ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሶስት መቶ መንገደኞችን ጭኖ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በደብሊን አድርጎ ወደ አሜሪካ ሲጓዝ የነበረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ድሪምላይን 787-8 አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ ላይ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር በድንገት አንድ ሞተሩ አየር ላይ ቢጠፋም በአየርላንድ ዋና ከተማ ደብሊን በሰላም ማረፍ ችሏል። መንገደኞቹ ከጀርመን ፍራንክፈርት በተላከ ተቀያሪ …

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊ ግብጽ ሉዞር ላይ በባቡር አድርገው በህገወጥ መንገድ የግብጽን ድንበር ተሻግረው የገቡ አስራ አንድ ሶማሊያዊያን እና አስር ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዛቸውን የአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ምንጭ ጠቅሶ ዮም ሰበን ዘግቧል። በህገወጥ መንገድ በግብጽ አድርገው ወደ ሊቢያ የሚገቡ ስደተኞች በቅርብ ጊዜያት ውስጥ እየበዙ መሆናቸውንና ከ2 ሺ 215 በላይ …

” የመጣው እርዳታ ጥቂት ነው … !” ~*~*~*~*~*~*~*~*~ (የቀበሌ ኣመራሮች) Amdom Gebreslasie  በኣሁኑ ወቅት በሃገር ኣቀፍ ደረጃ ከ8.3 ሚልዮን ህዝብ የድርቅ ሰለባ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በድርቅ የተጠቁ የትግራይ ቀበሌዎች ኣመራሮችና ካድሬዎች ህዝቡን እየሰበሰቡ ” ለቀበሌያችን የተመደበ የእርዳታ እህል በጣም ጥቂትና …

በድርቅ የተጠቁ የዓረና ኣባላት በትግራይ የእርዳታ እህል ድርጅታቹ ይስጣቹ ተብለው ተለይተዋል። Read more »

  ከነጭ ሽንኩርት ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን እነሆ  ነጭ ሽንኩርት በውስጡ ከያዘው የሰልፈር ማዕድን የተሰሩ አለይን እና አሊሲይን የተባሉ ኬሚካሎች በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የቅባት ክምችት ይቀንሳሉ፡፡ – የምግብ መፍጨት ሂደቱ የተቀላጠፈ እንዲሆን ያደርጋል – የደም ውስጥ ኮሌስትሮልን ይቀንሳል – የደም ግፊትን …

የነጭ ሽንኩርት ጠቀሜታዎች Read more »

ሃምሣ ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለማስገባት የሚያስችል የዲቪ (Diversity Visa) ዕጣ መርሃ ግብር በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር ለ2017 ዓ.ም መዘጋጀቱን አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ገለፀ።

ካለፈው አመት የፈረንጆቹ ሰኔ ወር መባቻ ላይ ወደ ኤርትራ ሲጓዙ የመን(ሰነኣ ) አለም አቀፍ አወሮፕላን ጣቢያ ላይ ታፈነው ለ አዲስ አበባ መንግስት ተላለፈው የተሰጡት እና ቀደም ሲልም በሌሉበት ኢትዮጵያ ውስጥ በ 2009 አኤአ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው የግንቦት 7ቱ ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እጣ ፈንታ ያሳሰበው አንድ ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእንግሊዝ መንግስት “ለጥቅሙ […]

ሲኖዶስ ማለት፡- ሲኖዶስ፣ ቃሉም ሥራውም የምሥራቃውያን ነው ቃሉ ግሪክኛ ኾኖ የአንድነት ስብሰባ ማለት ነው የእኛ ቤተ ክርስቲያን ከምሥራቃውያን አንዷ ነች ቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊትና ሲኖዶሳዊት ነች የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ፡- የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እንደ ማንኛውም ጉባኤ አይደለም፤ የቤተ ክርስቲያን የበላይ መሪዎች ስብሰባ ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ ስለሚመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ተብሎ ነው የሚጠራው፤ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል እንደተባለው፤ …

ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ሞያሌ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ወጣቶችን ለውትድርና ለመመዝገብ በድምጽ ማጉያ የታገዘ ቅስቀሳ ቢያካሂዱም፣ አንድም ለምዝገባው ፈቃደኛ ሆኖ የሄደ ወጣት አለመኖሩን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ። ወጣቶቹ የተደረገላቸውን የስብሰባ ጥሪ ባለመቀበላቸውም፣ መንግስት በሞያሌና አካባቢዋ አዳዲስ ምልምል ወታደሮችን ለመመዝገብ ያቀደው እቅድ ሳይሳካ ቀርቷል። አምና 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ወጣቶችን ለወትድርና …

ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-35ኛ አመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ ያለው ብአዴን ፣ በአማራ ክልል የሚኖረው ህዝብ ለበአሉ ማድመቂያ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያስገደደ ነው። ነጋዴዎች ከብአዴን ጽ/ቤት የተጣለባቸውን ክፍያ ያለፍላጎታቸው በግድ እንዲከፍሉ ታዘዋል። ከፍተኛ የረሃብ አደጋ በክልሉ ባንዣበበት በዚህ ወቅት፣ ብአዴን እንደ ህወሃትና ኦህዴድ መቶ ሚሊዮኖችን አፍስሶ በአሉን ለማክበር መሞከሩ ፣ ከታሪክ …

ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሳምብሩ ምስራቃዊ ኢዞሎ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ሎሲሳ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገቡ ያላቸውን አስራ አምስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሩን አስታውቋል። ባለፈው እሁድ ሃያአራት፣ ሰኞ ደግሞ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአካባቢው በታጣቂዎች በከበባ መያዛቸውን ገልጸዋል።ስደተኞቹ በሕገወጥ መንገድ ካለምንም ሕጋዊ ፍቃድ ድንበር አቋርጠው እንደሚገቡና አስራ አምስቱ ኢዞሎ …

በሣይንሳዊው መላ ምት ዘመናዊው የሰው ልጅ ምድር ላይ ተገኘ የሚባለው ከዛሬ 200,000 ዓመት በፊት ነው። ይኽ በሣይሳዊ አጠራሩ ሆሞ ሳፒያንስ (Homo Sapiens)፥ በላቲን ትርጓሜው ደግሞ «ጥበበኛው ሰው» አለያም «አዋቂው ሰው»፣ «ብልሁ ሰው» የሚል ስያሜ ያገኘው ዘመናዊ ሰው ምንጩ ከአፍሪቃ ብሎም ከኢትዮጵያ እንደሆነ ይነገራል።

በኢትዮጵያ የረሃብተኛው ቁጥር ወደ 11.3 ሚሊዮን አሻቅቧል::ወገን በጠኔ እየረገፈ ቀባሪ እየጠፋ ነው::

የወያኔው አገዛዝ ቅድመ ጥንቃቄ ያላደረገበት በተኮፈሱ ፖሊሲዎች እና በተቆለሉ ቁጥሮች ተተብትቦ በሃስት ፕሮፓጋንዳ በሚቦዝንበት በዚህ ወቅት የረሃብ አደጋውን ሞቅ ቀዝቀዝ እያደረገ ሰበቡን በተፈጥሮ ላይ በመላከክ የሕዝብን ሃሳብ ወደ ሌላ በመውሰድ አጀንዳው ለማጠፍ በሚታታርበት በዚህ ወቅት የረሃብተኛው ቀጥር ወደ 11.3 ሚሊዮን …

