ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞተር ሳይክል ሰዎችን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ህይወታቸውን የሚመሩ 500 ያክል ወጣቶች ስራ እንዲያቆሙ በመታዘዛቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል። ሰራተኞቹ በድንገት አቁሙ በመባላቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር ተቸግረዋል። መንግስት አማራጭ ስራ ሳይፈጥር በድንገት ስራ አቁሙ ማለቱ ተገቢ አይደለም በሚል ወጣቶቹ ያስነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው ባለስልጣናት ተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሰጥተዋል። አንድ …

ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተከዜ ወንዝ ጫፍ ላይ የምትኘውና የዋግና የበለሳ ነዋሪዎች መተላለፊያ የሆነችው አርባ ፀጓር ወረዳ ደርግን ለመጣል በተደረገው የትግል ወቅት የኢህአፓና የኢሕዲን መተላለፊያ መስመር የነበረች ሲሆን በወቅቱ የድሮው ኢሕዲን የአሁኑ ብአዴን ታጋዮች የነበሩት ለሕዝቡ የኑሮ ለውጥና ዴሞክራሲያ ስርዓት እንደሚገነቡ ቃል በመግባታቸው ነዋሪው ሸማቂዎቹን በማገዝ ከለላ ይሰጣቸው የነበረ ሲሆን ድል …

ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ፥ ESFNA በካናዳ የቶሮንቶን ከተማ የ2016 የስፖርት ክብረ በዓል ዓስተናጋጅ እንድትሆን መርጧል። ውሳኔው የተላለፈው፥ በኢትዮ-ስታር ቶሮንቶ የእግር ኳስ ክለብ ዓስተባባሪነት በቶሮንቶ ካናዳ በተዘጋጀው፥ የESFNA ዓመታዊ ጉባኤ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ የክለብ ተዎካዮችና የቦርዱ ዓመራር ዓባላት በተገናኙበት፥ ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ October 10 እና …

ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙት የቱርካና ሃይቅና የኦሞ ወንዝ ኢትዮጵያ በምትከተለው የኢንዱስትሪ ዘመቻ ምክንያት የመድረቅ እና የአየር ንብረት መዛባት አደጋን ማስከተሉንና በዚህም ለውጥ ሳቢያ የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ሂውማንራይትስ ወች በጥናት ሪፖርቱ አመልቷል። በሰሜናዊ ምዕራብ ኬንያ በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሚገኘው የቱርካና ሃይቅ በዓለማችን በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ከሚገኙት …

– ወያኔ መስጊዶችን መዋጮ ሊጠይቅ ነው – የወያኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተብየው በፖለቲካ መሪዎች ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ – የሱማሊያ የጦር ጉዳተኞች ኬኒያ መሆናቸው ተገለጸ – የግብፅ የወያኔና የሱዳን የአባይ ግድብ ድርድር ሊቀጥል ነው – በማላዊ እስር ቤት ታግተው የሚገኙ …

ወያኔ መስጊዶችን መዋጮ ሊጠይቅ ነው:: – በማላዊ እስር ቤት ታግተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፈተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው Read more »

አንድ ዜጋ በገዛ አገሩ አንገቱን ቀና አድርጎ በነፃነት መራመድ የሚችለው መብቱ ሲከበርለትና እሱም የሚፈለግበትን ግዴታውን ሲወጣ ነው፡፡ ይህ ግዴታውን የሚወጣ ዜጋ ፍትሕ ሲነፈግና መብቱ ሲጣስ ግን ዜግነቱን ይጠራጠራል፡፡ ስለልማት፣ ስለዕድገትና ብልፅግና ቢወራ አይሰማም፡፡ በጉልበተኞች ንብረታቸውን የተቀሙ ዜጎች ፍትሕ ሲጠይቁ ተነፍገው …

የፍትህ አካላቱ ጥጋብ ጣራ እየነካ የሕዝብን ብሶት ሊያፈነዳው ተቃርቧል:: Read more »

ዛሬ ጧት አንድ የብአዴን ባለስልጣን ፍፁም የበታችነት ስሜቱን በሚሳብቅ መልኩ “ብአዴን ከአንድ ጀግና ህዝብ የራሱን ዐላማ አንግቦ የተነሳ፣ ብዙ ጀብዶች የፈፀመ፣ ብዙ መስዋዕትነት የከፈለ፣ በራሱ ዐላማ የቆመ ፓርቲ እንጅ የማንም ተለጣፊ ሆኖ አያውቅም” ሲል ኢቢሲ ሰማሁ፡፡ እሰየው! እንዳፉ ያድርግለት! እውነት …

እስቲ ሐቁን እንመስክር፡ ብአዴን/ኢህዴን ማን ነው? Read more »

ይድረስ ለኩሩዋ የሃገሬ ሴት በሙሉ በሙሉ መስዋእትነት ከፍለን ይህን ሃገር አጥፊ ቡድን እናስወግድ። አንቺ የኢትዮጵያ ዉብ ሴትሆይ፤ አንቺ በሃገርሽ ሾል አጥተሽ በየአረብ ሃገሩ የምትንከራተቺው የኢትዮጵያ ኩሩ ሴት፤ አንቺ በሃገርሽ ለሃገርሽ ሰርቶ ለመኖር ተምረሽ ሾል አጥተሽ የምትንከራተችው ኢትዮጵያዊት፤ አንቺ በስርአቱ አስተዳደር …

ይድረስ ለኩሩዋ የሃገሬ ሴት በሙሉ መስዋእትነት ከፍለን ይህን ሃገር አጥፊ ቡድን እናስወግድ። Read more »

ኢሕአዴግ ያቋቋመው ፍፁማዊ አምባገነን መንግስት ለኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግሮች መፍትሔ ሊሰጥ አይችልም!! ============== ከኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ የኢፌድሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 54/1፣የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሁሉ አቀፍ፣ ነፃ፣ ቀጥተኛና ትክክለኛ በሆነ፣ ድምፅ በምስጢር በሚሰጥበት የምርጫ ስርዓት በየአምስት …

ኢሕአዴግ ያቋቋመው ፍፁማዊ አምባገነን መንግስት ለኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግሮች መፍትሔ ሊሰጥ አይችልም!! Read more »

