‹‹እኔ ጥሩ ግብር ከፋይ ነኝ ያለመግባባቱ የመጣው ወጪ እንደገቢ በመያዙ ነው›› ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ
(በኃይሌ ሙሉ)
በአራዳ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ትዕዛዝ ማንኛውም ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረታቸው እንዲታገድ ለባንክ የተጻፈባቸው ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ፣ ከግብር ጋር በተያያዘ ንብረታቸው እንዲታገድ መደረጉ አግባብ አለመሆኑንና ጥሩ ግብር ከፋይ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