በኢትዮጵያ የረሃብተኛው ቁጥር ወደ 11.3 ሚሊዮን አሻቅቧል::ወገን በጠኔ እየረገፈ ቀባሪ እየጠፋ ነው:: Read more »

የፀጥታው ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 2009 በኤርትራ መንግሥት ላይ ከጣለው የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ማለትም የፖለቲካ መሪዎችና ወታደራዊ አመራሮች ሀብት እንዳይንቀሳቀስ፣ እንዲሁም በእነዚህ አመራሮች ላይ ከጉዞ ማዕቀብ ውጪ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን በዲሴምበር 2011 ላይ ጥሏል፡፡ ይህ የኢኮኖሚ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ግፊት በኢጋድ …

ኤርትራ የተጣለባት ፍትሐዊ ያልሆነ ማዕቀብ እንዲነሳላት ተማፀነች :: Read more »

በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ትግበራው የተጀመረው ዘመናዊው የኹለትዮሽ ሒሳብ አሠራር፣ በሥልጠና ተደግፎ ግልጽና ተጠያቂ በኾነ መንገድ እስከ አጥቢያ መዋቅር እንዲተገበር የጋራ አቋም ተይዟል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ላለፉት አራት ቀናት ሲካሔድ የቆየው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 34ኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ፣ ዛሬ ቀትር ላይ ተጠናቋል፡፡ የሀገር ውስጥ ኃምሳ አህጉረ ስብከት እና የውጭ ስምንት አህጉረ ስብከት የሥራ ክንውን …

ዓቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሠርት ቀን ተቆርጦለታል 

ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም ከፍተኛ የሆነ ጉቦ በመቀበል አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን በማስገባት፣ በዘመዶቻቸውና በጓደኞቻቸው ስም ሀብት በማስቀመጥ፣ እንዲሁም ለመንግሥት መግባት የነበረበትን

ታክስና ቀረጥ ለግላቸው በማድረግ ከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ወንድሙ ቢራቱ፣ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን የሰጠው፣ በተጠርጣሪው ላይ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ምርመራውን ማጠናቀቁን ካስታወቀ በኋላ ነው፡፡ ቡድኑ ምርመራውን ጨርሶ ለዓቃቤ ሕግ ማስተላለፉን ገልጾ፣ ዓቃቤ ሕግ አቶ ወንድሙን ጨምሮ በአራት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ለመመሥረት የሚያስችለውን በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 109 (1) መሠረት የ15 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

የአቶ ወንድሙ ጠበቃ የተጠየቀውን ጊዜ በመቃወም፣ ደንበኛቸው ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግ ተጠርጣሪውን ዋስትና በሚያስከለክል ወይም በማይከለክል አንቀጽ ስለመክሰሱ ማወቅ እንደማይቻል ፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ የዋስትናውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡  

በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ በአቶ ወንድሙና በሦስት ተጠርጣሪዎች ላይ ጥቅምት 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ክስ እንዲያቀርብ ታዟል፡፡ 

 

ከዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች /ብሎገሮች/ እና ጋዜጠኞች እሥር ቤት ቀርቶ የነበረው በፈቃዱ ኃይሉ በሃያ ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርጅ ቤት አሥራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት አዝዟል።

በሀ/ስብከቱ÷ 55 ከእስልምና 115 ከሌሎች እምነቶች በጥምቀተ ክርስትና ተመልሰዋል   በመካከለኛው ምሥራቅ(በሊባኖስ እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ) ሀገረ ስብከት፣ በዱባይ ከተማ ቤሪያ በተባለ አካባቢ፣ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚነግዱ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ምንደኞች ከቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና ውጭ ስለከፈቱት ኮሌጅ ውሳኔ እንዲሰጥ ሀገረ ስብከቱ ጠየቀ፡፡ ሀገረ ስብከቱ፣ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን በያዘው የመንበረ ፓትርያርክ የሰበካ አስተዳደር አጠቃላይ ጉባኤ 34ኛ ዓመታዊ …

ኢሳት (ጥቅምት 10 ፡ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ እስከተያዘው አመት ማጠናቀቂያ ነሀሴ ወር ድረስ ቀጣይ ሊሆን እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ ማክሰኞ አሳሰበ ። በሀገሪቱ ተከስቶ ያለው የምግብ እርዳታ ፍላጎትም ከአራት አመት በፊት በአፍሪካ ቀንድ ተከስቶ ከነበረው አጠቃላይ መጠን ጋር ሲነጻጸር ከፍ ብሎ መገኘቱን ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። በጉዳዩ ዙሪያ ከለጋሽ ሀገራት የተጠየቁት …

ወደ ቢጫነት የተቀየረ ጥርስን ማከሚያ መንገዶች :-ስለ ውበት ሲታሰብና ያማረ ገጽታን ለመላበስ ሁሉም የሰውነት ክፍሎች በተመጣጠነ መልኩ አይነ ግቡ መሆን ይኖርባቸዋል።   አምሮና ደምቆ መታየት ሲታሰብ ደግሞ የፊት ገጽታ በተለይም ያማረና እና ማራኪ ፈገግታ ቀዳሚው ነው፤ ላማረ ፈገግታ ደግሞ ጤንነቱ …

ወደ ቢጫነት የተቀየረ ጥርስን ማከሚያ መንገዶች Read more »

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረዩተርስ እንደዘገበው የኢህአዴግ መንግስት ባለፉት 10 ወራት 1 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ከግል የውጭ አበዳሪ ባንኮች ከተበደረ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ 2 ቢሊዮን ዶላር ወይም 40 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመበደር በድርድር ላይ መሆኑን ረዩተርስ ዘግቧል። አዲሱ ብድር የኢትዮጵያን እዳ ከ32 ቢሊዮን ዶላር ወይም …

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደገለጹት በአሜሪካ ጊቢ ፣ በአዲስ ከተማና በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለአመታት ከኖሩበት ቤት ያለበቂ ካሳ እና ተለዋጭ ቤት ቤቶቻቸው እየፈረሰባቸው ነው። መንግስት ቤታቸው ለሚፈርስባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ተላዋጭ አድርጎ ቢሰጥም፣ ተከራዮች ግን ኪራዩን የመክፈል አቅም የላቸውም መንግስት ከህዝቡ ጋር ሳይማከር የሚወስደው እርምጃ፣ …

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ዓመት ከአምስት ወር በሽብር ክስ ተከሰው በእስር ሲንገላቱ የነበሩት የዞን 9 አምደ መረብ ጸሐፍት ውስጥ ብቻውን እንዲቀር ተደርጎ የነበረው ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ክሱን ውጪ ሆኖ እንዲከታተል የሃያ ሽህ ብር የዋስትና መብት የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት19ኛ ወንጀል ችሎት በመፍቀዱ ከእስር ተለቋል። በተጨማሪም የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን እሑድ ጥቅምት 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ከብሩንዲ አቻው ጋር ለሚያደርገው የቻን 2016 ወሳኝ የማጣሪያ ጨዋታ አራት ተጨዋቾች በዋና አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ጥሪ ተደረገላቸው፡፡ኤልያስ ማሞ ከኢትዮጵያ ቡና፣ መሐመድ ናስር፣ ነጅብ ሳኒና ፍሬው ሰለሞን ከመከላከያ ከጥቅምት 9 …

