ስዬ አብርሃ ወደ ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ያቀናሉ
‹‹ሕወሓት ወደ እስር ቤት ሸኘኝ፤ አንድነት ግን ወደ ትምህርት ቤት እየላከኝ ነው›› አቶ ስዬ አብርሃ
የሕወሓት የቀድሞ የአመራር አባል፣ የመከላከያ ሚኒስትርና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ስዬ አብርሃ፣ በዓለም ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጣቸው፡፡