አሠሪዎች ፌዴሬሽን በሆቴሎች ስም መንግሥትን ይቅርታ ጠየቀ
– ‹‹መንግሥት ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት የይቅርታ ጥያቄ አይቀበልም›› አቶ ታደለ ይመር
(በብርሃኑ ፈቃደ)
የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽን 10 ያህል ሆቴሎች ከቀረጥ ነፃ የገቡ ዕቃዎችን ያለ ፈቃድ በመሸጥ፣ ታክስ ባለመክፈልና ለሌላ ተግባር በማዋላቸው በወንጀል እንደሚጠየቁና ክስ እንደሚመሠረትባቸው ቢታወቅም፣ በሆቴሎቹ ስም ፌዴሬሽኑ ይቅርታ መጠየቁን አስታወቀ፡፡