ኤልያስ ማሞ፣ መሐመድ ናስር፣ ነጅብ ሳኒና ፍሬው ሰለሞን ለብሔራዊ ቡድን ተጠሩ Read more »

መረጃ ስፖርት:- ሓድነት አስመላሽ የደቡብ አፍሪካውን ታላቅ የብስክሌት ውድድር አሸነፈች::#Ethiopia #Sport #Bicycle በመጪው ነሐሴ በብራዚል ሪዮ ኦሊምፒክ የብስክሌት ተወዳዳሪነቷን ያረጋገጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሓድነት አስመላሽ ጥቅምት 6 ቀን 2008 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የብስክሌት ውድድር አሸነፈች፡፡የደቡብ አፍሪካው ሳይክሊንግ ኒውስ ከሥፍራው እንደዘገበው የ106 …

ሓድነት አስመላሽ የደቡብ አፍሪካውን ታላቅ የብስክሌት ውድድር አሸነፈች Read more »

በኢትዮጵያችን የፖለቲካ ስልጣን ፍትህን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ባላንጣን እና ንጹሃንን ለማጥቃት መጠቀም በወያኔ ጉጅሌ ባለስልጣናት የተለመደ ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ የሆነው የስርኣቱ ሰዎች ፍትህን በወሲብ ድርድር እና በጎሳ እየቸረቸሩት መሆኑን ሰማን አዘንን!!!ግን እስከመቼ?? ተቆጣጣሪ የሌላቸው ለፖለቲካው ተገሺ የሆኑት የፍትህ አካላት …

የስርኣቱ ሰዎች ፍትህን በወሲብ እና በጎሳ እየቸረቸሩት መሆኑን ሰማን አዘንን!!! ግን እስከመቼ?? (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

 -‹‹ምዕመናንን የመጠበቅ ተልዕኮ እየተወጣን አይደለም›› አቡነ ማትያስ ========= የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰበካ ጉባዔ መደራጀት ስትጀምር ገቢዋ በመቶ ሺሕ ብር የነበረ ቢሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ወደ ቢሊዮኖች ብር ማደጉን የገለጹት ፓትርያርኩ አቡነ ማቲያስ፣ የምዕመናኗ ቁጥር ግን እየቀነሰ መሆኑን አስታወቁ፡፡ ፓትርያርኩ 34ኛውን …

የኦርቶዶክስ ገቢ በቢሊዮን ቢቆጠርም የምዕመናኑ ቁጥር እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ Read more »

  -ከፖሊስና ከማረሚያ ቤት በበለጠ ፍርድ ቤት ለሙስና የተጋለጠ መሆኑ ተጠቆመ በኢትዮጵያ የፍትሕ ተቋማት ውስጥ ሙያዊ ሥነ ምግባራቸውን ጠብቀው ሕዝባዊ ኃላፊነታቸውን የሚወጡ ታማኝ የፍትሕ ባለሙያዎች ያሉትን ያህል፣ ፍትሕን በገንዘብ የሚቸበችቡ፣ የተሰጣቸውን የሙያ ሥነ ምግባር ዘንግተው ዳኝነትና ፍትሕን በአገር ልጅነት ወይም …

ፍትሕን በብሔር ግንኙነት የሚሸጡና ለወሲብ ድርድር የሚያቀርቡ ሙያተኞች እንዳሉ ተነገረ Read more »

“ሦስተኛ ሲኖዶስ አቋቁመዋል” በሚል ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱን ለመክሠሥ ተዘጋጅተው ነበር “ቤተ ክርስቲያን ለ30 ዓመት በሰላም ኖራ እየተናወጠች ትገኛለች”/ሊቀ ካህናት መርዓዊ ተበጀ/ “መጥነው እንዲያወሩ ዕድል ቢሰጣቸው ተዋረዱ፤ የእግዚአብሔር ሥራ ነው”/ብፁዕነታቸው/   ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩትና ከደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡት፣ ሊቀ …

የዞን ዘጠኙ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በዋስ ተፈታ:: Zone 9 Bloggers in Ethiopia

#‎Ethiopia‬ ‪#‎Freezone9bloggers‬ የወያኔው ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ካልወንጀላቸው ካሰራቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ውስጥ በማጎሪያው ካምፕ አስሮት የነበረውን ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በ20.000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ወስኗል::ግፊት እና ጫና መቋቛም ያቃተው የወያኔው ስርኣት በርካታ ንጹሃንን አሁንም በየማጎሪያ ካምፕ …

የዞን ዘጠኙ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በዋስ ተፈታ:: Read more »

የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ መቃረብን ተከትሎ መስዋእት ከሆኑት  የዞን ዘጠኝ ጦማር አባላት ውስጥ የሽብር ክሱ ወደ ወንጀል ክስ ተቀይሮ ዛሬም በግፍ እስር በብቸኝነት የሚገኘው በፍቃዱ ዘ ኃይሉ አመጽ ለመቀስቀስ አስበህ ነው የጻፍከው የተባለውን ጽሁፍ እንዲከላከል ተወስኖበታል፡፡ ይህ የአመጽ መቀስቀስ የተባለው ጽሁፍ ራሱን ሳይሆን የበፍቃዱን የማእከላዊ ምርመራ ቃል ብቻ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ቃሉን ብቻ መሰረት በማድረግ ይከላከል በማለት የማእላዊ ምርመራን በማሰቃየት ውስጥ የተሰጠ ቃል ተቀብሎታል ማለት ነው ?

በአስገዳጅ ሁኔታ የተገኘ ማስረጃ እንደማስረጃ አይቆጠርም የሚለው የሕጎች ሁሉ የበላይ ነው የሚገባለው እና በፍቃዱ ከጓዶቹ ጋር ሆኖ ይከበር! ሲል የነበረው ሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 19.5 እንዲህ ይላል

‹‹የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ  በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችልየእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነትአይኖረውም፡፡››

ከወራት በፊት የጦማርያኑን እስር አንደኛ ዓመት አስመልክቶ የመብት ጥሰቶችን ዞን ዘጠኝ ጦማር ባስታወሰበት ወቅት በበፍቃዱ የደረሰበት የማሰቃየት ወንጀል እንዲህ ገልጾት ነበር ፡፡

‹‹ማዕከላዊ ምርመራ በቆየሁባቸው ቀናት ከእሁድ በስተቀር ጠዋት ከሰአትማታ እየተጠራሁ በዛቻ በአጸያፊ ስድብ ጭካኔ የተሞላበት ግርፊያ ጥፊና እርግጫ አንዲሁም ከአቅሜ በላይ የሆነ ስፓርት እየሰራሁቃሌን እንድሰጥ ተገድጃለሁ፡፡ የተያዝክበትን ድብቅ አጀንዳ ንገረን በማለት ራሴን እንድወነጅል ተገድጃለሁ፡፡

