ኑሮን እያከበደ ያለው የዋጋ ንረትና እየተወሰደ ያለው ዕርምጃ

በውድነህ ዘነበ

ወይንሸት ተክሌና ቢንያም አያሌው በየጊዜው እየጨመረ የመጣው የኑሮ ውድነት አስመርሯቸዋል፡፡ ወይንሸት የሦስት ልጆች እናት ስትሆን ከባለቤቷ ጋር በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኮልፌ አካባቢ ነዋሪ ነች፡፡