አስታማሚ ባለማግኘታቸው ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል –115 ዶላር ብቻ ሲከፈላቸው መቆየታቸውንም ይናገራሉ (በዛብህና በየነ እውነተኛ ስማቸው ለዚህ ጽሁፍ ሲባል ተለውጧል) ሁለቱም በሐያዎቹ አጋማሽ የዕድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ፤አገራቸውን በወታደርነት ለማገልገል ቅጥር የፈጸሙት ከዛሬ ስድስትና አራት አመታት በፊት ነው፡፡የትውልድ አካባቢያቸው የነበሩትን ዲላና ሆሳህናን …

በሶማሊያ የተጎዱ ኢትዮጵያዊያን የሰላም አስከባሪዎች በኬንያ ሆስፒታል ተረስተዋል Read more »

ኢትዮጵያ አምና ወደዚያው ከላከችው ስጋ 58.8 ሚ ዶላር አግኝታለች
     የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ የስጋ ምርት ወደ ግዛቷ እንዳይገባ ከአንድ ሳምንት በፊት ጥላው የነበረችውን ማዕቀብ ማንሳቷን ተርኪሽ ዊክሊ ድረገጽ ትናንት ዘገበ፡፡
ከሳምንት በፊት ከኢትዮጵያ ሰባት ስጋ ላኪ ኩባንያዎች ወደ አገሪቱ ከገባው 36 ቶን የበግ ስጋ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ አገሪቱ የኢትዮጵያ የስጋ ምርት ወደ ግዛቷ እንዳይገባ ገደብ ጥላ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፣ ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ መንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩን መፍታት መቻሉን ገልጧል፡፡
ይህን ተከትሎም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ የስጋ ምርት ወደ ግዛቷ እንዳይገባ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳቷንና አገሪቱ ያሳለፈችው ውሳኔ በዘርፉ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንን እንዳስደሰተ ዘገባው አስረድቷል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያን የስጋ ምርት በስፋት በመግዛት ቀዳሚዋ አገር እንደሆነችና ኢትዮጵያ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከምትልከው የምግብ ኤክስፖርት ምርት በአመት በአማካይ 30 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታገኝም ገልጧል፡፡
ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከላከችው 11.692 ቶን የስጋ ምርት 58.8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷንም ዘገባው አክሎ አስታውሷል፡፡

የካናዳዋ ቶሮንቶ ከተማ የመጪውን አመት 2016 በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእግርኳስ ፌስትቫል እንደምታዘጋጅ ESFNA አስታወቀ::ከአስረአመስት አመት በኋላ የቶሮንቶ ከተማ ይህን ፌስትቫል ስታዘጋጅ የመጀመሪያዋ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ማህበር ደስታውን ገልጾ በቶሮንቶ ኢትዮጵያውን ኩራት እንደሚሰማው ተናግሯል:: ማንኛውንም የጉዞ እና የፕሮግራሙን …

ቶሮንቶ የመጪው አመት 2016 በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ፌስትቫል ታስተናግዳለች:: Read more »

ጉዳዩን ለአለም የሚያሳውቅ ገለልተኛ አካል እንዲቋቋም ጠይቋል
                                
    ሠማያዊ ፓርቲ፤ በኢትዮጵያ የተከሰተው “ረሃብ”፤ ከገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት የመነጨ ነው በማለት ችግሩን ለአለም የሚያሳውቅ ገለልተኛ አካል እንዲቋቋምና አለማቀፉ ህብረተሰብ እርዳታውን እንዲለግስ ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ከትናንት በስቲያ “ረሃቡ የገዥው ፓርቲ የፖሊሲ ውድቀት ነው!” በሚል ርዕስ በሠጠው መግለጫ፤ ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ አለማቀፉ ማህበረሰብ ለዜጐች እርዳታ እንዳያቀርብ መንግስት ጉዳዩን ሲሸፋፍን ቆይቷል ሲል ተችቷል፡፡
“መንግስት የኋላ ኋላ ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት ችግሩ እንደተከሰተ ቢገልጽም ዜጐች ተገቢውን እርዳታ በሚያገኙበት መልኩ እርምጃ እየተወሰደ አይደለም” ብሏል ፓርቲው በመግለጫው፡፡ የተከሰተው ችግር የፖሊሲ ውድቀትን ያመላክታል ያለው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ገዥው ፓርቲ ቆሜለታለሁ የሚለውን አርሶ አደርና አርብቶ አደር ህይወት ለማሻሻል የረባ ስራ እንዳልሠራ ማረጋገጫ ነው ብሏል፡፡ “ግብርናው ኢኮኖሚውን ይመራል የሚለው በተግባር አልታየም፤ ምክንያቱም ሚሊዮኖች በየአመቱ ለ“ረሃብ” ችግር መጋለጣቸውን ቀጥለዋል” ሲል ገልጿል ፓርቲው፡፡
ለተከሰተው ሀገራዊ ችግር መንግስት አፋጣኝ እርምጃዎችን እንዲወስድ ያሳሰበው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ስለ ችግሩ ለኢትዮጵያውያንና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚያስረዳ ገለልተኛ አካል ተቋቁሞ፤ በችግሩ ለተጠቁ ዜጐች መፍትሔ እንዲፈለግ ጠይቋል፡፡
የምግብ እጥረቱ (ረሃቡ) ከተፈጠረባቸው አካባቢዎች መረጃ በማሰባሰብና በማጣራት ለህዝብ በየጊዜው እንደሚያሳውቅ የገለፀው ፓርቲው፤ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያውያንና የአለም ህብረተሰብ ከተጐጂዎች ጐን እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
መንግስት በበኩሉ፤ ችግሩ የተፈጠረው በአለማቀፍ ደረጃ ከተከሰተው የአየር ፀባይ ለውጥ (ኤሊኖ) ጋር ተያይዞ መሆኑን በመግለፅ፣ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ዝናብ ባለመዝነቡ የምግብ እጥረት ቢያጋጥምም “ረሃብ” አለመከሰቱን በተደጋጋሚ አስታውቋል፡፡

     በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ በሃጂ ስነስርአት ወቅት በተፈጠረ መጨናነቅ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 47 መድረሱን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገልጿል፡፡
ባለፈው መስከረም 13 ቀን 2008 በሳዑዲ አረቢያ ሚና አካባቢ በደረሰ አደጋ ከ1ሺህ በላይ የተለያዩ ሀገር የሃይማኖታዊ ስነ ስርአቱ ተሳታፊዎች ህይወታቸውን ባጡበት ወቅት ኢትዮጵያውያን ላይ አደጋ ስለመድረሱ ወዲያው ማወቅ ያልተቻለ ሲሆን ከቀናት በኋላ 2 ኢትዮጵያን ህይወታቸው ማለፉ ተዘግቦ እንደነበርና ኋላም የሟቾች ቁጥር ወደ 31 ማደጉ ይታወቃል፡፡ ከትናንት በስቲያ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቁጥሩ 47 መድረሱንና ተጐድተው ሆስፒታል ገብተው ከነበሩት 26 ኢትዮጵያውያን 24 ተሽሏቸው ከሆስፒታል ሲወጡ፣ 2ቱ ተኝተው ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ታውቋል፡፡
ለሃጅ ስነስርአት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው የነበሩ ከ1ሺህ 100 በላይ አማኞች መመለሳቸውንም ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡ በዘንድሮ የሃጂ ስነስርአት ላይ 10ሺ ኢትዮጵያውያን መሣተፋቸውም ታውቋል፡፡

የእስካሁኑ ሳያንስ አሁንም ይጨፈርብን? – (ከኢትዮጵያ ልጅ) የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) የኤርትራ ቴሌቪዥን ሆነ እንዴ? ያስባለኝን ጥያቄ እንዳነሳ ያደረገኝ በነሐሴ መጨረሻና በጳጉሜን ወራት በተለያዩ ቀናት ደጋግሞ የኤርትራ ስደተኞች በስደት በሰፈሩበት ቦታ ላይ የነፃነት ትግል የጀመሩበትን 54ኛ ዓመት በዓል በኢትዮጵያ …

ወያኔ የሻዕቢያ ጉዳይ ፈጻሚና ተላላኪ ነው – ተጠያቂነት ይኑር በአገር አይቀለድ፡፡ – ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ቁስለት ነው Read more »

ጌታዬ! ላንተ ያለኝ ፍቅር ላንተ ያለኝ ክብር ምን ያህል እንደሆን… ተወው አልነግርህም ብትሆንም ኩራቴ ምስጢር አርጎት ይቆይ ልጉም አንደበቴ። ስላንተ ‘ሚያወራ የሚናገር አፌ ሰውን ካበሳጨ የፍቅሬ ጥግጋት በቃላት ተሰፍሮ በክፉ ካሳጨ ይቅር አልነግርህም…… እስካልቆረቆረኝ የተፈናጠጥኩት የፍቅርህ ኮርቻ ዝም………… ብዬ ልውደድህ …

*** ምስጢር ነው!*** Tigist Alemneh Read more »

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ከአገር አቀፍ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡

ባለፈው ዓርብና ቅዳሜ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክስ ኮሚሽን አዳራሽ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው 22 የፖለቲካ ፓርቲዎች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) እና ሰማያዊ ፓርቲ ‘በዕድገትና በልማት አጀንዳዎች ላይ ከመወያየታችን በፊት፣ በሌሎች አጠቃላይ ፖለቲካዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት መቅደም አለበት’ በማለት በስብሰባው እንደማይካፈሉ በማስታወቃቸው በአዳራሹ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ ባለፈው ዓርብ  በመጀመሪያው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ላይ በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው አደም አማካይነት ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን፣ በዕቅዱ አጠቃላይ አፈጻጸሞችና ጉድለቶች ላይ ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡    

 

በዚህ አውድ ለማቅረብ የተገደድኩበትን ዘግናኝ ታሪክ፣ ወደር በሌለው አስከፊነቱ የተነሳ ለንባብ ባላበቃው በወደድኩ ነበር፡፡ ግና! ይህ መንግስታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ እያደረገ በመሆኑ ህዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል …

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ (ከዝዋይ እስር ቤት) Read more »

  በአሥር ደረጃዎች ተከፋፍሎ ለገበያ ሲቀርብ የነበረው የኢትዮጵያ ቡና ምርት ወደ ስድስት ደረጃዎች ዝቅ ብሎ ለግብይት እንዲበቃ ተወሰነ፡፡

 ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ እስካሁን የአገሪቱ የቡና ምርት በአሥር ደረጃዎች ተከፋፍሎ እንደየደረጃው  ዋጋ እየተሰጠው ሲሸጥ ቆይቷል፡፡

ይህ የደረጃ አሰጣጥ ግን ለአሠራርም ሆነ የአገሪቱ የቡና ምርት ሊያገኝ የሚገባውን ዋጋ እንዳያገኝ በማድረጉ በአዲስ አሠራር እንዲለወጥ ተደርጓል፡፡ በቡና ደረጃዎች አሰጣጥ ላይ የተደረገ ጥናት አዋጭ የሚሆነው አሥር የነበሩትን የቡና ደረጃዎች ዝቅ ማድረግ እንደሚገባ ነው፡፡ 

በዚህ መሠረት የተደረገውን ጥናት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣንና ንግድ ሚኒስቴር በመቀበላቸው፣ የ2008 ዓ.ም. የቡና ምርት ከሚገባበት ከታኅሳስ ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ቡና በስድስት ደረጃዎች ተከፋፍሎ ለገበያ እንዲቀርብ መወሰኑን፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ አረጋግጠዋል፡፡

እንደ አቶ ኤርሚያስ ገለጻ፣ በዚህ ውሳኔ መሠረት ለምሳሌ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተብሎ ደረጃ ይሰጣቸው የነበሩትን በአንድ ደረጃ ማጠቃለል ያስችላል፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ የሚሰጣቸው የቡና ዓይነቶች ዋጋ ልዩነት ተቀራራቢ በመሆኑ በአንድ ዋጋ እንዲሸጡ ያስችላል፡፡ የተሻለ ዋጋም ያስገኛል፡፡ በመጋዘን አሠራርም አሥር ቦታዎች ከፋፍሎ ከማስቀመጥ በስድስት ቦታዎች ማስቀመጥ ጊዜና ጉልበትን ይቆጥባል ብለዋል፡፡

በአዲሱ የምርት ዘመን ከታኅሳስ 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ አሠራር፣ በቡና አቅራቢዎችም መደገፉን የምርት ገበያው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከአንድ እስከ አምስት ደረጃ የተሰጣቸው ለኤክስፖርት የሚቀርቡ ሲሆን፣ ደረጃ ስድስት የተሰጠው ቡና ደግሞ ለአገር ውስጥ ገበያ የሚውል ነው፡፡

