ሰኔ ሰላሳና ‹‹የነጋዴ አበሳ›› ይገጣጠሙ ይሆን?
– ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካፒታልና በሥራ አድራሻ ምክንያት መመዝገብ ላልቻሉ ጊዜ አራዝመዋል
ንግድ ሚኒስቴር ሐምሌ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. በተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀውን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ከየካቲት 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን በመግለጽ አተገባበሩን አስመልክቶ በትናንትናው ዕለት ለኢትዮጵያ ነጋዴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ በሒልተን ሆቴል ሰጥቷል፡፡