የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና አንድ እንግሊዛዊ የተወዛገቡበት ክፍያ በድርድር ተፈታ
በብርቱካን ፈንታ
ከሁለት ዓመታት በፊት ‹‹ሊከፈለኝ የተስማማሁት ክፍያ አልተፈጸመልኝም›› በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደብዳቤ ጽፎ የነበረው እንግሊዛዊው ሚስተር አንዲ ኢቡላሚና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ውዝግብ በድርድር መፈታቱን፣ የሚኒስቴሩ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