 

 ኤርትራ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ተጠቃሚ በመሆን አለምን ትመራለች
   በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነው ከአጠቃላዩ ህዝብ 1.7 በመቶ የሚሆነው ብቻ ነው መባሉን የአሜሪካው የቢዝነስ መጽሄት ፎርቹን ዘገበ፡፡ኢንተርኔት ላይቭ ስታትስ የተባለው አለማቀፍ ተቋም ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ እጅግ ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቦት ካላቸው አስር የአለማችን አገራት መካከል ስምንቱ በአፍሪካ አህጉር እንደሚገኙና ኢትዮጵያም አንዷ እንደሆነች በጥናት ተረጋግጧል፡፡በኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቦት ዝቅተኛነት ከአለማችን ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ኤርትራ መሆኗን የጠቆመው ዘገባው፣ ከአገሪቱ ህዝብ የአገልግሎት ተጠቃሚ የሆነው 0.91 በመቶ ብቻ መሆኑን ገልጧል፡፡ከአውስትራሊያ በስተሰሜን የምትገኘው ቲሞር ሌሴቴ ደሴት በ1 በመቶ፣ ማይንማር በ1.16 በመቶ፣ ብሩንዲ በ1.39 በመቶ እንዲሁም ሴራሊዮን በ1.49 በመቶ በኢንተርኔት አቅርቦት ዝቅተኛነት እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል ተብሏል፡፡  ሶማሊያ በ1.51 በመቶ፣ ኒጀር በ1.61 በመቶ፣ ኢትዮጵያና ጊኒ በ1.7 በመቶ እንዲሁም ኮንጎ በ1.92 በመቶ እንደሚከተሉም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

ግርማዊ እቴጌ መነን መጋቢት 25 ቀን 1883 ዓም በወሎ ጠ/ግዛት በአምባሰል አውራጃ ልዩ ስሙ ዕጎ ከተባለው ቀበሌ ከጃንጥራር አስፋውና ከወ/ሮ ስሀን ሚካኤል ተወለዱ። እቴጌ መነን በልጅነት ዘመናቸው በእናት በእባታው ቤት መምህር ተቀጥሮላቸው አማርኛ ማንበብና መፃፍ ጠንቅቀው አወቁ። በተጏዳኝ ልዩ ልዩ የቤት ባልትና ሙያዎችን ተምረው በማጠናቀቃቸው የቤት ራስ ለመባል በቅተዋል፡፡ በ1892 ማለትም በተወለዱ በአሥረኛ አመታቸው ለመጀመሪያ […]

The post ስለ እቴጌ መነን በጨረፍታ (ከስሜነህ ጌታነህ) appeared first on ሳተናው .

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

  መንግስት በጠራው ውይይት ላይ ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች አልተሳተፉም
  •  ፓርቲዎቹ መቅደም ይገባቸዋል ሏቸውን ጉዳዮች አስቀምጠዋል

         መንግስት በነደፈው የ2ኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ውይይት ላይ ትናንትናና ዛሬ ተቃዋሚዎች እየመከሩ ሲሆን ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች መድረክ፣ ሠማያዊ እና መኢአድ በውይይቱ ላይ አልተሳተፉም፡፡
መንግስት ለሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች 20 አባሎቻቸውን አርብና ቅዳሜ በሚደረግ ውይይት ላይ እንዲያሳትፉ በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን ኢዴፓን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በውይይቱ መሳተፋቸውን ሲያረጋግጡ ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች ግን ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ በውይይቱ ሳይሳተፉ ቀርተዋል፡፡
ሠማያዊ ፓርቲ የመንግስት እቅድ ላይ ለውይይት ከመቀመጤ በፊት በብዙሃን ፓርቲ ዲሞክራሲ፣ በሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የነፃ መገናኛ ብዙሃንና ሲቪክ ማህበራትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየት አለብኝ ሲል በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፈው የምላሽ ደብዳቤ አስታውቋል፡፡
“በኢትዮጵያ ሰላምና እድገት እቅድ ላይ ከመወያየት በፊት በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ መወያየት አስፈላጊ ነው” ያለው የፓርቲው መግለጫ፤ መሠረታዊ ጉዳዮች መፍትሔ ባልተበጀላቸው ሁኔታ በዕቅዱ ዝርዝር አፈፃፀም ላይ መወያየት ለኢትዮጵያ እድገትና ብልጽግና ያመጣል ብሎ እንደማያምን በደብዳቤው አመልክቷል፡፡
የመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በበኩሉ፤ በውይይቱ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት በቀረበለት ጥሪ ላይ ስራ አስፈፃሚ ተሰብስቦ መቅደም ያለባቸው ብሔራዊ ጉዳዮች አሉ በማለት ከመሳተፍ መቆጠብን እንደመረጠ ለአዲስ አድማስ አስታውቋል፡፡ ፓርቲው ስብሰባው ላይ ለመሳተፋ የማይችልባቸውን ሶስት ምክንያቶች ጠቅሷል፡፡ የብሔራዊ እርቅና መግባባት ላይ ያተኮረ ስብሰባ በቅድሚያ እንዲጠራም ጠይቋል፡፡
ግዙፉ ብሔራዊ እቅድ ሁሉንም አሣታፊ በሆነ መልኩ ከግብ እንዲደርስ መጀመሪያ ሁሉንም ተቃዋሚ ያሳተፈ የብሔራዊ መግባባትና እርቅ ጉባኤ መጠራት አለበት ያለው ፓርቲው፤ “የልማት መሠረቱ የዜጐችን ሰብአዊ መብት መጠበቅ ስለሆነ የመኢአድ አባላትም ሆኑ ሌሎች የተቃዋሚ አባላት እየተሰቃዩ፣ እየተሳደዱ፣ እየተዋከቡ ባለበትና አጠቃላይ የሰብአዊ መብታቸው በተገፋበት ሁኔታ እንዲሁም ዜጐች ክልልህ አይደለም በሚል እየተፈናቀሉ፣ በስብሰባው ላይ መገኘት ፍሬ ሊሰጥ የሚችል አይደለም” ብሏል፡፡ የሚካሄደው ውይይት ለሠፊው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚዲያዎች በቀጥታ የሚሠራጭ ባለመሆኑ ሃሳባችን ተቆራርጦ የተሳሳተ መልዕክት ሊተላለፍ ይችላል በሚል ስጋት ከውይይቱ ራሱን ያገለለው ደግሞ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ነው፡፡
ትናንት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ በተደረገው የመጀመሪያ ቀን ውይይት መክፈቻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የተገኙ ሲሆን “የተለያዩ የፖለቲካ አቋሞች ቢኖሩም ያለን አንድ አገር በመሆኑ ሁሉም አካላት በአገሪቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ መወያየትና ግብአት መስጠት አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን አፈፃፀም ላይ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው አደም ጽሑፍ ካቀረቡ በኋላ የፓርቲ ተወካዮቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የኢዴፓ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ፤ የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱ መልካም መሆኑን ጠቅሰው በመጀመሪያው የእቅድ ዘመን ላይ ተመዘገበ ተብሎ የቀረበው የኢኮኖሚ እድገት አሃዝ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ በተለይ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅና ግብርናን ከማዘመን አንፃር የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉ ጠቅሰዋል፡፡ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ተወካይ በበኩላቸው፤ የኑሮ ውድነቱ ላይ መንግስት ትኩረት አድርጐ አልሠራም፤ በቀጣይ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ተወካይ ደግሞ ከመሠረተ ልማት ግንባታና ከሃብት ብክነት ጋር የተያያዙ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡ ትናንት በመጀመሪያው የእቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ሲደረግ የዋለ ሲሆን በዛሬው እለት በቀጣይ ሊተገበር በታሰበው ሁለተኛው እቅድ ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ ኢዴፓ፣ አንድነት፣ ቅንጅት እና ኢራፓን ጨምሮ 20 ያህል ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ተሣታፊ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

