የቤይሩት አውሮፕላን አደጋ ተጎጂ ቤተሰቦች ኢንሹራንስ አልተከፈላቸውም

የመታሰቢያ ሐውልት እየተሠራላቸው ነው

በቃለየሱስ በቀለና በብርቱካን ፈንታ

ባለፈው ዓመት በጥር ወር በቤይሩት አቅራቢያ ድንገተኛ አደጋ በደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ሕይወታቸውን ላጡ ተሳፋሪዎችና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ቤተሰቦች እስካሁን ድረስ ኢንሹራንስ እንዳልተከፈላቸው ታወቀ፡፡