አዋሽ ባንክ አቶ ለይኩን ብርሃኑን ከኃላፊነት አሰናበተ

በየማነ ናግሽ
ላለፈው አንድ ወር በግዳጅ ዕረፍት ላይ እንዲቆዩ ተወስኖባቸው የሰነበቱት የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ለይኩን ብርሃኑ፣ ከኃላፊነታቸው እንዲሰናበቱ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ወሰነ፡፡ የ10 ሺሕ ብር መቀጮ እንዲከፍሉም ተወስኖባቸዋል፡፡