#Ethiopia : በምርጫ እና በብልጫ የምታደምጡት የናንተው የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ለዚህ ሳምንት የመራረጥናቸውን ዜናዎች እና መጣጥፎችን ቀልብን ከሚስቡ ሙዚቃዎች ጋር አዋዝተን ቀርበናል። መልካም ጊዜ… [youtube http://www.youtube.com/watch?v=2OrTNwGiwSg]

በኢትዮጵያ የአስችኳይ ረድኤት ፈላጊዎች ቁጥር 8.2 ሚልዮን የደረሰ ሲሆን ወደ $596. 4 ሚልዮን ዶላር የሚሆን እርዳታ እንደሚያስፈልግ ታወቀ።

-ህወሃት መልሚ ኢህአዴግ ዳግም የመጅሊስ ግልበጣ ለማድረግ በተባረሩ ሰራተኞች ተጻፈ የተባለ የመጅሊሶችን ገበና የሚያጋልጥ አስደንጋጭ ደብዳቤ እንዲሰራጭ አደረገ ልዩ ዘገባ ይዘናል http://goo.gl/R36eUa -በሜዳወላቦ ዩንቨርስቲ በኒቃብና በሶላት ሁለት ተማሪዎች ተባበረሩ በኒቃብ ምክኒያት የተባረረችው ተማሪ ከቢቢኤን ጋር ቆይታ አድርጋለች ሁሉም ሊነቃ በቃ …

ህወሃት መልሚ ኢህአዴግ ዳግም የመጅሊስ ግልበጣ ለማድረግ አስደንጋጭ ደብዳቤ እንዲሰራጭ አደረገ:: Read more »

ሙሉጌታ ሉሌ / Mulugeta Luleበልጅግ ዓሊ

“ደግ ደጉን ስናጣ፣ ኀዘኑ መረረ

ሞት አምላኩ ከድቶት፣ ገሎት በነበረ።”

– የሠፈራችን ሙሾ አውራጅ

እነሆ ጋሼ ሙሉጌታ ዐረፈ። ከዚህ ምስቅልቅሉና ቅጥ አምባሩ ከወጣ ዓለም በአካል ተለየ። ጋሼ ሙሉጌታ ከእንግዲህ የሀገሩን አፈር በሞቱ እንኳ ላይቀምስ ነው። ዛሬ የሰው ሀገር አፈር ለብሶ በዝምታ ማሸለቡን መርጧል። ሀገሩን እንደናፈቀ የተለያት ቢሆንም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር ትምህርት ሰጥቶን አልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚገኙ 8 ሚሊዮን 200 ሺ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚሹ፣ በከተማ ውስጥ የሚኖሩ 4 ሚሊዮን ተረጅዎች እንዳሉ በመንግስት እና በአለማቀፍ ድርጅቶች ይፋ ከሆነ በሁዋላ፣ የአለማቀፍ ድርጅቶች መንግስት ለልማት በሚል የመደበውን ገንዘብ የዜጎቹን ነፍስ ለመታገድ እንዲያውለው ጠይቀዋል። እስከሚቀጥለው ታህሳስ ወር ድረስ ምግብ ገዝቶ ለማቅረብ የሚያስፈልገው 12 …

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው እሁድ ጀምሮ በኢትዮጵያውያንና በሱዳን መንግስት ወታደሮች መካከል የተነሳው ጦርነት መቀጠሉን ከአካባቢው የደረሱን መረጃዎች ያመለካታሉ።ኢትዮጵያውያን ታጣቂዎች፣ ከዚህ ቀደም ማንነታቸው ያልታወቁ የሱዳን ታጣቂዎች 8 ኢትዮጵያውያንን ለሹፌርነት እንቀጥራችሁዋለን በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ከመኪና ላይ አውርደው መግደላቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያኑ በወሰዱት አጸፋ እርምጃ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የሱዳን ወታደሮችን ገድለዋል። የሱዳን መንግስት ተጨማሪ …

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ ፣ ወታራና ጉጉማ በሚባሉ አካባቢዎች ከ2004 ዓም ጀምሮ በእየአመቱ የሚቀሰቀሰው ግጭት ሰሞኑን አገርሽቶ፣ እስካሁን 2 ሰዎች በከባድ ሁኔታ ተጎድተው አዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሲገቡ፣ መጠኑ ያልታወቀ ንብረትም ወድሟል። በቦንኬ ጎሳና በጉኑፋ ጎሳዎች መካከል የተነሳው ግጭት መንስኤ የአንዱ አካባቢ ተወላጅ ሌላውን ማስተዳደር አይችልም …

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በማላ ዊ የድንበር ጠባቂዎች የተያዙ ከ317 በላይ ኢትጵያዊያን ስደተኞች በተለያዩ እስርቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው መሆኑን አጃን ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። የማላዊ ፍርድ ቤት በስደተኞች ላይ የእስር ቅጣትና ስድሳ አምስት የአሜሪካን ዶላር መቀጮ የጣለባቸው ሲሆን ፣ አብዛሃኞቹ ከስድስት ወራት …

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብር ወንጀል ተከሰው በ19ኛው ወንጀል ችሎት ነጻ የተባሉት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሃብታሙ አያሌው፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ም/ል ሰብሳቢ የነበረው የሽዋስ አሰፋ፣ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ም/ል ስብሳቢና የደቡብ ተወካይ የነበረው ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም አብርሃም ሰለሞን ፣ ዛሬ ጠ/ፍርድ ቤት ቀርበው፣ በአቃቢ ህግ የተጠየቀባቸው ይግባኝ …

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በፍቼ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት መስሪያ ቤትስራችንን በአግባቡ ሊያሰራን አልቻለም በሚል ምክንያት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከትናንት ጀምረው የስራማቆም አድማ አድርገዋል። የከተማው መንገድ ትራንስፖርት ባጃጅ ለመንዳት የታክሲ አንድ ፈቃድ መያዝ ያስፈልጋል የሚል መመሪያ ያወጣ ሲሆን፣ በሶስተኛ መንጃ ፈቃድ ሲያሽከረክር የተገኘ ሹፌር 2 ሺ 500 ብር ይቀጣል። የቅጣቱን መጠንና …

በቲፒ የታገቱ ፖሊሶችን ለማስለቀቅ የኃይል እርምጃ ይወሰዳል ተባለ :: ========= ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ የወያኔ የብድር መጠን አሳሳቢ ነው አሉ :: ======== በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዝበራው ጦፏል :: ============= and more Others information [youtube http://www.youtube.com/watch?v=___4F1lmtAY]

