ኣብራሃ ደስታ፣ ሃብታሙ ኣያሌው፣ የሺዋስ ኣሰፋና ዳኒኤል ሺበሺ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
Habtamu ayalew . abrha desta .yeshiwas . daniel shibeshi in Ethiopian Prison
ጀግኖቹ የነፃነት ታጋዮች ኣብራሃ ደስታ፣ ሃብታሙ ኣያሌው፣ የሺዋስ ኣሰፋና ዳኒኤል ሺበሺ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
ጀግኖቹ የተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ “… መሰረት የሌለው ውንጀላ ነው ሰዎቹም ከክሱ ነፃ ናቸው…” ብለው ዳኞች ውሳኔ የሰጡት ሲሆኑ ዓቃቢ ህግ ይግባኝ በመጠየቁ ክእስር ሳይለቀቁ ቀርተዋል።
ድሮም በሰለማዊ መንገድ ከሰላማዊ ድርጅቶች ጋር ተደራጅተው ከመታገል የዘለለ ጥፋት እንዳልነበረባቸውና በፖለቲካዊ ልዩነት ምክንያት የታሰሩ መሆኑ ግልፅ ነበር።
ጀግኖቹ የቃል ክርክር ለማድረግ ነገ እሮብ ከጥዋቱ ሁለት ተኩል 03 / 02 / 2008 ዓ/ም በጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎት ይቀርባሉ።
ጀግኖቹ ነፃ እንደሆኑ እናውቅ ነበር፣ ፍርድ ቤትም ነፃናቸው ብሎ ፍርድ ሰጠ። በፍርዱ መሰረት ከእስር መለቀቅ ነበረባቸው፣ ይግባኝ ቢባል እንኳ ውጭ ሁነው የመከራከር መብት ነበረባቸው።
ሕግ ተጥሶ እስካሁን ቃሊቲ እስር ቤት ቆይተተዋል።
ጠቅላይ ፍርድቤቱ “ነፃ ይፈቱ” የሚለው ፍርድ እንደሚያፀድቀው እንጠብቃለን።
ባርያ ሁነህ ሺዓመት ከመኖር ነፃ ሁነህ መሞት ይሻላል።
በኣዲስ ኣበባ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ጠቅላይ ፍርድቤት ድረስ በመሄድና ችሎቱ ላይ ተገኝታቹ ከጎናቸው እንድትቆሙ እንጠይቃለን።