ይድረስ ለኩሩዋ የሃገሬ ሴት በሙሉ መስዋእትነት ከፍለን ይህን ሃገር አጥፊ ቡድን እናስወግድ።
ይድረስ ለኩሩዋ የሃገሬ ሴት በሙሉ በሙሉ መስዋእትነት ከፍለን ይህን ሃገር አጥፊ ቡድን እናስወግድ።
አንቺ የኢትዮጵያ ዉብ ሴትሆይ፤ አንቺ በሃገርሽ ስራ አጥተሽ በየአረብ ሃገሩ የምትንከራተቺው የኢትዮጵያ ኩሩ ሴት፤
አንቺ በሃገርሽ ለሃገርሽ ሰርቶ ለመኖር ተምረሽ ስራ አጥተሽ የምትንከራተችው ኢትዮጵያዊት፤
አንቺ በስርአቱ አስተዳደር ችግር የተነሳ ኑሮ ተወደብሽ ኑሮ ለማሸነፍ ስትይ ሳትወጅ ገላሽን ሸጠሽ ለመተዳደር የተገደድሽው ምስጊን ኢትዮጵያዊት፤
አንቺ ለወገንሽ በመቆርቆርሽ በየእስር ቤቱ የምትንገላቺው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ አንቺ ስራም ብታገኚ በሃገርሽ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተሳቀሽ የምትኖሪው እውን አንቺን የመሳሰለ ስንት ለሃገሩ መስራት የሚችል እያለ ከቻይና ሆስቴስ ያስፈልጋልን?
ይህን የመሳሰለ ስንት በስርአቱ ሆን ተብሎ አንቺን የሚጎዳ ጉድ እንዳለ ተገንዝበሽዋልን?
ዝምታሽ ከቀጠለ ነገ የሚፈጠረውን አስተውለሽው ይሆን?
ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ይህን ስርአት ማስወገድ ብቻ እንደሆነ ልብ ብለሽ ው ይሆን?
እንግዲያውስ መፍትሄውን እንነጋገር እንደኔ ከሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ስርአት ለማስወገድ አንድ እርምጃ ሄድዋል ይህ አካሄድ እንዲሳካ ያንቺ በትግሉ ተሳትፎ ጉልህ ሚና ይጫወታል።
ታድያ ይህን ከግምት በማስገባት የኢትዮጵያ ሴቶች ተደራጅተው ስርአቱን አስወግደው ከማስወገድም አልፎ በህዝብ የተመረጠ ህዝብን የሚወክል ህዝባዊ መንግስት ለመመስረት የሚደረገው ትግል ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆን ያስፈልጋል። አንድ እንሁን ከዚህ ከገለማ ስርአት ምንም አንጠብቅ የሚያስፈልገውን መስዋእትነት ከፍለን ይህን ሃገር አጥፊ ቡድን እናስወግድ።
Fetsume Mengesha