Amdom Gebreslasie የመንግስት ኣካላት ይሁኑ ኣይሁኑ ለህዝቡ ግልፅ ያልሆኑ ኣካላት በክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ የሚገኘው የዮዲት ጉዲት ( ጋዕዋ ) መቃብርና በዙርያው የሚገኙ ተዛማጅ ቅርሶች ወዳልታወቀ ቦታ ነቅለው ሊወስዱ ሲሞክሩ ከኣከባቢው ህዝብ ጋር ተጋጭተዋል። መቃብሩ የሚገኝበት ወረዳ ክልተ ኣውላዕሎ፣ ኣይናለም ቀበሌ፣ …

በትግራይ ክልተ ኣውላዕሎ የህዝባ ቁጣ ተቀሰቀሰ። Read more »

በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ በሃጂ ስነስርአት ወቅት በተፈጠረ መጨናነቅ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 47 መድረሱን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገልጿል፡፡ ባለፈው መስከረም 13 ቀን 2008 በሳዑዲ አረቢያ ሚና አካባቢ በደረሰ አደጋ ከ1ሺህ በላይ የተለያዩ ሀገር የሃይማኖታዊ ስነ ስርአቱ ተሳታፊዎች …

በሃጂ ስነስርአት ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 47 ደርሷል Read more »

ፓርቲዎቹ መቅደም ይገባቸዋል ሏቸውን ጉዳዮች አስቀምጠዋል የኢህአዴግ  መንግስት በነደፈው የ2ኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ውይይት ላይ ትናንትናና ዛሬ ተቃዋሚዎች እየመከሩ ሲሆን ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች መድረክ፣ ሠማያዊ እና መኢአድ በውይይቱ ላይ አልተሳተፉም፡፡ መንግስት ለሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች 20 አባሎቻቸውን አርብና ቅዳሜ በሚደረግ ውይይት ላይ እንዲያሳትፉ …

የኢህአዴግ መንግሥት በጠራው ውይይት ላይ ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች አልተሳተፉም:: ታማኝ ተቃዋሚዎች ተሳትፈዋል:: Read more »

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤ ሰሞኑን የተቋቋመው አዲሱ የኢህአዴግ መንግስት፣ ለኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግሮች መፍትሔ ሊሰጥ አይችልም አለ፡፡ “የህዝብን ይሁንታ አግኝቶ ውክልና ያለው መንግስት አይደለም” ሲልም መድረክ ተቃውሟል፡፡ ከትናንት በስቲያ በጽ/ቤቱ ለሀገር ውስጥና ለውጭ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጠው መድረክ፤ ኢህአዴግ ለአዲሱ …

መድረክ፤ አዲሱ የኢህአዴግ መንግሥት ለሀገሪቱ ችግሮች መፍትሄ አይሠጥም አለ Read more »

– የኢትዮጵያ ጠቅላላ የብድር መጠን ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወይም ከ1.2 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው:: – የአገሪቱ የብድር ዕዳ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አንፃር ሃምሳ ከመቶ ደርሷል:: – የዋጋ ግሽበት ከሚጠበቀው በላይ የእጥፍ እጥፍ አሻቅቧል:: – በፋይናንስ አቋሞች ላይ ቁጥጥር …

የወያኔ ባለስልጣናት እና አማካሪዎቻቸው ውሸታቸውን አጧጡፈውታል::እውን የብድር እዳ ክምችት አያሳስብም? (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

የሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት በጣም ረጅም ፅሁፍ በርካታ ሂሶችን ያነሳ ነው! የህወሕት ልሳን በክልልና የፌደራል ተቇማት ስፖንሰር እየተደረጉ ተቃዋሚዎችን እንደሚወነጅሉ መከላከያው በፖለቲካው እንደተዘፈቀ ይተቻል! ፍርድ እንደጠፋ ይሄሳል! መቶ ፐርሰንት አስቂኝ ብቻ ሳይሆን አደገኛ ነው ይላል! እውን ኢትዮጵያ ፓርላማ አላት? ብሎ ይጠይቃል! …

ብልሹ አስተዳደርን የዴሞክራሲ ምህዳር በማስፋትና በተቋማት ግንባታ (ሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት “ጆቤ”) Read more »

ከአዲስ አበባ በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ ሲጓዙ የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞንን ያገኛሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ዞኖች ሞቃታማና ዓመቱን ሙሉ የሚፈስ የውኃ ሀብት ያላቸው ናቸው፡፡በእነዚህ አካባቢዎች ከሚበቅሉ የግብርና ምርቶች መካከል በቆሎ፣ ማሽላ፣ ማሾ፣ ሽንኩርትና ትምባሆ ቅጠል ይገኙበታል፡፡ የአካባቢው አርሶ አደሮች …

