የዋጋ ተመን በጥናት ወይስ በፖለቲካ ውሳኔ?

መንግሥት በገና በዓል ዋዜማ በተመረጡ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ተመን ገደብ ማውጣቱ አይዘነጋም፡፡ ከአምስት ወራት በኋላም ከሦስት ሸቀጦች በስተቀር ማለትም ስኳር፣ ዘይትና ዱቄት በስተቀር፣ ያስቀመጠውን የዋጋ ተመን አንስቷል፡፡