  1. መርማሪው በመጀመሪያ ቀን ምርመራ በጥፊ መማታት የጀመረ ሲሆን እያንዳንዱን ጥያቄ ከጠየቀኝ በኋላ በጥፊ ይመታኝ ነበር
  2. የዞን9 ዓላማ ጠይቆኝ ስነግረው ድብቁን አውጣ በማለት መሬት ላይ አንድቀመጥ እና ያደረኩትን ነጠላ ጫማ እንዳወልቅ አዞኝ በኮምፒውተር ገመድ እግሬን መግረፍ ጀመረ፡፡ በተጨማሪም በሆዴአንተኛ በማዘዝ እና እግሬን አጥፌ ከፍ አንዳደርገው በማድረግ ውስጥ እግሬን ገርፎኛል፣ግርፊያው ውስጥ እግሬን ሲለበልበኝ ነበር ፡፡
  3. ድብቁን አጀንዳህን ካልተናገርክ ነገ እዘለዝልሃለሁ በሚል አስፈራርቶኛል፡፡
  4. ድምጽ እንዲያፍን ሆኖ ወደተሰራው የስብሰባ አዳራሽ ተወስጄ በጥፌ እየደበደቡኝ የዞን9አላማ ተናገር ተብዬ ተደብድቤያለሁ፡፡ ስቃዬ ሲበዛብኝም የፈጠራ ታሪክ እንዳወራ ተገድጃለሁ፡፡ እኔ የምጽፈው ኢትዮጵያ ውስጥ አብዬት ለማስነሳት ነው ብዬ እንድፈርምም አስገድደውኛል››
  5. በምርመራ ወቅት እጄ በካቴና እነደታሰረ ለሰአታት ቁጭ ብድግ አንድል ተገድጃለሁ፡፡
  6. መርማሪው በአንድ ወቅት አራት የዞን9 አባላት ሆናችሁ ስለአላማው የተወያያችሁትን በቃል መስጫው ክስ ላይ ልጽፍ ነው ሲለኝ አንደዛ አይነት ውይይት ማድረጋችንን አላስታውስም ስለው እንዴት አታስታውስም ብሎ በጥፊ መማታት ጀመረ። በተደጋጋሚ ከመደብደብም በላይ እስክስታስታውስ እዚሁ ታድራታለህ በማለት ድብደባው በመቀጠሉ አስታውሳለሁ ብዬ ተገላገልኩ ፡፡ የሰጠሁት ቃል ላይም እንደፈለገው አድርጎ ጻፈው፡፡  እኔም በድብደባ ብዛት መርማሪው አለ ብሎየጻፈውን ፈርሜያለሁ ፡፡
  7. ዞን9 ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሌለው ከሆነ ይህንን ህዝብ አንዴት ነው ነጻ የምታወጡት በሚል ሲጠይቁኝ የነጻ አውጪነት ሚና የለንም ስላቸው ከወንበሬአንድነሳ አዘዙኝ፡ ከዚያም በቆምኩበት ግራ ብብቴን እና እጄን በአንድ እጁ አንዳልወድቅ ወጥሮ ይዞ በእግሩ ጭኔን በሃይል ደበደበኝ ፡፡ ከድብደባው በማስከተል ደግሞእግሬ መሃል እግሩን በማስገባት ወደግራ እና ወደቀኝ በመምታት ተዘርጥጬ እንድቆይ በማድረግ እጄን ወደላይ አድርጌ እግሬ ግራና ቀኝ ተዘርጥጦ ( በተ<a></a>ለምዶ ስፕሊት ሚባለው) በግራ እና ከቀኝ በመደብደብ እጄን ወደላይ አድርጌ እነድመረመር ተደርጌያለሁ፡፡ከዚህ ምርመራ በኋላ ለሁለት ቀን እያነከሰኩ ነበር፡፡››

በፍቃዱ ሃሳቡን በነጻነት በመግለጹ ብቻ እንደወንጀለኛ ተቆጥሮ እስካሁንለ542 ቀናት አግባብ ባልሆነ እስር ላይ ይገኛል፣ በዚህ ሁኔታ የተሰጠ ቃል ተቀባይነት ማግኘት ስለማይገባው በፍቃዱ ሃይሉእሮብ ከቤተሰቡ ጋር ሊቀላቀል ይገባል ፡፡

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የሚገኙትን የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ህገወጥ እስር አስመልክቶ የእንግሊዝ ባለስልጣናት ነገ በሚጀመረው የኢትዮጵያና የእንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ላይ ሊያነሱት እንደሚገባ አቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ሪፕሪቭ የተባለው ተቋም ጠይቋል። የንግድ እና የኢንቨስትመንት ስብሰባው ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው እንደመሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግራንት ሻፕስ ለኢትዮጵያ …

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-18 የእስር አመታት በግፍ ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 አሸናፊ ሆነ መመረጡን ድርጅቱ አስታውቋል። ለብዙዎች የዲሞክራሲ ሃይሎች የጽናት ምልክት ተደርጎ የሚቆጠረው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለፉትን ሶስት አመታት በእስር ቤት አሳልፏል። የእስክንድር ስራዎቹ ድንበር እና ባህል ተሻጋሪ ናቸው በማለት ያወደሰው …

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች “መሰረታችን ሕገ መንግስቱ ነው ተብሎ የወልቃይት ነዋሪዎች ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገና የሕዝቡን ስነ ልቦናዊ፣ ባሕላዊ ወግን ያላማከለና ያላጠቃለለ ክልላዊ አከላለል በማድረግ የወልቃይት ሕዝብ የማይፈልገውንና የማያምንበትን በመጫን በግድ ወደ ትግራይ እንድንካለል መደረጋችን በውስጣችን ያለውን ማንነታችንን በመጨፍለቅ እንድንቀበል እየተደረግን ነው ፣ዛሬ ስነ ልቦናችን የማይቀበለውን ሕወሃት በዘዴ ማንነታችንን ለማሸማቀቅ …

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ተከሶ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘው አቶ አበበ ካሴ እስር ቤት ውስጥ በማንነቱ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየደረሰብኝ ነው ሲል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታውን አሰምቷል፡፡ በእነ አበበ ካሴ የክስ መዝገብ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው አቶ ታጠቅ አስማረ የተከላካይ ጠበቃ ለማቅረብ ዛሬ ጥቅምት 9/2008 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ለልደታ ፍርድ …

ኢሳት ዜና (ጥቅምት በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አሜሪካን ግቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ሶስት ሺ የሚጠጉ የንግድ ተቋማት ቦታው ለልማት ይፈለጋል ተብሎ ንብረታቸው መታሸጉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ። የንግድ ተቋማት መታሸግን ተከትሎም የአካባቢው ነዋሪዎች መሰረታዊ የፍጆታ እቅርቦቶችን ለማግኘት ተቸግረው እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። ወፍጮ ቤቶች ሱቆችና ምግብ ቤቶች ከታሸጉበት የንግድ ተቋመት መካከል እንደሚገኙበት …

 

ሰሞኑን የቀድሞው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ የጻፉትንና ‹አብዮቱና ትዝታዬ› የተሰኘውን መጽሐፍ ሳነብብ ስለ አቡነ ቴዎፍሎስ አሟሟት የጻፉትን አገኘሁ፡፡ ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ እስካሁን ከጻፉት የቀድሞ ባለሥልጣናት በሁለት ነገር ተለይተውብኛል፡፡ የመጀመሪያው በቡድንና በጋራ ለሠሯቸው ስሕተቶች ይቅርታ መጠየቃቸው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሁሉም ወገኖች የተፈጠሩትን ያለፉትን ስሕተቶች ለማረም ያስችላል ያሉትን የጋራ መድረክ ሐሳብ ማቅረባቸው ነው፡፡
ምንም እንኳን በዘመነ ደርግ የተፈጠሩት ስሕተቶችና ጥፋቶች ደርግ ብቻውን ያደረጋቸው ባይሆኑም አንዱና ዋነኛው ተዋናይ ደርግ ነበርና ለተሠሩት ጥፋቶች ይቅርታ መጠየቃቸው ለሌሎች አካላትም አርአያነት ያለው ነው፡፡ ዋናው የደርጉ መሪ ያ ሁሉ ጥፋት ሲሠራ ‹እኔ አላውቅም ነበር›› ብለው በካዱበት ሁኔታ ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ የራሳቸውን ይቅርታ መጠየቃቸው ለሰማዩም ለምድሩም ጉዟቸው ምትክ አልባ ተግባር የሚሆን ነው፡፡ ክብር ይስጥልን፡፡

ያ ዘመን በተሻለ እንመራለን ብለው የተነሡ ፖለቲካዊ ኃይሎች እንደየዐቅማቸው ስሕተቶችን የሠሩበትና ጥፋቶችን ያጠፉበት ዘመን ነው፡፡ ሁሉንም ጥፋት ለደርግ በመስጠት እጅን መታጠብ አይቻልም፡፡ እርሳቸው እንዳሉትም የደርግን ባለ ሥልጣናት ብቻ ወደ ፍርድ ከማቅረብ ይልቅ የነበረው ጥፋት ከየአቅጣጫው የሚፈተሽበትና ሁሉም እንደ ጥፋቱ የሚከሰስበት ወይም የሚወቀስበት አለበለዚያም ደግሞ ይቅርታ የሚጠይቅበት መንገድ ቢመቻች መልካም ነበር፡፡ ችግሩንም በተቻለ መንገድ ሊፈታው የሚችለው ሁሉን አቀፍ የሆነው አካሄድ ነበር፡፡ አሁንም መሪ ተዋናዮቹ ከማለፋቸው በፊት ሁሉም እንደየድርሻው ኃላፊነቱን የሚወስድበትና ይቅርታ የሚጠይቅበት ሥርዓት ቢመቻች መልካም ነበር፡፡
ያ ካልሆነ ግን ሥርዓት በተቀየረና ሕጎች በተሻሻሉ ቁጥር ተከድነው የሚንተከተኩ ነገሮች እንደገና የመውጣታቸውና በመድረቅ ላይ ያሉ ቁስሎችን የማመርቀዝ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ፕላስተር የተለጠፈበት ቁስል ሁሉ አይድንምና፡፡
ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ በጻፉት መጽሐፍ ላይ ግን ጥያቄ እንዳነሣ ያደረገኝ አንድ ጉዳይ አለ፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን የተመለከተ፡፡ በመጽሐፉ ላይ የሚከተሉት ነገሮች ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ መገደል ጋር ተያይዘው ቀርበዋል፡፡
1.      1. ቤተ ክህነት መሬቷ ስለተነጠቀ አብዮቱን እንደተቃወመች

