ለቅዱስ ሲኖዶስ ቅሬታ ሊያቀርቡ የመጡ ከ200 በላይ ሰዎች ዱከም ላይ በፖሊስ ታገቱ

ከደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከሐዋሳ ከተማ በሰባት አውቶቡስ ተሰባስበው ቅሬታቸውን ለማሰማት ወደ አዲስ አበባ ያመሩት የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አገልጋዮችና የእምነቱ ተከታዮች ምዕመናን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በምትገኘው ዱከም ከተማ ላይ ሲደርሱ በፖሊስ መታገታቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