የኦሮሞ ዞን አርሶ አደሮች ኡኡታ – “…..የሚያዋጣንን ማብቀል አልቻልንም ::” Read more »

አቶ ኢሳያስ በታዲያስ አዲስ ጋዜጠኞች ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለምን ቻይና እንደቀጠረ ሲጠየቁ ፣ በፈረንጅኛ እንዲህ ነበር ያሉት <<China is the biggest humanity >> ፣ በመጀመሪያ ይህ አርፍተ ነገር ምን ማለት ነው ? ብሎ መጠየቅ አይቻልም ። ሁለተኛ ምንም ማለት …

ቻይንዬ ቻይንዬ ፣ ቻይኑካ ፣ ቻይንሻ (ሄኖክ የሺጥላ ) Read more »

ዘውዴ ረታ - የታሪኩ ቀንድ ስብራት (1927 – 2008)

‹‹… ዘውዴ! ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ከሆነው ትውልድ መካከል እንደ አንተ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መንግሥት አመራር በቅርብ የማየትና የመረዳት ዕድል ያገኘ ብዙ ሰው የለም፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ያየውንና የተረዳውን፣ ጣዕም ባለው ጽሑፍ

አብራርቶ ለመግለጽ ተሰጥኦ ያለው እንደ አንተ የመሰለ ጸሐፊ ብዙ የለም፡፡ ስለዚህ በእኔ አመለካከት ሁለት የተጣመሩ ዕድሎች በአንተ እጅ ተይዘው ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ታሪኩን የማወቅና የጽሕፈት ችሎታህ ናቸው፡፡ ስለዚህ እኔ አጥብቄ አደራ የምልህ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መንግሥት ጉዳይ አንተ ዕድል አጋጥሞህ ያየኸውንና ከአዋቂዎች ዘንድ ቀርበህ ያጠናኸውን እውነተኛውን ታሪክ ገልጠህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጻፍለት፡፡ ለዚህ ሕዝብ ከአንተ በኩል ከዚህ የበለጠ የምታደርግለት ሊኖር አይችልም፡፡ አንተም አስበህ የጀመርከውን ለመፈጸም እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡ … እኛም ወዳጆችህ፣ ዕድሜና ጤና አግኝተን የምትደክምበትን ለማንበብ ያብቃን…›› 

ከአሥራ ሁለት ዓመታት በፊት ነበር ታዋቂው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደ አረጋይ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት አመራርን በቅርቡ የማወቅ ዕድል ለነበራቸው፣ ከእልፍኝ እስከ አደባባይ ከንጉሠ ነገሥቱ ያልተለዩትን ዘውዴ ረታን እውነተኛው ታሪክ ገልጠህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጻፍለት ብለው የተማፀኗቸው፡፡ 

ይህን የማበረታቻ ምክር መቼም ያልረሱት ዘውዴ ረታ አምና እጅግ ግዙፍ የሆነውን ‹‹የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት›› አንደኛ መጽሐፍ ከነገሡበት 1923 እስከ 1948 ዓ.ም. ድረስ የሚሸፍነውን ታሪክ ለንባብ አደባባይ ያዋሉት፡፡ 

የአዲሱ መጽሐፋቸውንም የተለየ ፋይዳም እንዲህ አስቀምጠውታል፡፡ ‹‹እንግዲህ ማንም ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው ኢትዮጵያ የነፃነት ችግር ያጋጠማት በሁለት ኮሎኒያሊስት በሆኑ አገሮች ነው፡፡ የመጀመሪያው የፋሽስቱ የሙሶሊኒ የግፍ ወረራ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ነፃ አውጪዎች ነን ብለው በመጡት ወዳጆቻችን በምንላቸው በእንግሊዞች ወታደራዊ የሞግዚት አስተዳደር የተፈጸመብን በደል ነው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱም ኮሎኒያሊስቶች የኢትዮጵያን ነፃነት ለማስመለስ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የደረሰበት መከራና ፈተና በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ ይህን ሁሉ በተለይ አዲሱ ትውልድ እንዲያውቀው ስለሚያስፈልግ፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ታሪኩ በተቻለ መጠን ተዘርዝሮ ቀርቦለታል፡፡›› 

ጋዜጠኛ፣ ዲፕሎማትና ስመጥር የታሪክ ጸሐፊ (ሦስት ዓይና) የነበሩት አምባሳደር ዘውዴ ረታ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዕረፍት በኋላ የነበረውን የልጅ ኢያሱን፣ የንግሥት ዘውዲቱ፣ ብሎም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ታሪክ ትክክለኛውን ሒደት የዘመኑም ሆነ መጪው ትውልድ ማወቅ ያስፈልጋል በሚል ነበር የታሪክ መጽሐፋቸውን ‹‹ተፈሪ መኰንን ረዥሙ የሥልጣን ጉዞ›› ለኅትመት ያበቁት፡፡ ‹‹በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኤርትራ ጉዳይ 1941-1963›› ሌላው በመረጃና በማስረጃ የተደገፈ ታሪካዊ መጽሐፍንም እነሆ ብለዋል፡፡ 

የኤርትራን ጉዳይ የተመለከተው መጽሐፋቸው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘበው በዶ/ር ኃይሉ ሃብቱ አማካይነት “THE ERITREAN QUESTION” በሚል ተተርጉሞ ለሕትመት ዝግጁ መሆኑም ይነገራል፡፡ 

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሕገ መንግሥቱ ከተሻሻለበት ከ1948 ዓ.ም. በኋላ የነበረውን በለውጥ የታጀበው ዓቢይ ዘመን የሚያወሳውን መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ ነበሩ አምባሳደር ዘውዴ ረታ፡፡ በተለይ በለንደን (እንግሊዝ)፣ ፓሪስ (ፈረንሣይ) እና ሮም (ኢጣሊያ) ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ስለ ዘመነ ኃይለ ሥላሴ የሚያወሱ ሚስጥራዊ ሰነዶች በቅርቡ ክፍት መሆናቸውን ተከትሎ፣ ጥናትና ምርምር ለማድረግ ነበር መስከረም 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ ባሕር ማዶ ያቀኑት፡፡ ያለሙት የዘመናት ሕልም እውን ሳያደርጉት ተቀጨ እንጂ፡፡ ሞት ቀደማቸው፡፡ የጥናታቸው ቀዳሚ መነሻ ባደረጉት ለንደን ከተማ መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በድንገት አርፈዋል፡፡ 