Minilik Salsawi – በጥልቀት አትኩሮት እንዳይሰጠው እየተሸፋፈን እየተድበሰበሰ ያለው በሃገራችን ውስጥ የተከሰተው ድርቅ ስምንት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚወጡ ሪፖርቶች እየጠቆሙ ነው:: የወያኔው አገዛዝ በሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የረሃብ አድጋ ተድበስብሶ ተደብቆ እንዲቀር …

ስምንት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ በሞት አፋፍ ላይ ይገኛል::(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ባለፈው ቅዳሜ በተነሳው ግጭት ከፖሊስና ከመከላከያ አንዳንድ ወታደሮች ቆስለዋል። የግጭቱ መንስኤ ሁለት የመከላከያ ፖሊስ አባላት በፖሊሶች መደብደባቸው ነው። ከዚህ ቀደም አንድ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ፍቼ አካባቢ ሰፍሮ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት አባል ከገደለው በሁዋላ፣ በመከላከያና በፖሊስ መካከል ለወራት የዘለቀ ቁርሾ እንዲፈጠር አድርጓል። ባለፈው ቅዳሜ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማው እየተዝናኑ በነበረበት ወቅት፣ ፖሊሶቹ የደበደቡዋቸው ሲሆን፣ የመከላከያ […]

አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ፈላጊዎች 8.2 ሚሊዮን መድረሳቸውን መንግሥት ይፋ አደረገ

–   ጠቅላላ የሚያስፈልገው የዕርዳታ መጠን 12 ቢሊዮን ብር ደርሷል

–    አራት ቢሊዮን ብር ከመንግሥት ካዝና ወጪ መደረጉ ተጠቁሟል

በድርቅ ምክንያት አስቸኳይ የዕለት ደራሽ የምግብ ዕርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር 8.2 ሚሊዮን መድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ፡፡ ለጋሾች አስፈላጊውን ዕርዳታ እያቀረቡ

አለመሆኑን መንግሥት ሲያስታውቅ፣ በጠቅላላው አስከፊነቱ እየተባባሰ ለመጣው ድርቅ 12 ቢሊዮን ብር ወይም 600 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደሚያስፈልግ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ይፋ አድርገዋል፡፡ 

ጥቅምት 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ከለጋሽ አገሮች፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲዎችና መንግሥታዊ ካልሆኑ ለጋሾች ጋር በተደረገ የሁለትዮሽ ስብሰባ ላይ የብሔራዊ አደጋ መካከልና ዝግጁነት ኮሚቴ ጸሐፊ አቶ ምትኩ ካሳ እንዳስታወቁት፣ በኤልኒኖ ክስተት ምክንያት በበልግና በመኸር (ክረምት) የዝናብ ሥርጭት በመዛባቱ 8.2 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ 

‹‹የበልግ ዝናብ መዛባት ከመኸር ዝናብ መስተጓጎል ጋር ተዳምረው የፈጠሩት ችግር ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ግን በልግ በሚዛባበት ወቅት መኸር ጥሩ ይሆን ነበር፡፡ ለወትሮው በመኸር አምራች የሆኑ አካባቢዎች ለችግር ስለማይጋለጡ የተረጂዎች ቁጥር ዝቅ ያለ ነበር፡፡ አሁን ግን የሁለቱም መዛባት ችግሩን ፈጥሯል፡፡ ከዚህ ባሻገር ከጥር እስከ ሰኔ ወር በሚተገበረው ሴፍቲኔት ፕሮግራም ታቅፈው የነበሩ 4.4 ሚሊዮን ሰዎችም በ8.2 ሚሊዮን አኃዝ ውስጥ ይገኛሉ፤›› ያሉት አቶ ምትኩ፣ ከጥር ወር በኋላ በመደበኛው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑት ሰዎች ከዕለት ደራሽ ተረጂዎች ሲለዩ፣ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ የሚቀርብላቸው ሰዎች ቁጥር እንደሚቀንስ አስረድተዋል፡፡ 

ባለፈው የበልግ ግምገማ ተካሂዶ ነሐሴ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው አኃዝ መሠረት የተረጂዎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን እንደነበር መገለጹን ያስታወሱት አቶ ምትኩ፣ ይህ አኃዝ ይፋ ከተደረገ በኋላ መንግሥት በአብዛኛው ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱን፣ በተወሰነ ደረጃ የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካል ያልሆኑ ድርጅቶች ማለትም በካቶሊክ ሪሊፍ ሶሳይቲ ሥር የሚንቀሳቀሱ ተቋማት ለድርቅ ጉዳተኞች ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡ የበልጉ ዝናብ በመዛባቱ የተከሰተው የምግብ እጥረት 4.5 ሚሊዮኖችን ጉዳት ላይ ጥሏል ቢባልም፣ የክረምቱ ዝናብም በኢልኒኖ ሳቢያ ዘግይቶ ከመግባት ባሻገር በመጠንና በሥርጭት ስለተዛባ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ከ4.5 ሚሊዮን ወደ 7.4 ሚሊዮን፣ ቀጥሎም ወደ 7.7 ሚሊዮን ሊደርስ ችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 8.2 ሚሊዮን መድረሱ ታይቷል ያሉት አቶ ምትኩ፣ ይህ ቁጥር ከዚህ ቀደም በሴፍቲኔት ፕሮግራም የታቀፉት 4.4 ሚሊዮን ሰዎች ያካተተ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡ 

አቶ ምትኩ በሪፖርተር ተጠይቀው እንዳብራሩት፣ መንግሥት ከራሱ መጠባበቂያ ፈንድና ከክልሎች በተዋጣ በጀት አራት ቢሊዮን ብር ወይም 192 ሚሊዮን ዶላር ለዕርዳታ ማዋሉንና እንደሚቀጥልበትም ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ለአስቸኳይ ዕርዳታ እየዋለ ካለው ገንዘብ ውስጥ አብዛኛውን ከፌደራል መጠባባቂያ ፈንድ ቢያወጣም፣ ክልሎችም በራሳቸው ከያዟቸው የመጠባበቂያ ፈንድ በጀት ለድርቁ ሰለባዎች ማዋላቸው ተነግሯል፡፡ 

የኦሮሚያ ክልል 565 ሚሊዮን ብር በክልሉ ለተጎዱ ሰዎች ሲያውል፣ የአፋር ክልል በበኩሉ 100 ሚሊዮን ብር በመመደብ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርም ተመሳሳይ ዕርምጃ በመውሰድ ተጎጂዎችን እየታደገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በከፍተኛ መጠን የድርቅ ተጎጂዎች ካሉባቸው ክልሎች መካከል አፋር ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡ ሶማሌ ክልልም በተጎጂነት ከፍተኛውን ድርሻ ከሚይዙት ክልሎች ውስጥ ሲካተት የደቡብ፣ የአማራና የትግራይ ክልሎችም በድርቅ ምክንያት ተጎጂዎች የሚገኙባቸው ሆነዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እስካሁን ለተረጂዎች የተገዛውን 450 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ጨምሮ አንድ ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ እንደሚገዛ ይፋ አድርገዋል፡፡ በጠቅላላው ከ620 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ ስንዴ ለመግዛት ዓለም አቀፍ ጨረታ መውጣቱን አቶ ምትኩ አስታውቀዋል፡፡ 

ይህም ቢባል ግን ከዚህ ቀደም በተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ጥሪ ያቀረበበት አስቸኳይ የዕርዳታ መጠን 450 ሚሊዮን ዶላር (ከ9.4 ቢሊዮን ብር በላይ) ሊያስፈልግ እንደሚችል የሚጠቁም እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል፡፡ እስካሁን ግን ይህ ነው የሚባል ድጋፍ አለመገኘቱን መንግሥት አስታውቋል፡፡ አቶ ምትኩ በጽሕፈት ቤታቸው ካነጋገሯቸው የውጭ ዕርዳታ ለጋሾች መካከል የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት መሥሪያ ቤት (ዴፊድ) 45 ሚሊዮን ፓውንድ (ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ)፣ የስዊዝ ትብብር ተቋም ሰባት ሚሊዮን የስዊዝ ፍራንክ (152.74 ሚሊዮን ብር) ለመለገስ ቃል ከመግባታቸው ውጪ፣ ሌሎቹ ተቋማት ዕርዳታ ለመስጠት ፍላጎት እንዳላቸው ከመግለጽ በቀር ቃል የገቡት የገንዘብ መጠን አልነበረም፡፡ 

መንግሥት ድርቅ ያስከተለው ከባድ አደጋ ከቁጥጥሩ ውጪ እንዳልሆነ ለለጋሽ አገሮች፣ ለተመድ ኤጀንሲዎች ተወካዮችና ለዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች ያብራሩት አቶ ምትኩ፣ በአንፃሩ ከእነዚህ አካላት የተጠበቀውን ያህል ምላሽ አለመገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡ የሰብዓዊ ዕርዳታ ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ማግኘት አስቸጋሪ ከሆነባቸው ምክንያቶች መካከል፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተከሰቱ ቀውሶች የኢትዮጵያን የድርቅና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ቸል እንዲባል ሰበብ መሆናቸውን ሲገልጹ ተደምጠዋል፡፡ 

በዓለም የምግብ ፕሮግራም የቀጣናው አስተባባሪና በብሔራዊ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ጆን አይሊፍ የተመራው የለጋሾች ቡድን፣ በኢትዮጵያ የተከሰተው አስከፊ የድርቅ አደጋ አስቸኳይ ምላሽ እንደሚያስፈልገው ከስምምነት በመድረስ፣ በጥቅምት ወር ማብቂያና በኅዳር ወር መጀመሪያ አካባቢ ተጠቃሎ ይፋ እንደሚወጣ የሚጠበቀውን ሪፖርት በመንተራስ፣ የጉዳተኞች መጠንና የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ምን ያህል እንደሚሆን በግልጽ እንደሚታወቅ ገልጸዋል፡፡

ይህም ሆኖ በጠቅላላው ለኢትዮጵያ የድርቅ ሰላባዎች ያስፈልጋል ከተባለው 12 ቢሊዮን ብር ውስጥ እስካሁን 258 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ5.1 ቢሊዮን ብር በላይ ከለጋሾች ቢገኝም ጥቅም ላይ በመዋሉ የምግብ፣ የተጨማሪ ምግብ አቅርቦት፣ የግብርና ዘርፍ ላይ ለህልውና የሚያስፈልጉ ምግብ ነክ አቅርቦቶች ከፍተኛ እጥረት መከሰቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት ፈንድ (ዩኒሴፍ) ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ መሠረት በመጪዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ ለሰብዓዊ ድጋፎች በአስቸኳይ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን 237 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ4.7 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ዩኒሴፍ ይፋ አድርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር ለልማት ከተያዘው በጀት መንግሥት ወደ አስቸኳይ ዕርዳታ መዋል እንዳለበት ዩኒሴፍ አሳስቧል፡፡ የዴንማርክ ኤምባሲም የዩኒሴፍ ጥያቄን አስተጋብቷል፡፡ በዓለም ላይ በተከሰቱት ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ሳቢያ የዕርዳታ ሽሚያ በማጋጠሙ፣ መንግሥት ለልማት ሥራዎች ከሚያውለው ፈንድ ውስጥ ለድርቁ ተጎጂዎች የሚውል ገንዘብ እንዲመድብ ጠይቋል፡፡

  ሴቭ ዘ ችልድረን ኢትዮጵያ ለለጋሾች ቡድን እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የከረረ  መሆኑን፣ መንግሥት ምላሽ የሰጠበት መንገድ ከወትሮው የተለየና ያልተለመደ ፍጥነት የታየበት እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ሆኖም አስቸኳይ ዕርዳታ ካልተገኘ ግን አስከፊ የምግብ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ሥጋቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የካናዳ ኤምባሲና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) መንግሥት መረጃ በመስጠትና ድርቅ በከሰተባቸው አካባቢዎች ፈጣን ግምገማ በማካሄድ ያገኛቸውን ውጤቶች በማሠራጨት በኩል ጥሩ ሥራ መሥራቱን ገልጸዋል፡፡ አቶ ምትኩ በበኩላቸው ዘንድሮ በተከሰው ድርቅ መንግሥት ትልቁን ድርሻ በመያዝ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ከማቅረብ በተጨማሪ፣ ዕለታዊ መረጃዎችን ለለጋሾች በመስጠት ግልጽነት የተሞላበት ግንኙነት መመሥረቱን አስታውቀዋል፡፡ 

 

 

 

