ጠበቆች ለተመሳሳይ ዓላማ ሁለት ስያሜ ይዘው እየተወዛገቡ ነው
‹‹የ40 ዓመት ዕድሜ እያለን ስማችንን ተነጥቀናል›› (የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር)
‹‹የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር የሚባል ከእኛ በፊት አልነበረም›› (የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር)
‹‹ሙያውና ስያሜው አንድ ዓይነት ያልሆነ ማኅበር ፈቃድ ሊሰጠው አይችልም›› (የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጀንሲ)
‹‹የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር የሚባል ከእኛ በፊት አልነበረም›› (የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር)
‹‹ሙያውና ስያሜው አንድ ዓይነት ያልሆነ ማኅበር ፈቃድ ሊሰጠው አይችልም›› (የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጀንሲ)
(በብርቱካን ፈንታ)
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበርና የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር ተመሳሳይ ባለሙያዎችን ይዘው እየተወዛገቡ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡ በአዳዲስ የጥብቅና ሥራ ባለሙያዎችም ዘንድ ግራ መጋባትን ፈጥሯል፡፡