ብሔራዊ ባንክ የወርቅ ግብይቱን በክልሎች ብቻ እንዲያደርግ መመርያ ወጣ

– መመርያውን ወርቅ አቅራቢዎች እየተቃወሙት ነው

ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ በማቅረብና በመሸጥ ላይ ያሉ ወርቅ አቅራቢዎች ከዚህ በኋላ በተመረጡ የክልል ከተሞች ብቻ በሚዘጋጅ የወርቅ መቀበያ ማዕከል ብቻ እንዲያቀርቡ የሚያስገድድ መመርያ ወጣ፡፡