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ለተሿሚዎች መኖሪያ ቤት ማቅረብ ተቸግሯል

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በተለይ ሰሞኑን ለተሾሙ ሚኒስትሮችና የተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ፣ ከምክትል ዋና ዳይሬክተር በላይ ሹመት በሚሰጣቸው የመንግሥት ተሿሚዎች የሚሰጠው በቂ ቤት እንደሌለው አስታወቀ፡፡

በሌላ በኩል ላለፉት 24 ዓመታት አዳዲስ መኖርያ ቤቶችን እንዳይገነባ የተደረገው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ፣ ለተሿሚዎች የሚያቀርበው መኖርያ ቤት በማጣቱ ነባር ነዋሪዎችን ለማስለቀቅ መዘጋጀቱን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያ ገለጹ፡፡ 

ከ600 በላይ የመንግሥት ተሿሚዎች የመኖርያ ቤት ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየተጠባበቁ ቢሆንም፣ ኤጀንሲው ለተሿሚዎች የሚያቀርበው መኖርያ ቤት በማጣቱ ሦስት አማራጭን ለከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አቅርቧል፡፡ 

የመጀመርያው አማራጭ ለዘመናት በኪራይ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ግለሰቦችን ማፈናቀል ነው፡፡ ሁለተኛው አማራጭ በቤት ልማት ፕሮግራሞች እየተገነቡ ያሉ ኮንዶሚኒየሞችና ከግለሰቦች ደግሞ ሪል ስቴት ቤቶችን መግዛት ነው፡፡ ሦስተኛው አማራጭ በራሱ አቅምና በጀት መኖርያ ቤቶችን መገንባት የሚሉት መሆናቸው ታውቋል፡፡ 

ነገር ግን የተሿሚዎቹ የመኖርያ ቤት ፍላጎት አጣዳፊ በመሆኑና የመኖርያ ቤት ግዢም ሆነ ግንባታ አማራጮች ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት የማያስችሉ በመሆናቸው፣ ኤጀንሲው ትኩረቱን ተከራዮችን ማፈናቀል ላይ ማድረጉ እየተነገረ መሆኑን ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል በተደረገ ስብሰባ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ኤጀንሲው ‹‹የተሻሻለው የቤቶች አስተዳደር በግል ርዕስ ባወጣው መመርያ ቁጥር 41/2007 አንቀጽ 3 ለመንግሥት ተሿሚዎች (ብቻ) ቤቶች እንደሚሰጥ አስቀምጧል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ለፌዴራል መንግሥት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ከኃላፊነት ለሚነሱ ባለሥልጣናት መኖርያ ቤት ይሰጣል ይላል፡፡ በመመርያው ለነዋሪዎች መኖርያ ቤት እንደሚሰጥ የሚገለጽ አንቀጽ አልተቀመጠም፡፡

በዚህ መሠረት ከመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በግለሰብ ደረጃ ቤት መከራየት የሚታሰብ አለመሆኑን በርካታ ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገርም የኤጀንሲው ነባር ተከራዮች የመፈናቀል አደጋ እያንጃበበብን ነው በማለት ሥጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ይህ አደጋ ሊያንዣብብ የቻለው ለመንግሥት ባለሥልጣናት አዲስ ሹመት ከመሰጠቱ በተጨማሪ፣ ለአምስት ዓመታት ያገለገሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሥራ ጊዜያቸውን ጨርሰው በአዲስ መተካታቸው ነው፡፡ ይህ ሁኔታ አሳሳቢ ሊሆን የቻለው በርካታ አዳዲስ ተሿሚዎች የመኖርያ ቤት ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን፣ ከነባሮቹ የፓርላማ ነዋሪዎች መኖርያ ቤቶች ውስጥ 155 የሚሆኑት አገልግሎት ለመስጠት የማይችሉ በመሆናቸው ልዋጭ ያስፈልጋል በመባሉ ነው፡፡ 

ይህ ጉዳይ ገኖ ባይወጣም የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በ2008 የሥራ ዕቅድ ላይ ከተከራይ ደንበኞቹና ከባለድርሻ አካላት ጋር ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ባደረገው ውይይት በተወሰነ ደረጃ ተነስቷል፡፡ 

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኃይለ ማርያም ዓለም ሰገድ፣ ‹‹የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ከዚህ በኋላ ቤት የሚያቀርበው ለመንግሥት ተሿሚዎች ብቻ ነው፤›› ካሉ በኋላ፣ ኤጀንሲው 17 ሺሕ ቤቶችን እንደሚያስተዳድር ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ የሲኤምሲ አፓርታማዎችን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚኖሩባቸው 141 አፓርትመንቶች ሲኖሩት፣ እነዚህ አፓርትመንቶች 5,294 ቤቶች አሏቸው፡፡ ኤጀንሲው እነዚህን አፓርትመንቶች ለማስተዳደር አዲስ መመርያ ማዘጋጀቱን አቶ ኃይለ ማርያም አስታውቀዋል፡፡ 

የአፓርትመንት አስተዳደር፣ አጠቃቀምና አጠባበቅ ረቂቅ መመርያ ላይ፣ በኤጀንሲው ደንበኞች በተቋቋሙ የአፓርታማ ነዋሪዎች ማኅበራት ተወክለው ከተገኙና ከተለያዩ አካላት ከተወከሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ 

ተከራዮች የተከራዩትን ቤት እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ማለትም የንፅህና አጠባበቅ፣ በየሕንፃዎቹ ላይ የተከራዩ ደንበኞች አንዱ የሌላውን መብት ሳይነካ የሕንፃውን ደኅንነት ጠብቀው መኖር እንዳለባቸውና ችግር የሚፈጥር ካለ ቤቱን እስከማስለቀቅ የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልበት በዝርዝር በረቂቅ መመርያው ተካተዋል፡፡ 

ኤጀንሲው፣ ‹‹የደንበኞቼን ደኅንነት ለመጠበቅ የቤቴን ደኅንነት መጠበቅ ግዴታ አለብኝ›› በማለት የሕንፃዎቹን ውበትና ንፅህና ለመጠበቅ ያዘጋጀውን ረቂቅ መመርያ ለተወያዩ ካስተዋወቀ በኋላ፣ መድረኩን ለተሳታፊዎች ክፍት አድርጓል፡፡ 

የውይይቱ ተሳታፊዎች የመመርያው መዘጋጀት ጥሩ መሆኑን በጥቅሉ ከተናገሩ በኋላ ትኩረት የሰጡት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ ‹‹የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ከዚህ በኋላ የሚሠራው ለመንግሥት ተሿሚ ኃላፊዎች ብቻ ነው፤›› ለሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ‹‹ቤት የምንሰጠው ለመንግሥት ባለሥልጣናት ብቻ ነው መባሉ ያሠጋናል፡፡ እናንተ ከቤታችን ልትወጡ ነው የሚል አባባል ይመስላል፤›› ያሉት ተሳታፊዎቹ ምን ማለት እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀው፣ ኤጀንሲው ልብ ሊል የሚገባው የቤት ተከራዮች ታክስ እየከፈሉ አገልግሎት ማግኘት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ 

ኤጀንሲው ተከራዮችን ሊያዳምጥና ያለባቸው ችግርም ሊመለከት እንደሚገባ ተናግረው፣ ፅዳትንና ዕድሳትን በሚመለከት በረቂቅ መመርያው ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መቀመጡ ተገቢ በመሆኑ፣ ከኤጀንሲው ጋር ተባብረው ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ 

አንዳንዶቹ ሕንፃዎች ለተለያዩ አገልግሎቶች እየዋሉ በመሆናቸው፣ ኤጀንሲው በጥቃቅን ሥራዎች ላይ ማተኮሩን ተወት አድርጎ የትኛው ሕንፃ ለንግድ፣ የትኛው ለመኖሪያና ለቢሮ መዋል እንዳለበት በመለያየት ሥርዓት እንዲያሲዝላቸው ጠይቀዋል፡፡ ኤጀንሲው ከደንበኞቹ በሚቀርቡለት ጥያቄዎች ላይ ተገቢና አፋጣኝ ምላሽ እንደማይሰጥ የተናገሩት የውይይቱ ተካፋዮች፣ በምርኩዝ የሚሄዱ ጥበቃዎችን ቀጥሮ ሁሉም ነገር የተሟላለት ሕንፃ እንዳከራየ አድርጎ የሚናገረው ተገቢ እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡ 

በውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡት የኤጀንሲው የተለያዩ ክፍሎች ኃላፊዎች እንደገለጹት፣ ቤቶች ለመንግሥት ተሿሚዎች ይሰጣሉ ማለት፣ ነባር ተከራዮች ይፈናቀላሉ ማለት አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአንድ አፓርትመንት ውስጥ ብዙ ተከራዮች ስላሉ፣ ወደ ሕንፃዎቹ ማን እንደሚገባ፣ ማን እንደሚወጣና ማን ነዋሪ እንደሆነ ለይቶ ለማወቅ፣ እንደሁም በዓለም ደረጃ ሥጋት እየፈጠሩ ያሉ አንዳንድ ችግሮች በዚህም እንዳይከሰቱ የደንበኞቹንም ደኅንነት ለመጠበቅ ጭምር መሆኑን፣ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ይገዙ አስረድተዋል፡፡ 

ኤጀንሲው ያስጨነቀው የደንበኞቹን ደኅንነት እንዴት መጠበቅ እንዳለበት መሆኑን የሚያሳየው ለ40 ዓመታት በነበረው የኪራይ ተመን አከራይቶ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ደንበኞች የሕንፃዎችን ደኅነነት ጠብቀው እንዲኖሩና በአብዛኛው መታደስ ያለባቸው ሕንፃዎች ስላሉ ተባብሮ ለማደስ እንዲቻል ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዝቅ ባለ የኪራይ ዋጋ የተከራየ ደንበኛ የቤቱን፣ የግቢውንና የአካባቢውን ንፅህና መጠበቅ እንዳለበትም አክለዋል፡፡ 

ለዜጎች ነፃነት ለመታገል ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ ትግል ቦታ ወጥተው የነበሩ ታጋዮች በመንገድና በቱቦ ሥር እየኖሩ ባለበት ሁኔታ፣ በአራትና በስድስት ብር የተከራዩ የኤጀንሲው ደንበኞች የቤቱን ንፅህና አለመጠበቃቸው አሳዛኝ መሆኑን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኃይለ ማርያም፣ ከኤጀንሲው ባከራዩት ቤት አሥር ሕንፃ የሚያስገነባ ሀብት ያገኙ ነጋዴዎች አንድ ጋሎን ቀለም መግዛት አቅቷቸው ሕንፃው ቆሽሾ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ 

 

የአንጎል የደም ሥሮች ደም የማዘዋወር ሥራቸውን ሲያቋርጡ አለያም በአንጎል ውስጥ ደም ሲፈስ የሚከሰት ድንገተኛና አደገኛ የሕመም ሁኔታ ነው።

የሕመሙን ምልክቶች፤ ለድንገቱ አጋላጭ የሆኑትን ሌሎች የሕመም ዓይነቶች፥ የመከላከያ አማራጮችና እንዲሁም አጣዳፊ የሕክምና እርዳታና ሊገኙ የሚችሉ ውጤቶች የሚመረምር ተከታታይ ዝግጅት ነው።

በሕክምናው ዘይቤ “ስትሮክ” (Stroke) በሚለው መጠሪያው የሚታወቀውን የዚህን የጤና ሁከት ምንነት ጨምሮ ሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች የሚመልሱት በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በአትላንታ ከተማ በነርቭና በአንጎል ሕክምና አማካሪ ሃኪምነት በማገልገል ላይ የሚገኙት ዶ/ር ዳንኤል ተስፋዬ ናቸው።

 

ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2 ፣ 2015) የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት ) ማእከላዊ ኮሚቴ ከአመታት በፊት በጡረታ የተገለሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች በድጋሚ እንዲደራጁ አዘዘ። ባለፈው እሁድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመቀሌ ከተማ ጉባኤ ያካሄደው የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ፣ በትጥቅ ትግሉ ወቅት እንዲሁም በጡረታ ሰበብ የተሰናበቱ ታጋዮች ዳግም የማደራጀት ስራ እንዲካሄድ ወስኗል። ከአመታት በፊት በእድሜና በተለያዩ ምክኒያቶች …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2 ፣ 2008 ዓም) በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል በአባይ ግድብ ዙሪያ ሊካሄድ የነበረው ድርድር መዘግየትን ተከትሎ፣ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ከሱዳን ጋር የሚመክር የልዑካን ቡድን ወደ ሃገሪቱ ላኩ። በሃገሪቱ የመስኖ ልማት ሚኒስትር ሆሳም ሞግሃዚ የተመራው ይኸው ልዩ የልዑካን ቡድን፣ ከፕሬዚዳን አልሲሲ የተላከን ልዩ መልዕክት በመያዝ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር ለመምከር ካርቱም መግባቱን አል-አህራም …

ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2, 2008ዓም) በቅርቡ ወደሶማሊያ የተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል ለሁለተኛ ሳምንት ከባድ ውጊያ ኣያካሄደ ኣንደሚገኝ የሶማሊያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ትናንት ገለጹ። ለሁለተኛ ሳምንት ቀጥሎ የሚገኘው ግጭት ልዩ ስሙ አልዩ ዲዮ በተባለ ደቡባዊ ምዕራብ የሶማሊያ አካባቢ እየተካሄደ እንደሚገኝ እነዚሁ ወታደራዊ ባለስልጣናት ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በአካባቢው እየተካሄደ ባለው ውጊያ፣ የኢትዮጵያ …

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስትና አለማቀፍ ድርጅቶች በሰጡት መረጃ መሰረት የተረጂው ጠቅላላ ቁጥር 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ደርሷል፡፡ መረጃዎች ግን ከዚህ በላይ መሆኑን ያመለክታሉ። የተጠቀሰው አሃዝ ቀደም ሲል በሴፍቲኔት ፕሮግራም ታቅፈው የሚረዱ ወደ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኢትዮጵያዊን ወገኖችን ይጨምራል ተብሎአል። ይሁን እንጅ መንግስት ያዘጋጀው እና አለማቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች የሚጠቅሱት ሰነድ …

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳ በርጋ ወረዳ 30 ወጣቶች በኦሮምያ ልዩ ሃይሎች በሌሊት ታፍነው መወሰዳቸውን ሂውማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ ገለጸ። ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ አብዛኞቹ የታሰሩት ወጣቶች የናይጀሪያዊው ባለሀብት ንብረት የሆነው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች እና ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች …

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብር ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእስር ቤት አስተዳዳሪዎች በሚያሳድሩበት ጫና ለተጨማሪ ስቃይ እየተዳረገ መሆኑን የሙያ አጋሮቹ ተናግረዋል። የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ውቤ እንደገለጹት፣ እስክንድርን ከሁለት የቅርብ የቤተሰብ አባላት ውጭ ሌሎች ሰዎች እንዳይጥቁት ተከልክለዋል። በሃይማኖት አባቶችም ሆነ በጠበቃ እንደማይጎበኝ የገለጸው …

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦህዴድ ላለፉት 2 አመታት ከተማዋን ሲመሩ የነበሩትን አቶ አብርሃም አዱላን ወደ ክልል ቢሮ በማዛወር የሻሸመኔ ከንቲባ የሆኑትን ለከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አዲሱ ከንቲባ በሻሸመኔ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በማሰቃት የሚወነጀሉ ሲሆን፣ ለአዳማ የተወሳሰበ ችግር መፍትሄ ያመጣሉ ተብሎ እንደማይታመን ምንጮች ይገልጻሉ። ነባሩ ከንቲባ፣ በደባል ሱሶች በመጠመድ ያለፉትን ሁለት አመታት …

Minilik Salsawi – መቸም ራስን ማወቅ ራስን ማግኘት የመሰለ ነገር የለም::ይህ እውቀት አዘል ለሆነ ለበሰለ ሰው ይገባዋል:: ስሜትና ፕሮፓጋንዳ ለተደበላለቁበት ጫፍ አንባቢ ዘራፍ ባይ ደግሞ ላይዋጥለት ይችላል::የለውጥ ሃይል ነን የምንል ከሆነ ቆም ብለን ራሳችንን ልንዳብስ ይገባል ልንፈትሽም ይገባል:: ሃገር እየፈረሰ …

ጥፋተኞችም እኛ … መፍትሄዎችም እኛው …..የለውጥ ሃይሎች ነን የምንል ቆም ብለን ልናስብ ይገባል:: Read more »

በኦነግ አባልነት የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር ተከለከለች ‪#Ethiopia #Oromo በ2004 ዓ.ም በኦሮሞ ነፃአውጭ ግንባር (ኦነግ) አባልነት ተጠርጥራ ከታሰረች በኋላ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር መከልከሏን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘው አሊማ (ቢፍቱ) …

በኦነግ አባልነት የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር ተከለከለች ‪ Read more »

«ሱዳን የወደብ መሬት ሰጠችን Âť Samuel Zewoin ልክ የዛሬ አምስት አመት ገደማ በ October 2010 ፔሩ ወደብ አልባ ለሆነችው ቦሊቪያ ለንግድ ለመዝናኛ እና ለባህር ሐይል ግልጋሎት የሚሆን ቁራሽ የባህር ጠረፍ መሬት ለ 99 አመት በሊዝ መልክ በመስጠት ስምምነት ተፈራርመው ነበር። …

«ሱዳን የወደብ መሬት ሰጠችን Âť ወደብ ተገነባ አንዳች ነገር ቢፈጠር አንደ አሰብ ቢሊዮኖችን ለባዕድ ልናስረክብ ? Read more »

የባንክ ዘራፊ የሆነው እና ከኢኖቫ ፋየርፋክስ ሆስፒታል እጅግ በሚገርም ሁኔታ ያመለጠው ከዘጠኝ ሰአታት አደን በኋላ በቁጥጥር ሾር የዋለው ኢትዮጵያዊው ወሰን አሳዬ የሰላሳ ሁለት አመት ፍርድ መከናነቡን የፍትህ ባለስልጣናት አስታውቀዋል:: የአርባ ሶት አመት እድሜ ባለጸጋው ወሰን አሳዬ ላይ አቃቢ ሕግ እንዳለው …

በቨርጅንያ ከእስር አምልጦ የነበረው ባንክ ዘራፊ ኢትዮጵያዊው ወሰን አሳዬ 32 ዓመት ተፈረደበት። Read more »

ቅጥ አንባሩ የጠፋው የኢትዮጵያችን ፖለቲካ በዋነኝነት የሚጎድለው ልክ ያልሆነን ነገር ልክ አይደለም ማለት ያለመቻል ነው፡፡ በግል አስተያየት ልክ አይደለም ብሎ መቆም ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ የተሳሳተ ውሳኔ ባለቤቶች በድጋሚ ጥፋታቸውን በጥፋት ለማረም ሌላ ስህተት ይደግማሉ፡፡ አሰተያየትን በአሰተያየት ለመመለሾ ይከብዳቸዋል፡፡ የዚህ ደግሞ …

ኢህአዴግ በሚጠራው መድረክ አለመገኘት ማንን ይጠቅማል? ግርማ ሠይፉ ማሩ Read more »

ወንድማችን ሃብታሙ አያሌዉ በጠና ታሞ ትናንት ምሽት ዘዉዲቱ ሆስፒታል ለህክምና ገብቷል፡፡የህመሙ ምክንያት ለቤተሰቡ ያልተገለጸ ሲሆን ባለቤቱም ገብታ እንድትጥቀዉ ያልተፈቀደላት መሆኑን (እንባ ባላባሩት አይኖችዋ ዘለላዎችን እያፈሰሰች በለቅሶ ታጅባ) ትናገራለች፡፡ሰሞኑን በሙሉ ጤና እንደነበር ቂሊንጦ እስር ቤት ሄደዉ የጠየቁት ጎዶች ይናገራሉ፡፡

Habtamu ayalew . abrha desta .yeshiwas . daniel shibeshi in Ethiopian Prison

ጀግኖቹ የነፃነት ታጋዮች ኣብራሃ ደስታ፣ ሃብታሙ ኣያሌው፣ የሺዋስ ኣሰፋና ዳኒኤል ሺበሺ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ጀግኖቹ የተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ “… መሰረት የሌለው ውንጀላ ነው ሰዎቹም ከክሱ ነፃ ናቸው…” ብለው ዳኞች ውሳኔ የሰጡት ሲሆኑ ዓቃቢ ህግ ይግባኝ በመጠየቁ ክእስር ሳይለቀቁ ቀርተዋል። …

ኣብራሃ ደስታ፣ ሃብታሙ ኣያሌው፣ የሺዋስ ኣሰፋና ዳኒኤል ሺበሺ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። Read more »

ዛሬ ወደአንድ ሆስፒታል ጎራ ብየ ነበር ….(አይዞን በሰላም ነው) እና የገረመኝን ነገር አስተዋልኩ ባለቤቱን ጨምሮ አራት ዶክተሮች አሉ አራቱም ከአንድ ብሔር የወጡ ለመሆናቸው የአነጋገራቸው ቅላፄና ስማቸው ይገልፃል …. የገረመኝ ይሄ አይደለም ነርሶቹ ሁሉም በሚባል ሁኔታ ከአንድ ብሄር የወጡ መሆናቸውን ማወቅ …

ይሄ ነገር ዘረኝነት ይሆን እንዴ፡) (አሌክስ አብርሃም) Read more »

እስከ 360 ሺሕ ብር ከፍተኛ ውዝፍ ያለባቸው ተከራዮች እንደሚገኙበት ታውቋል በቤተ ዘመድ የተሸፋፈነው የክፍያው አሰባሰብ የአስተዳደር ጉባኤ አባላቱን አወቃቅሷል በፍሳሽ እና በቃጠሎ አደጋ የተጎዳው ሕንጻ ከዕድሳት ዕጦት ደኅንነቱ ለአደጋ ተጋልጧል *          *          * ሓላፊው፣ በደንቡ መሠረት ለአስተዳደር ጉባኤው የሒሳብ ሪፖርት አቅርበው አያውቁም የበጀት ዓመቱ የኻያ በመቶ የፈሰስ …

ዜጎች በተራ ‹‹ወንጀል›› 14 ከዚህ አለፍ ሲል 28 ቀን እየተቀጠሩ በሚመላለሱበትና በሚጉላሉበት ሀገር፣ አባሪው እንኳ ባልተያዘበት ሁኔታ፣ ይህ ነው የሚባል ምርመራ ሳይደረግ የሳሙኤል አወቀ ገዳይ በ17 ቀን ውስጥ 19 አመት እስራት እንደተፈረደበት ተሰምቷል፡፡ ትናንት ችሎቱን የተከታተሉት ሰዎች በግምት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ አዲስ አበባ ለሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የነበረውን ድራማ በስልክ ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ […]

The post የሳሙኤልን ገዳይ መደበቅ ያልቻለው ድራማ – ጌታቸው ሺፈራው appeared first on ሳተናው .

የኢትዮጵያ መንግሥት በቀጣይ አምስት አመታት ተግባራዊ ሊያደርጋቸው ባቀዳቸው ነጥቦች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ከተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጋር ዕርብ ዕለት ተወያይተዋል።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአመት የዘለቀው የቴፒ ግጭት በአካባቢው ለሰፈረው የፌደራል ፖሊስ እና ለፌደራል ባለስልጣናት እንቆቅልሽ ሆነ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ባለፈው ቅዳሜ ከሌሊቱ 6 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ሚሊኒየም ጎዳና ላይ ወይም ሚካኤል አካባቢ ካሳሁን የተባለ የከተማው ፖሊስ አባል ተገድሏል። ፖሊሱ በቅርቡ ለከተማው ተመድቦ የመጣ ነበር። እርምጃውን የወሰዱት ራሳቸውን የቴፒ ወጣቶች …

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በተነሳው ግጭት ከፖሊስና ከመከላከያ አንዳንድ ወታደሮች ቆስለዋል። የግጭቱ መንስኤ ሁለት የመከላከያ ፖሊስ አባላት በፖሊሶች መደብደባቸው ነው። ከዚህ ቀደም አንድ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ፍቼ አካባቢ ሰፍሮ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት አባል ከገደለው በሁዋላ፣ በመከላከያና በፖሊስ መካከል ለወራት የዘለቀ ቁርሾ እንዲፈጠር አድርጓል። ባለፈው ቅዳሜ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት …

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ከሚገኙ አምራች አካባቢዎች አንዱ በሆነው በየዓመቱ ከሰኔ እስከ ህዳር ወር ድረስ ከፍተኛ የሰራተኛ ቁጥር የሚያስተናግደው የምዕራብ አርማጮኾ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች የሚገኙ የጤና ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸውን በጀት የክልሉ መንግስት ባለመመደቡ በየአመቱ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳልቻሉ የወረዳው የጤና አመራሮችና ባለሙያዎች ተናገረዋል፡፡ በምዕራብ አርማጮኾ ወረዳ ያለው …