በሙስና ወንጀል የተከሰሱ አራት ግለሰቦች በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

በጋዜጣው ሪፖርተር

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል ክስ ከመሰረተባቸው ስድስት ተከሳሾች ውስጥ በአራቱ ላይ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ከ6 ዓመት እስከ 8 ዓመት ከ6 ወር በሚደርስ ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