እግዚአብሔር የለም ብሎ የሚክደው ኮሚንስታዊ መንግሥት ሲመጣ ቤተ ክህነት ባትቃወም ነበር የሚገርመው፡፡ በተለይም የመሬት ለአራሹ አዋጅ የጭሰኛውን የዘመናት ጥያቄ የመለሰ ቢሆንም የፈጠራቸውም ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተመሠረተው በመሬት ላይ በመሆኑ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማትም የመተዳደሪያ መሬት ነበራቸው፡፡ ልክ ዛሬ የመተዳደሪያ ሕንጻና ገንዘብ እንዳላቸው ሁሉ፡፡ ነገሥታቱና መኳንንቱ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ስለነበሩም ለቤተ ክርስቲያን የመሬት ስጦታ ሰጥተዋል፡፡ የመሬት ላራሹ ዐዋጅ ሲታወጅ ግን የካህናትንና የገዳማውያን ሁኔታ ግምት ውስጥ ሊያስገባ አልቻለም፡፡ እንደ አንድ በመሬት የሚተዳደር ኢትዮጵያዊ ዜጋ ካህናቱና መነኮሳቱ ለአንድ ገበሬ የተመደበውን መሬት እንዲያገኙ እንኳን አልተደረገም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ስም መኳንንቱ ይዘውት የነበረው  መሬት ከግምት ውስጥ አልገባም፡፡ ቢያንስ በቶፍነት ሥርዓት ውስጥ የነበሩትን ካህናት እንኳን አብዮቱ ሊያያቸው አልፈቀደም፡፡ ሲሆን ቅርስና ባሕል ጠባቂ እንደመሆናቸው በተለይ ገዳማቱ ተጨማሪ የጋራ መሬት ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ የወቅቱ የደርግ ባለሥልጣናት ግን ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመጀመሪያው በጠላትነት ስለፈረጁ የድርሻዋን እንኳን ለመስጠት አልቻሉም፡፡ በምዕራብ ሸዋ የነበረው ደብረ ጽሙና ገዳም መሬቱን ሙሉ በሙሉ አጥቶ ሊፈርስ ሲል ኮሎኔል ደበላ ዴንሳ በሰጡት መመሪያ ጥቂት መሬት አግኝቶ መትረፉን አረጋውያኑ ዛሬም ከምስጋና ጋር ያስታውሱታል፡፡
ገዳማትና አድባራቱ ከልክ በላይ የያዟቸው መሬቶች ከነበሩ መጠኑን መቀነስና በቂ ነው የተባለውን ያህል መስጠት እንጂ ያላቸውን በሙሉ ነጥቆ በድህነት እንዲማቅቁ ማድረግ በምንም መልኩ ፍትሐዊ ሊሆን የማይችል ነው፡፡ ‹‹ኮሚኒዝም ማለት ድህነትን እኩል ማካፈል ነው – an even distribution of poverty›› የተባለው ነው የተፈጸመው፡፡ ፍትሐዊነት ያላገኘውን አካል እንዲያገኝ አድርጎ እኩል ማድረግ እንጂ ያገኘውን እንዲያጣ አድርጎ በድህነት ማስተካከል አይደለም፡፡ ይኼንን የወቅቱ ቤተ ክህነት ብትቃወመውና ከአብዮቱ ጋር ለመጓዝ ቢቸግራት ተገቢ ነው፡፡ ያውም በበቂ ሁኔታ አልሄደችበትም፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስ በ1967 ዓም ለዘመን መለወጫ ባስተላለፉት መልእክት ‹‹በጦር ኃይሉና በሕዝቡ የተጀመረው የተቀደሰ እንቅስቃሴ መልካም ውጤት እንዲያስገኝ ፈጣሪያችን ይርዳን›› ነበር ያሉት፡፡(ሐዲስ ሕይወት፣ ግንቦት 1፣ 1967 ዓም፣ ገጽ 17)፣ የዕድገት በኅብረት ዘመቻንም ፓትርያርኩ በበጎ ነበር ያዩት፤ ይህም ጥቅምት 3 ቀን 1967 ዓም በሰጡት መግለጫ ላይ ተመልክቷል፡፡(ገጽ 17)
ይኼ ጉዳይ በከተማ ቦታና ትርፍ ቤት ዐዋጁም ጊዜ ተከሥቷል፡፡ ብዙ ምእመናን ብጽዐት ገብተው እየሠሩ፣ ሲሞቱም እያወረሱ ለአድባራትና ገዳማት የሰጧቸው ቤቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ ቤቶች በሀገር ቤት ብቻ ሳይሆን በኢየሩሳሌም ከተማ ሳይቀር ይገኙ ነበር፡፡ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት ዐዋጅ ሲታወጅ ግን ለአንድ ሰው የሚኖርበት የ500 ካሬ ሜትር ቦታና አንድ ቤት ሲፈቅድ ለአድባራትና ገዳማት ግን ምን አልተፈቀደም፡፡ በሙሉ ነው የተወረሰው፡፡ ራሳቸው ፍሥሐ ደስታ እንደመሰከሩት ዐዋጁ ጠላ ሽጣ፣ ማገዶ ቸርችራ ድኻዋ የሠራቺውን፣ ኮርያና ኮንጎ ዘምተው ባገኙት የደም ዋጋ መለዮ ለባሾች የገነቡትን ሁሉ ሀብት ከተትረፈረፋቸው ጋር እኩል በመውረሱ ‹‹ብዙዎች አብዮቱን የደገፉ ጭቁኖች ከበዝባዦች ጋር አብዮቱን ያጥላሉ ጀመር››(ገጽ 160)፡፡
ከነዚህ በዐዋጁ ከተጎዱት መካከል አብያተ ክርስቲያናቱ አንዱ ናቸው፡፡ ቢያንስ የተወሰነውን ቤት እንዲያገኙ መደረግ ነበረባቸው፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱን ደርግ የተመለከተበት መነጽር ችግሩን እንዳያይ የሚጋርደው ነበር፡፡ ለዚህም ነው ቤተ ክህነት ለውጡን በበጎ ልታየው ያልቻለቺው፡፡ በርግጥ መንግሥት 4 ሚሊዮን ብር ምትክ ካሣ ሰጥቻለሁ ብሎ ነበር፡፡ በጎላ ወስዶ በጭልፋ መመለስ ማለት እንዲህ ነው፡፡ ያውም አራት ሚሊዮን ብሩ ሳይጨመር ሳይቀነስ በደርግ ዘመን ሁሉ የኖረ ነው፡፡
አቡነ ቴዎፍሎስ በ60ው ባለ ሥልጣናት የግፍ ግድያና በንጉሠ ነገሥቱ ሞት በእጅጉ አዝነው ነበር፡፡ የንጉሠ ነገሥቱን አስከሬን ወስደው በክብር ለመቅበር በነሐሴ 1967 ዓም ደርግን ጠይቀው አልተፈቀደላቸውም፡፡ ከዚህም አልፎ ለንጉሠ ነገሥቱ በይፋ የፍትሐት ጸሎት እንዳያደርጉም ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው(ፍሥሐ ደስታና ሌሎችም ቢዘሉትም)፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስ ከዚህ በኋላ ነው ለውጡን በሥጋት ማየት የጀመሩት፡፡
2     2. አቡነ ቴዎፍሎስ የራሳቸውን ወገኖች በመሾም በአብዮቱ ላይ ውስጥ ውስጡን ሤራ እንደሠሩ
አቡነ ቴዎፍሎስ የራሳቸውን ሰዎች ሾሙ ያሰኛቸው ሦስት አባቶችን በጵጵስና መሾማቸው ነው፡፡ ደርግ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ተለያይተዋል፤ እንዱ በሌላው ጣልቃ አይገባም ብሎ ዐወጀ፡፡ ፓትርያርኩ ይህንን ተከትለው ደርግን ሳይጠይቁ ሦስት አባቶችን ሾሙ፡፡ አቡነ ጳውሎስን፣ አቡነ ባስልዮስና አቡነ ጴጥሮስን፡፡ ሦስቱም አባቶች በነበራቸው ዕውቀት የተሾሙ እንጂ ለአቡነ ቴዎፍሎስ በነበራቸው ዝምድና አልነበረም፡፡ በሀገር ልጅነትም ሆነ በዝምድና አይገናኟቸውም ነበር፡፡ ደርግን ተደፈርኩ አስብሎ ፓትርያርኩን እንዲያሥር ያደረገው ይኼ የፓትርያርኩ ሳያስፈቅዱ መሾማቸው ነው፡፡ ያሠረውም ፓትርያርኩንና አዲስ የተሾሙትን ኤጲስ ቆጶሳትን ነው፡፡  
3  3. አቡነ ቴዎፍሎስን በተመለከተ የቤተ ክህነት ሰዎች ለመንግሥት አቤቱታ አቅርበው ነበረ ፡፡
  በሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ መጽሐፍ ላይ የቤተ ክህነት ሰዎች አቡነ ቴዎፍሎስን በተመለከተ ያቀረቧቸው ክሶችና አቀራረቡን ገልጠውታል፡፡ የመጀመሪያው ክስ አቡነ ቴዎፍሎስ አባ መልእክቱ ተብለው መነኩሴ እያሉ በአቡነ ጴጥሮስ ግድያ ላይ እጃቸው አለበት የሚለው ነው፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስ ወደ አዲስ አበባ ከቤተሰቦቻቸው ጠፍተው የመጡት በ1920 ዓም ነው፡፡ የሄዱትም በአዲስ ዓለም ማርያም ወደነበሩት ሐዲስ ተክሌ ዘንድ ነው፡፡ ሐዲስ ተክሌ በቀለም አያያዛቸው ስለወደዷቸው አቀረቧቸው፡፡ አባ መልእክቱ ከአዲስ ዓለም ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው በ1930 መነኮሱ፡፡ ጣልያን ሀገሪቱን ሲወር እርሳቸው የመምህራቸው የሐዲስ ተክሌ ደቀ መዝሙር ሆነው በአዲስ አበባ ነበሩ፡፡
በወቅቱ የነበሩት አባቶች የጣልያን ወረራን በተመለከተ ሁለት ዓይነት ሐሳብ ነበራቸው፡፡ እንደ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል ያሉት ከዐርበኞች ጋር ሆነው ጣልያንን ለመፋለምና ሀገሪቱን ነጻ ለማውጣት ወሰኑ፡፡ ሌሎች አባቶች ደግሞ ሕዝቡ ያለ እረኛ መቅረት የለበትም የሚለውን ሐሳብ ደግፈው የሊቃውንት ጉባኤ በማቋቋም ወደ ሀገራቸው የሄዱትን  ግብጻዊውን አቡነ ቄርሎስን ተክተው መሥራት ጀመሩ፡፡
አቡነ ቴዎፍሎስ የአቡነ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር እንደመሆናቸው መምህራቸውን ተከትለው ከማገልገል ያለፈ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ በተፈጸመው ግፍ እጃቸው ነበረበት የሚል ምንም ዓይነት ማስረጃ እስካሁን አልቀረበም፡፡ ደግሞም በዚያ ጊዜ በነበራቸው ሁኔታ ይህንን ለመፈጸም የሚበቃ ሥልጣን አልነበራቸውም፡፡ የጠሉትን ሰይጣን፣ የወደዱትን መልአክ ማለት ልማድ ሆኖ ጠላቶቻቸው ለውጡን ተጠቅመው ለጥብስ አቀረቧቸው እንጂ ማስረጃ ሊያቀርቡበት የሚችሉበት ነገር አልነበረም፡፡ ደርግም ማስረጃ አልጠየቀም፤ ለማጣራትም አልሞከረም፡፡ ሌ/ ኮሎኔል ፍሥሐም አገላለጣቸው ‹ቤተ ክህነቱ ስለከሰሳቸው አሠርናቸው እንጂ ነገሩ ከኛ አልመጣም› ዓይነት ነው፡፡ የአቡነ ቴዎፍሎስን ሕይወት የቀጠፈው ግን ክሱ ሳይሆን ‹ከፍርድ በፊት ወንጀለኛ የሚያደርገው› የደርግ አሠራር ነበር፡፡ በዚያ ላይም ሳያስፈቅዱኝ ሾሙ ብሎ ደርግ ምክንያት ፍለጋ ላይ ነበር፡፡
ሁለተኛው ክስ ‹በቤተ ክህነት ሤራና አሻጥር ይሠራሉ› የሚለው ነው፡፡ ምን ዓይነት ሤራና አሻጥር እንደሆነ አልተገለጠም፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ በመጣ ቁጥር ሰውን የመክሰሻ ቀላሉ መንገድ ‹ለውጡን ይቃወማል፣ ያለፈውን ሥርዓት ይደግፋል፣ ውስጥ ውስጡን አድማ ይመታል› የሚሉት አቤቱታዎች ናቸው፡፡ ምግቡን ለበዪው እንዲስማማ አድርጎ ማቅረብ፡፡ ይህንን እንድገምት ያደረገኝ ክሱን ያቀረቡትን አካላት በተመለከተ ኮሎኔሉ የሰጡን መረጃ ነው፡፡ ‹ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ገዳማት ፈርመውበት ነበር›(ገጽ 199) ይላል፡፡
እጅግ አስገራሚ መረጃ ነው፡፡ ሳይበጠር ይከካ፣ ሳይለቀም ይፈጭ እንደነበር የሚያሳይ፡፡ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በ1972 ዓም ባካሄደው የሰበካ ጉባኤ ቆጠራ የኢትዮጵያ ገዳማት ቁጥር 1000 እንደነበረ ያመለክታል፡፡(ከ1966-1972 ባለው ጊዜ እንኳን አዲስ የሚቋቋምበት ያሉትም በፕሮፓጋንዳውና በለውጡ እየተንገዳገዱ ነበር) ያ ዘመን እንዳሁኑ መንገድ ያልተስፋፋበት፣ ሞባይል ስልክ የሌለበት ጊዜ ነው፡፡ ወቅቱም የግርግር በመሆኑ ገዳማውያን ከበኣታቸው እንዲወጡ የሚያበረታታ አይደለም፡፡ በዚህ ላይ ራሳቸው ፍሥሐ ደስታ እንደነገሩን ገዳማቱ ሁሉ መሬታቸውን ተወርሰዋል፡፡ እንዴት ሆነው ነው በአብዮቱ ቅር የተሰኙ 900 ገዳማት ተገናኝተው በአቡነ ቴዎፍሎስ ላይ ሊፈራረሙ የሚችሉት? በየቦታቸው ሆነው ፈረሙ ቢባል እንኳን ማነው በዚያ ዘመን ከዋልድባ እስከ ማንዳባ፣ ከደብረ ዳሞ እስከ ደብረ ወገግ፣ ከማኅበረ ሥላሴ እስከ ዝቋላ፣ ከደብረ ቢዘን እስከ ደብረ ሊባኖስ ተዘዋውሮ ገዳማቱን ሊያስፈርም የሚችለው(ያውም ያኔ የኤርትራንም ገዳማት ይጨምራል)፡፡ ገዳማቱ ያሉበት አስቸጋሪ አካባቢ፣ የገዳማቱ ብዛትና የወቅቱ ሁኔታ ተደምሮ 10 በመቶ ገዳማት እንኳን ሊፈርሙ አይችሉም፡፡ አብያተ ክርስቲያናቱ ናቸው የፈረሙት እንዳንል እንኳን እነርሱም ቁጥራቸው በ1972 ዓም ከ25 ሺ በላይ ነበሩ፡፡ ፈጽሞ ሊሆን የማይችል ነው፡፡
የአቡነ ቴዎፍሎስ ሞትና አሟማት አሁንም ያልተፈታ ጉዳይ ነው፡፡ በሞታቸውና አሟሟታቸው ሦስት አካላት የነበራቸው ሚና አሁንም በሚገባ መፈተሽ አለበት፡፡ ቤት ክህነት(ከጳጳሳት ጀምሮ)፣ ደርግና ሌሎች አካላት(ለምሳሌ አስያዛቸው የሚባለው ሰው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጎፋ አካባቢ ነበረ)፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የእኒህን አባት ሁኔታ በሚገባ ማጣራት ይኖርባታል፡፡ አንድም ዋና ተዋንያን የነበሩት የቤተ ክህነትና የቤተ መንግሥት ሰዎች መረጃውን ይዘውት ጨርሰው ከማለፋቸው በፊት፤ ሁለት ቤተ ክህነቱንም ሆነ ደርግን የሚያስወቅስ ያልተሰማ መረጃ ነገ ከመውጣቱና ማጣፊያው ከማጠሩ በፊት፡፡ ቤተ ክህነት አንድ አጣሪ አካል አቋቁማ ታሪኩ የተጣራ እንዲሆን ማድረግ አለባት፡፡ የአብዮቱን ዘመን ታሪክ የምትነግሩን አካላትም መጻፋችሁ የሚያስመሰግናችሁ ቢሆንም የምትሰጡን መረጃ ግን እውነትና ሊታመን የሚችል ቢሆን በታሪክ ውስጥ የሚኖራችሁን ሥፍራ ምቾት የሚሰጠው ይሆናል፡፡
የአቡነ ቴዎፍሎስን አሟሟት በተመለከተ ሻለቃ ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስም ሆኑ ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ በሁለተኛው እትሞቻቸው የሚያብራሩት ነገር ሊኖር ይገባል፡፡ አዲስ እየጻፋችሁ ያላችሁም አስቡበት፡፡