በኢጣሊያና በቱኒዚያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አቶ ዘውዴ ረት የተወለዱት በአዲስ አበባ ከተማ በ1927 ዓ.ም. ነው፡፡ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በፊት ደጃዝማች ገብረ ማርያም የአርበኞች ትምህርት ቤት በሚባለው፣ ከዚያም ሊሴ ገብረ ማርያም በተባለው ትምህርት ቤት ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ሬዲዮ አንባቢነትና በቤተ መንግሥት ዜና አቅራቢነት ተቀጥረው ያገለገሉ ሲሆን፣ በፈረንሣይም በጋዜጠኝነት ተመርቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ ድምፅ ዕለታዊ ጋዜጣና ወርኃዊው መነን መጽሔት ዳይሬክተርም ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የፓን አፍሪካን ኒውስ ኤጀንሲ ፕሬዚዳንት፣ የማስታወቂያ ረዳት ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርም ነበሩ፡፡ በዘመነ ደርግ የስደት ዘመናቸውም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ በዓለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ የመንግሥታት ግንኙነትና የፖለቲካ ኃላፊ ሆነው ለ13 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ 

ሦስት ዓይናው ዘውዴ ረታ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ለሃያ ሁለት ዓመት በላይ ላበረከቱት ውጤታማ ተግባር ከንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የምኒልክ የመኰንን ደረጃና የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ አዛዥ መኰንን ኒሻን ተሸልመዋል፡፡ ከተለያዩ አገሮችም ኒሻኖችን የተሸለሙ ሲሆን፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህም በባሕር ማዶና በአገር ውስጥም ልዩ ልዩ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል፡፡ 

ከ49 ዓመት በፊት ከወይዘሮ ገሊላ ተፈራ ጋር ጋብቻ መሥርተው ሦስት ልጆች ያፈሩት አምባሳደር ዘውዴ አስከሬን፣ በሳምንቱ መገባደጃ ከእንግሊዝ መጥቶ ሥርዓተ ቀብራቸው በአዲስ አበባ እንደሚፈጸም ከቤተሰቦቻቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ 

 

Minilik Salsawi – ህዝቦች እኩልነት ያልተረጋገጠባት ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰብ መብቶች ለይስሙላ በሚሰበኩባት አገር ዜጎች ህግ ይከበር ብቻ ስላሉ በሌላው አለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሸባሪ ተብለው ወህኒ የሚወርዱባት ኢትዮጵያ የሃይማኖት ምሁራን ከአያት ቅድማያቶቻቸውን የተረከቡትን እምነታቸውን በነጻነት ለማካሄድ ሲሰሩ ታፍሰው ለእስር የተዳረጉባት …

እያለማን ነው እየሰራን ነው በሚል ሽፋን ዜጎችን ማሳደድ መግደል ማፈንና ማሰር ላይ የተሰማራ ጁንታ (ምንሊክ ሳልሳዊ‬) Read more »

ፌስቡክ አንዳንዴ ጨርቁን ጥሎ ያብዳል። እብደቱ ገጀራ እስከማቀበል ሊደርስ ይችላል። እንደዚህ ሲሆን በተቻለ መጠን ጥግ ይዘህ አሰላስል፤ አብረህ እንዳታብድ ተጠንቀቅ። አንዳንዴ ደግሞ ፌስቡክ ወፈፌ ይሆናል። ወፍፎ ያወፍፍሃል። አብረህ ትወፍፍና “ግን ምን ነካኝ?” ብለህ ራስህን ትጠይቃለህ። አንዳንዴም መረን የለቀቀ ባለጌ ያደርግሃል። …

ወፈፌው ፌስቡክ… (ትንሽ ቀልዳዘል ምክር) – ዳንኤል ተፈራ Read more »

ደግ ደጉን ስናጣ ፣ ሃዘኑ መረረ ሞት አምላኩ ከድቶት፣ ገሎት በነበረ። የሠፈራችን ሙሾ አውራጅ እነሆ ጋሼ ሙሉጌታ ዐረፈ። ከዚህ ምስቅልቅሉና ቅጥ አምባሩ ከወጣ ዓለም በአካል ተለየ ። ጋሼ ሙሉጌታ ከእንግዲህ የሃገሩን አፈር በሞቱ እንኳ ላይቀምስ ነው። ዛሬ የሰው ሃገር አፈር …

“ወያኔዎችን አጥኗቸው ፣ እወቋቸው “ ሙሉጌታ ሉሌ በልጅግ ዓሊ Read more »

ኤልያስ ገብሩ አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌን በአካል አላውቀውም፤ በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሕይወት ግን ስማቸው ገንኖ ከወጡ ሰዎች መካከል በቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፍ መሆኑን ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ የሞቱን መርዶ፣ አርአያ ተስፋማርያም በፌስ ቡክ ገጹ ጽፎት ካረዳን ጀምሮ፣ በምናቤ ሙሉጌታን ማሳላሰሌ አልቀረም፡፡ ድንገተኛ ሞቱ ልብ ይነካል፤ ከውድ ሀገር ርቆ መሞት ደግሞ ልብ ይሰብራል!!! ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ስለሙሉጌታ የተለየ የአጻጻፍ ዘዬውን […]

The post እስከመቼ ስደት …እስከመቼ በባዕድ ሀገር ሞት … እስከመቼ መንገላታት …እስከመቼ ሀዘን …. appeared first on ሳተናው .

