“ወያኔዎችን አጥኗቸው፣ እወቋቸው“ ሙሉጌታ ሉሌ
በልጅግ ዓሊ
“ደግ ደጉን ስናጣ፣ ኀዘኑ መረረ
ሞት አምላኩ ከድቶት፣ ገሎት በነበረ።”
– የሠፈራችን ሙሾ አውራጅ
እነሆ ጋሼ ሙሉጌታ ዐረፈ። ከዚህ ምስቅልቅሉና ቅጥ አምባሩ ከወጣ ዓለም በአካል ተለየ። ጋሼ ሙሉጌታ ከእንግዲህ የሀገሩን አፈር በሞቱ እንኳ ላይቀምስ ነው። ዛሬ የሰው ሀገር አፈር ለብሶ በዝምታ ማሸለቡን መርጧል። ሀገሩን እንደናፈቀ የተለያት ቢሆንም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር ትምህርት ሰጥቶን አልፏል።