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በቅርቡ በክብር ወደ ቦታው ይመለሳል ተባለ:: በአዲስ አበባ የቀላል ባቡር መስመር ዝርጋታ ሳቢያ ከቦታው የተነሳው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በቅርቡ በክብር ወደ ቦታው እንደሚመለስ በቅርስ ጥበቃና ጥናት ባለሥልጣን ከፍተኛ የቅርስ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ኃይሉ ዘለቀ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ እስካሁን …

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በቅርቡ በክብር ወደ ቦታው ይመለሳል ተባለ :: Read more »

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፡- ቤተ ክርስቲያናችንን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት በቊጥር እጅግ የላቀ የውሉደ ክህነት ብዝኅነት ያላት ስትኾን ስብከተ ወንጌልን ለውሉደ ሰብእ በማዳረስ ረገድ ያለን ውጤት ግን አናሳ ነው ማለት ይቻላል ባሕርን አቋርጦ፣ ድንበርን ተሻግሮ እስከ ጽንፈ ምድር ተጉዞ፣ አስተምሮና ያላመነውን አሳምኖ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ማድረጉ ይቅርና በሀገር ውስጥ ያሉትን ወገኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሰባስቦ ምእመናንን ማብዛት …

በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ክስ የተመሰረተበት ከጋዜጠኝት ስራው ጋር በተያያዘ ነው፡፡ የቀድሞ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና አዘጋጅ የነበረው ሰለሞን ከበደ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ከቤቱ ወደ ስራ ቦታው ሲሄድ ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ በማእከላዊ ለአራት ወራት ያህል …

ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ የተከሰሰው በጋዜጠኝነት ስራው ነው! በማእከላዊ ቆይታው አሰቃቂ ጊዜ አሳልፏል! Read more »

ብሔራዊ ጭቆናን አንቀበልም! መብቶቻችን ተሟልተው እስኪከበሩ ሕዝባዊ ትግላችን ይቀጥላል! ድምፃችን ይሰማ #‎EthioMuslims‬ ‪#‎EthioMuslimPeacefulStruggle‬ ‪#‎Fidake‬  ማክሰኞ ጥቅምት 9/2008 የኢትዮጵያ ሙስሊም ብዙ የሀይማኖት መብት ጥያቄዎች ቢኖሩትም የትግላችን መነሻዎች ግን ሶስት ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ ሆኖም ቀደም ሲሉ የነበሩት በሀይማኖታችን ላይ የሚደርሱ ትንኮሳዎች የመንግስት ፖሊሲ …

ብሔራዊ ጭቆናን አንቀበልም! መብቶቻችን ተሟልተው እስኪከበሩ ሕዝባዊ ትግላችን ይቀጥላል! (ድምፃችን ይሰማ) Read more »

ጠንካራ እና ጽኑ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የሰብአዊነት የመጀመሪያ ደረጃ ሽልማት አሸናፊ ሆነ:: ‪ ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሽልማቱ የሚሰጠው በ36ኛው የአለም ጸሃፊዎች ፌስቲቫል (IFOA 36)ላይ ሲሆን ሽልማቱ 5000 ዶላር ዋጋ ያለውና የሚሰጠውም በጸሃፊነታቸው ታላቅ አስታውጾ እና ሕዝባዊ አመኔታ …

ጠንካራ እና ጽኑ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የሰብአዊነት የመጀመሪያ ደረጃ ሽልማት አሸናፊ ሆነ:: ‪ Read more »

የዮሃንስ ቡድን የት ሊደርስ ይችላል!? Written by  ግሩም ሠይፉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ፈታኝ ሂደት ውስጥ ይገኛል፡፡ በዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለሚመሩት ዋልያዎች ዓመቱ በሴካፋ፤ በቻን፤ በአፍሪካ ዋንጫና በዓለም ዋንጫ ማጣርያና ዋና ውድድር ጨዋታዎች የተጨናነቀ ነው፡፡ ከ2 ዓመት …

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ፈታኝ ሂደት ውስጥ ይገኛል፡፡ Read more »

በትግራይ ክልል ለተከሰተዉ የድርቅ ኣደጋ ለመከላከል እየገባ ባለዉ የእርዳታ ስንዴ ለግል የዱቄት ፋብሪካ እየተሸጠ እንደሆነ ተሰማ። በዝናብ እጥረት ሳብያ በተከሰተዉ የድርቅ ኣደጋ በተለያዩ የክልሉ ኣከባቢዎች የረሃብ ኣደጋን እያሰከተለ ቢሆንም ለጋሽ ድርጅቶች ኣደጋዉ ለመከላከል እያስገባ ባለዉ የእርዳታ ስንዴ ለጭረት ከ250-300 ብር …

በትግራይ ክልል ለተከሰተዉ የድርቅ ኣደጋ ለመከላከል እየገባ ባለዉ የእርዳታ ስንዴ ለግል የዱቄት ፋብሪካ እየተሸጠ እንደሆነ ተሰማ። Read more »

አስገራሚ ቁጥሮች… ስህተት ይሆኑ እንዴ? – ካልተጠነቀቅን አፋፍ ላይ ነው ያለነው!! ዮሃንስ ሰ. ===== ቁጥሮቹ አስገራሚ ናቸው – ማለቴ ለኢትዮጵያ። በ1997 ዓ.ም፣ (ከአስር ዓመት በፊት መሆኑ ነው…) የአገሪቱ ገበሬዎች ጠቅላላ የእህል ምርት 119 ሚሊዮን ኩንታል ነበር። አምና ደግሞ፣ 236 ሚሊዮን …

አስገራሚ ቁጥሮች… ስህተት ይሆኑ እንዴ? – ካልተጠነቀቅን አፋፍ ላይ ነው ያለነው!! ዮሃንስ ሰ. Read more »

ኤሪትራዊው ፍልሰተኛ የሞተው በስህተት በተተኮሰበት ጥይት ሲሆን፤ የተኩሱ ዒላማ ግን፣ አንድ የእሥራኤል ወታደር በመግደል ሌሎች 10 ሰዎችን አቁስሎ በኦቶቡስ ያመለጠ ተጠርጣሪን ለመግደል ያነጣጠረ እንደነበር ታውቋል።

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን የተመሰረተበትን 35ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ በማድረግ የተለያዩ ጋዜጠኞችንና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ያካተተ ጉዞ ላይ ፣ የትግል ተሞክሮ እንዲያካፍሉ የተጋበዙት የቀድሞ ታጋዮች በርካታ ጓዶቻቸው መጠለያ በማጣት በየከተማው በላስቲክ ቤት መንገድ ላይ እንደሚኖሩ ለጎብኝዎች ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ህዝብ እንደኖረው ለመኖር ዕድሉን …

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሱ የተገደለው በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ተጣልቶ ነው። ፖሊሶች አንድ የግሮሰሪ ሰራተኛን ሲደበድቡ ፣ ወጣቶች በብስጭት በፌደራል ፖሊሱ ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በከተማዋ ከፍተኛ ግርግር መኖሩን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ገዳዮችን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ነው። የከተማው ወጣቶች የፌደራል ፖሊስ አባላት ከፍተኛ የሆነ ጫና …

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከታላላቆቹ የአለም የመገናኛ ብዙሃን መካከል ዘ ኒውዮርክ ታይምስና ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ድርቅ የዜና ሽፋን በመስጠት ላይ ሲሆን፣ ዘ ኒዮርክ ታይምስ ባወጣው ዘገባ ድርቁ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል። “ያሲን ሙሃመድ ከአነስተኛ የእርሻ ማሳው ላይ እየወሰደ ጫት ይቅማል፣ ለምን ተብሎ ሲጠየቅ ፣ ጫት ረሃብን ያስታግሳል “የሚል …