Amdom Gebreslasie = ትናት መቐለ ዩኒቨርቲ በድምፂ ወያነ ሬድዮ የሚያስተላልፈው ፕሮግራም ስከታተል ነበር። በፕሮግራሙ ስለ የኣዲሱ ዓመት የትምህር መጀመር፣ ስለ ጂቲፒ_2 እየተካሄዱ ያሉት ስልጠናዎች (ስብሰባ) በመካሄድ ላይ መሆኑ፣ በስብሰባው መሃል በዩኒቨርስቲው ስላለ ሙስና በተለይ የምግብ መበላሸትና ችግር ተማሪዎቹ ጠንከር ያለ …

“…ቢርባቹም እንዳታምፁ…!” መቐለ ዩኒቨርስቲ Read more »

የሰማይ ላይ ላም ቁጥር አንድ: መልካም አስተዳደር ስለዚች የሰማይ ላይ ላማችን በየስብሰባው እንሰማለን። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ስለእሷ ተናግረው አይጠግቡም። ይሁን እንጂ ስለዚች ላማችን ወሬዋ ይሰማል እንጂ እግሮቿ የኢትዮጵያን ምድር ረግጠው አያውቅም። ይህች ላም አንድ ቀን እግሯን መሬት ላይ ታሳርፍ ይሆናል …

የሰማይ ላይ ላሞቻችንን ቆጠራ (Inventory) – ዶክተር ታደሰ ብሩ Read more »

TPLF EPRDF Corruption in Ethiopia By Minilik Salsawi 2010

እንደሁኔታው ተስተካክሎ ቀዳዳዎችን መጠቀም አስተዋይነት ነው፡፡ መንገዶች ሁሉ በአንድ በኩል ብቻ ነው የሚሄዱት ብሎ ግትር አለመሆን ታላቅነት ነው!ዕውቀት እያነሰ በመጣ ቁጥር ሐሜትና ስለሰው መተቸት እጅግ የሚዘወተር ነገር እየሆነ ይመጣል፡፡ በዚህም ሳቢያ ችግርን በመላ ከመፍታት ይልቅ ከአፍ አፍ ማዛመት ዋና ሥራ …

ሙሰኛና ሙሰኛ ጀርባቸውን በሚተሻሹበት አገር ልማት ሃሰት ነው:: Read more »

የዚህ ታላቅ ሰው ድንገተኛ ዜና-ዕረፍት ህሊናዬን ዘልቆ አናውጦታል ፣ ለጥቂት አፍታዎች ተደነባብሬ ነበር፣ እስከ አሁንም ውስጤን በምናቤ ሳሰላስለው የሰቀቀን ስሜት እንደ ዋጠኝ አለሁ። ታላቅ ዋጋ የምትሰጡት ፣ ፋይዳ ያለው የአገር ፣ የህዝብ እና የታሪክ ስንከሳር የታጨቀበት ግዙፍ መርከብ በማእበል ተመቶ ባህር ውስጥ የመስመጥ አደጋ ደረሰበት የሚል ዜና የሰማሁ መሰለኝ። የዕውቀት ክምችት ፣ የዳበረ ልምድ ፣ […]

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 16 ቁጥር 821፤ ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን 2008 ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(ኢቢኤስ)፤ በሳምንት አንድ ቀን በጣቢያው መንፈሳዊ ዝግጅት የሚያስተላልፉ ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች፣ የታደሰ የፈቃድ ማስረጃዎቻቸውን እንዲያስገቡ አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ የቴሌቪዥኑ ፕሮግራሚንግ ኮሚቴ መስከረም 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ለአራት የሃይማኖታዊ ፕሮግራም ክፍሎች በጻፈው ደብዳቤ፤ ከጣቢያው ጋር በገቡት ውል መሠረት ለሚወክሉት የሃይማኖት ተቋም ወይም የሃይማኖት …

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በሁለተኛው የትራንስፎርሜሽን ረቂቅ እቅድ ላይ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መወያየት ተገቢና አስፈላጊ መሆኑን አስታወቁ።

Minilik Salsawi ከሕወሓት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ውስጥ ከተለያዩ የጦር እዞች እና ክፍሎች 543 የሚሆኑ የጦር መኮንኖች ለየክፍላቸው ሪፖርት ሳያደርጉ በዛው መጥፋታቸው እና የት እንደገቡ እንደማይታወቅ የመከላከያ ሚኒስቴር ሪፖርታዥ ጠቁሟል::ከተለያዩ የጦሩ ክፍሎች የተሰበሰቡ መረጃዎችን አጣቅሶ የቀረበው ሪፖርታዥ እንደሚያመለክተው በሕመም በእረፍት እንዲሁም …

ከሕወሓት መከላከያ ሰራዊት ክ500 በላይ የጦር መኮንኖች የት እንደጠፉ አይታወቅም:: Read more »

ኢሳት ዜና (ጥቅምት 27 ፣ 2008) በዋሺንግተን ዲሲ አቅራቢያ አርሊንግተን በተካሄደው በዚህ የቀብር  ስነ-ስርአትና በአሌክሳንድሪያ ከተማ በተከናወነው የጸሎት ፕሮግራም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ መገኘቱንም ለማየት ተችሏል ። ከአውሮፓ፣ ከካናዳና፣ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛት የመጡ እንዲሁም በዋሺንግተን ዲሲ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት የጸሎትና የቀበር  ስነ-ስርአት የአቶ ሙሉጌታ ወዳጆች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ እንዲሁም የፖለቲካ ተንታኝ የአቶ …

በቂ የተማረ የሰው ሃይል ባለበት ኢትዮጵያውያንን በቻይንኛ ቋንቋ አሰልጥኖ በሃገሪት የተንሰራፋውን የስራ አጥነት መቅረፍ እየተቻለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይናውያን ሴቶችን ሰብስቦ በበረራ አስተናጋጅነት መቅጠሩን CCTV Africa በድህረገጹ በቭድዮ አስደግፎ አስነብቦናል:: በኢስያ አፍሪካ መካከል የሚገኘውን የበረራ ደንበኞች ቁጥር ያሳድግልኛል ብሎ የታሰበው …

ቅምጥሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይናውያን የበረራ አስተናጋጆችን መቅጠሩ ተሰምቷል (ቪዲዮ) Read more »

መስከረም 27, 2008 አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ሃያሲ፣ ደራሲና፣ የፖለቲካ ተንታኝ ሙሉጌታ ሉሌ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የኢሳት ማኔጅመንት፣ ጋዜጠኞችና፣ መላው የኢሳት ቤተሰብ ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቶታል። አቶ ሙሉጌታ ሉሌ በተባ ብዕራቸው ሃገራዊ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ነፃነትንና፣ ፍቅርን የሰብኩ፥ በአንደበታቸው ስለኢትዮጵያ የመሰከሩ፣ እስከመጨረሻ እስትንፋሳቸው ድረስ ኢትዮጵያን ያገለገሉና፣ ኢትዮጵያን ተቀምተው በስደት የቀሩ ሃገራዊ ሃብት ነበሩ። የሙያ አባታችን ሙሉጌታ ሉሌ …

መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በ በቆጂ ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ ከ20 በላይ ወጣቶች በፖሊሶች ተደብድበው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነዋሪዎች ደግሞ ተደብድበዋል። ግጭቱ የተከሰተው የወረዳው ባለስልጣናት ቤት አፍራሽ መኪኖችን በመላክ ህገወጥ ቤቶች ያሉዋቸውን ቤቶች ማፍረስ መጀመራቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ነዋሪዎች ድንጋይ በመወርወር ተቃውሞቸውን ገልጸዋል። …

መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጸጥታ እና ከደህንነት ዋስትና ማጣት ጋር በተያያዘ፣ ስራ ያቋረጡት የመንግስት ሰራተኞች፣ ከወረዳው ባለስልጣናት ጋር ተናንት የተወያዩ ቢሆንም፣ መተማመን ላይ ባለመድረሳቸው አብዛኞቹ ዛሬም ስራ ሳይጀምሩ ቀርተዋል። አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች በግዴታ ስራ እንዲጀምሩ ቢደረግም፣ ብዙዎቹ በአድማው ቀጥለውበታል። የሀመር ወረዳ አርብቶአደሮች በየጊዜው በሚሰነዝሩት ጥቃት የፖሊስ፣ የመከላከያና የልዩ ሃይል አባላትን …

መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የተከሰተውና ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ለምግብ እጥረት የዳረገው የድርቅ ችግር በቀጣይ ወራትም ሊስፋፋ እንደሚችል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። ከብሔራዊ ሚቲሮዎሎጂ ኤጀንሲ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከኤልኒኖ ክስተት ጋር ተያይዞ ከቀጣይ ጥቅምት ወር ጀምሮ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚያጋጥም ዓለም አቀፍ ትንበያ መኖሩን በመጥቀስ፣ …

መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዳንግላ ዙሪያ ነዋሪ የሆነው አቶ ደግአረገ በአካባቢው ያሉ ወጣቶችን በትጥቅ ትግል ለሚታገሉ ሃይሎች እየመለመልክ ትልካለህ በሚል አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድቧል። ማንነታቸውን በውል ለይቶ የማያውቃቸው ሰዎች አይኑን በጨርቅ ሸፍነው ወደ ባህርዳር እንደወሰዱትና በመጨረሻም መረጃ ሲያጡ ፣ አይኑን ሸፍነው እንደለቀቁት ገልጿል።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

  የአንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስርዓተ ቀብር ዛሬ በስደት በኖረበት በሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒአ ዛሬ ማለዳ ተፈጽሟል።የዘ-ኢትዮጵአያ አዘጋጅና አሳታሚ ጋዜጠኛ ደረጄ ደስታ ባለፉት ጥቂት ቀናት በብዙ ድካም በርከት ያሉ ወዳጆቹንና የሙያ አጋሮቹን አነጋግሮ መረጃ አገላብጦ የሕይወት ታሪኩን አዘጋጅቶ ለስርዓተ ቀብሩ አድርሷል።ስለ …

የዕውቁ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስርዓተ ቀብር ተፈጽሟል። የጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ አጭር የሕይወት ታሪክ Read more »

ዩሱፍ ያሲን (ኦስሎ)

የዴሞክራሲያዊ ምንቕስቓስ ህዝቢ ትግራይ ዴምህት ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሞላ አስገዶም / Mola Asgedom

ከሰሞኑ ጫጫታ ባሻገር

የሞላ አስገዶም ኩብለላ፣ ፍርጠጣ ክሕደት ወይም በመንግሥት ደጋፊዎች እንደተባለው ወሽመጥ በጣሽ የጀግንነት ሥራ በአሥመራ ተጓዞችና ደርሶ – ተመላሾች መሓል እየተቋጠረ መጥቷል ብለን ያሰብነው ንትርኩን እንደገና አደበላለቀው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሃመር ወረዳ በዲመካ ከተማ ማክሰኞ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ እስከ ዛሬ የቀጠለ ሲሆን፣ የዞኑ ባለስልጣናት ነዋሪውን ለማነጋገር ስብሰባ ጠርተዋል። የስራ ማቆም አድማው መንስኤ ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ በአካባቢው በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ስራቸውን ለመስራት ስላላስቻላቸው ነው። የመንግስት ሰራተኞች እንደሚሉት ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በወረዳው …

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት ሳምንት በፊት በሳዑዲ አረቢያ ሚና አካባቢ በሀጂ ስነ-ስርዓት ወቅት በተከሰት ግፊያና መጨናነቅ በደረሰ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥራቸው ከ47 በላይ የበለጠ ቢሆንም ፣ የኢህአዴግ መንግስት ለዚህ ከባድ ሐዘን የሰጠው ትኩረት ማነስ እንዳሳዘናቸው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው በአዲስአበባ የሚኖሩ ሙስሊሞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመጅሊሱን ወሬ በመያዝ …

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በነሶልያ ሽመልስ የክስ መዝገብ በሽብረተኝነት በተከሰሱት ወጣት ጸሃፍት ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ዳኞች “አዳማ ስልጠና ላይ ናቸው” በሚል ለ38 ኛ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጓል። ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ለ5ኛ ጊዜ ቀጠሮ አራዝሟል። በአንድ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል የተወሰኑት መለቀቃቸው፣ ቀሪዎቹም ይለቀቃሉ የሚል ተስፋ አሳድሮ ነበር። ድንበር የለሽ …

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት አሚሶል ስር ያለውን ንብረነታቸው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት የሆኑትን ሁለት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በደቡባዊ ምዕራብ ሶማሊያ በጌዶ ግዛት በደፈጣ ውጊያ ማውደሙን አልሸባብ አስታውቋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በአሊላን መንደር ውስጥ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ሰራዊት መሃከል ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ ነው። በአርፒጂ የጦር መሳሪያ ተሽከርካሪዎቹ መመታታቸውን የአካባቢው …

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 4 ቀናት ያለማስጠንቀቂያ የተቋረጠው ኤሌክትሪክ፣ በንግድ ቤቶች እና በነዋሪዎች የእለት ተለት ህይወት ላይ ችግር ማስከተሉን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ የተቋረጠበት መንስኤ ለህዝቡ አለመገለጹንም ተናግረወዋል። ከዚህ በፊት በከተማው በተደጋጋሚ የ ኤሌክትሪክ መቋረጥ የሚከሰት ሲሆን ፣ ያሁኑ ደግሞ የተለየ ነው ሲሉ ነዋሪዎች በምሬት ይገልጻሉ። በከተማው በሳምንት አንድ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት