ጥፋተኞችም እኛ … መፍትሄዎችም እኛው …..የለውጥ ሃይሎች ነን የምንል ቆም ብለን ልናስብ ይገባል::
Minilik Salsawi – መቸም ራስን ማወቅ ራስን ማግኘት የመሰለ ነገር የለም::ይህ እውቀት አዘል ለሆነ ለበሰለ ሰው ይገባዋል:: ስሜትና ፕሮፓጋንዳ ለተደበላለቁበት ጫፍ አንባቢ ዘራፍ ባይ ደግሞ ላይዋጥለት ይችላል::የለውጥ ሃይል ነን የምንል ከሆነ ቆም ብለን ራሳችንን ልንዳብስ ይገባል ልንፈትሽም ይገባል:: ሃገር እየፈረሰ ወገን እየታሰረ እየሰደደ እየተንገላታ ከዚህም አልፎ እየተገደለ ነው:: በየማህበራዊ ድህረገጹ የሚወራው ሆይሆይታ እና መሬት ላይ ያለው ጉዳይ ደሞ አይገናኝም::እውነተኛ የትግል መንፈስ ይዞ ትክክለኛውን ግብ ለመምታት መፍትሄ መሆንን የመሰለ ነገር የለም:: መፍትሄው ደሞ እኛ ራሳችን ነን::ስለ ዘረኝነት ስለ ጀግንነት ስለ ልማት ስለ አዋቂነት ስለ ጡዘት ስላሌለ ነገር ወዘተ እየተሰበክን ነው:: እኛም ከየወገን ወገኑ ሆነን እየተቧደንን በየአጀንዳው ውሮሸባውን እያቀለጥነው ነው::
ከአመት አመት የምንናገረው ነገር አለ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል::የፖለቲካ ጫና ከጫንቃው ላይ እንደወርድ ይሻል::የኑሮ ውድነት ወገቡን ቆርጦታል::የማህበረሰቡ መዘበራረቅ ራስ ምታት ሆኖበታል ከዚህ ጋር በተመሳሰሉ ሂደቶች በአምባገነኖች ጡጫ የሚዋዥቀው ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል::ለዚህ ለውጥ ደግሞ ሁላችንም በየፊናችን እየሮጥን ነው::ሲለን ተቧድነን ሲለን ተነጣጥለን ሲለን ተፈራርጀን ሲለን አሽሟጠን ሲለን ተሰዳድበን ሲለን ሲለን ሲለን .. ኧረ ስንት ጉድ አልፈናል::ካልፈው መማር ከጥፋታችን መታረም መፍትሄም ማበጀት ለትግሉ ጠቀሜታ አለው::አንዱን እየፈረጀ አንዱ ቢሮጥ ባለህበት እርገጥ ካልሆነ በስተቀር ምንም አይፈይድም ከወያኔ ምን እንማራለን?ልብ ብለን ከተመለከትን የወያኔ ካድሬዎች ከአንድ ፋብሪካ ተመርጦ የወጣ እባብ ይመስል ሁሉም አንድ አይነት መርዝ በኛ ላይ ይረጫሉ::እኛ ደሞ እርስ በርሳችን ስንበራረዝ ለነሱ በር በመክፈት መርዛቸው እናራባለን::ይህ መሆን የለበትም::እኛም ወያኔን ለመጣል እስከተነሳን ድረስ በጋራ ሆነን እርስ በርስ ሳኮራኮም ሳንፈራረጅ ከኛ በላይ ላሳር ሳንል መርዞቻችንን በጋራ ጠላታችን በሆነው ወያኔ ላይ መርጨት ያስፈልጋል::
ድርጅታዊ ዲሲፒሊን ግለሰባዊ ግብረገብነትን መተግበር ይጠበቅብናል::የለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ነን ማለት ጠላታችን ወያኔ ነው ማስወገድ ያለብን ወያኔን ነው ማለት ነው::ቆም ብለን ረጋ ብለን ማሰብ አለብን::አንዱ የለውጥ ሃይል ሌላውን ቢንቀው ምንም የሚመጣ ለውጥ የለም ባለንበት ከመርገጥ ውጪ::አትኩሮታችን ሁሉ ወያኔን ማስወገድ ይሁን::እኛ የለውጥ ሃይሎች ስንባላ ወያኔ ስራዋን ትሰራለች::እኛ ስንተባበር ግን ወያኔ ያሰበችውን ሁሉ እናኮላሽባታለን::በየማህበራዊ ድህረገጹ ላይክ ኮሜንት እና ሼር ከመቁጠር ይልቅ ከመፈራረጅ ይልቅ እየፈረሰች ያለችውን አገር በጋራ እናቅና::በማይሆን ነገር ራስን ማጭበርበር ይብቃ::በጋራ በአንድነት እንቁም::መንቃት ያስፈልጋል::አትኩሮቶች ሁሉ ወያኔን እና የወያኔን እኩይ ተግባራት ወደ መደምሰስ ይሁኑ::በማይሆን አጀንዳ ተዘናግተን አንባላ::ሃገራችንን ከአውሬዎች እናድን::እንንቃ::ከባለፈው እንማር::አትኩሮቶች ሁሉ በወያኔ መደምሰስ ላይ ከሆኑ ተረባርበን በጋራ ከቆምን ከባለህበት እርገጥ ወጥተን አሸናፊነታችንን እናረጋግጣለን::ድል የሰፊው ሕዝብ ነው!!#ምንሊክሳልሳዊ
You are correct thank you
Let us start fighting rather than writing to blame woyanes. Enough is enough
Ginbot7 Arbegnochginbar is paying its blood for freedom so why not we join them rather than shouting for 24 Years long
I am investing on AG7.I am not sitting and watching.Support a movement you believe in.ባለመታደል ተቃዋሚ ነን ብለው አገር ውስጥም አገር ውጭም ያሉ አብረው መስራት አልቻሉም።እስቲ መቸም መድረክን እንተወው ልክ እንደ ወያኔ የዘር ስብስብ ነው። Can some one tell me why መኢአድ፥አንድነት and ሰማያዊ are not working together ? ? ? እነዚህ አንድ አጀንዳ ይዘው በተልያየ ጎራ ሆነው ጊዜ እና resource የሚያባክኑ ጉዶች ቁመንለታል የሚሉት የኢትዮጵያ ሕዝብ የመከራ ዶፍ እየወረደበት እነሱ ገና ባልተገኘ ስልጣን ሲባሉ ተስፋ አያስቆርጥም ትላላችሁ ? ? ? አበስኩ ገበርኩ ነው ! ! !
Oh ! ! ! bravo Gilentufa. Although I have a serious doubt that Isayas will be willing to see a free Ethiopia,I am supporting አርበኞች ግንቦት ሰባት and I hope they will come up with one name than sticking to this weird ጥምር ስም። I believe adopting one name is a sign of confidence between the two and the sooner is the better.
ወያኔ ከሥህተቱ የማይማር አድሮ ጥጃ የወረበላ ሥብሥብ ነው!!!
የወያኔ ጅራፍ ራሡን ገርፎ ራሡ ይጮሀል
ወያኔን to start off,እንደሰው ትቆጥረዋለህ እንዴ ? ? እንደሰው ከቆጠካቼው ትልቅ ስህተት ተሳስተሃል ወንድሜ።ከአራዊትም በታች ናቸው እኮ።ከስህተቱ የሚማር እኮ የሰው ስብዕና መላበስን ይጠይቃል። ታላቁ የብዕር ሰው” ጠላቶቻችን እንወቃቸው” ያለውን አስታወስከኝ ወንድሜ።ነብሱን በገነት ያኑርልን የውዱን የሙሉጌታ ሉሌን።ጠላትክን እወቅ ወንድሜ ! ! !
ሚኒሊክ ሳልሳዊ ሰላይ ነው:
ለአባይ ቦንድ በመግዛቴ ኩራት ይሰማኛል