ዘነበ)

ቦታ ወስዳችሁ ግንባታ አላካሄዳችሁም በሚል ካርታቸው እንዲመክን የተደረገባቸው የሪል ስቴት አልሚዎች፣ ቅሬታቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢሮ ማቅረብ ጀመሩ፡፡