አቶ ጌቱ ገለቴ ከተከሰሱበት የወንጀል ክስ ነፃ ያደረጓቸው ዳኛ ተባረሩ

– የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ተሾመለት

በታምሩ ጽጌና በኃይሌ ሙሉ

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አቶ ጌቱ ገለቴን ከተከሰሱበት የወንጀል ክስ በነፃ ያሰናበቷቸው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ዳኛ አቶ ዘሪሁን ቦዴ፣ ከፍተኛ የሥነ ምግባር ግድፈት መፈጸማቸውን በማረጋገጥ ከሥራ እንዲባረሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የውሳኔ ሐሳብን ምክር ቤቱ በትናንትናው ዕለት አፀደቀው፡፡