ላም ካንገቱ በላይ ሰው የሚመስል ፍጡር ወለደች

በደቡብ ክልል ከሻኪሶ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዲባቦቴ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ አንዲት ላም ከአንገቱ በላይ ሰው የሚመስል ፍጡር ሰኔ 26 ለ27 አጥቢያ 2003 ዓ.ም. ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት አካባቢ መውለዷን የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