በኣዋሳ የመሬት መንቀጥቀጡ ኣሰጋን ያሉ ተማሪዎች ላይ ተኩስ ተከፈተ። የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው እንዲዘጋ እና ወደየቤታቸው እንዲበተኑ ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበረ። ፌደራል ፓሊስ እንደተለመደው በዱላ እና ወደ ሰማይ በመተኮስ ሰልፉን ለመበተን የሞከረ ቢሆንም አልተሳካም። ሰልፉን ተከትሎም …

በኣዋሳ የመሬት መንቀጥቀጡ ኣሰጋን ያሉ ተማሪዎች ላይ ተኩስ ተከፈተ። Read more »

በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በሃገሪቱ መጭውን ጊዜ ኣስመልክቶ የሕወሓት ወታደራዊ ባለስልጣናት ስብሰባ በመቀመጥ የተወያዩ ቢሆንም በሰራዊቱ ላይ ያለውን መተማመን አጅግ የወደቀ አና ለውጊያ ሞራል የለውም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሳቸው ታውቃል። ከዚህ ቀደም እንደተባለው የትግራይ ሚሊሻዎችን በወታደራዊ መልኩ ማደራጀት የትግራይ ወጣት …

ሰራዊቱ ለውጊያ የሚሆን ሞራል የለውም ሲል የሕወሓት ወታደራዊ ሹማምንት ስብሰባ ጠቆመ። Read more »

By Eyob Dadi የቀድሞ ኮከብ ሮናልዲንሆ ጎቾ የሴይንት ናግጄ የእግርኳስ ውድድር ለመክፈት በህንድ ይገኛል። ሮናልዲንሆ በህንድ ቆይታው ከሞት መትረፉን ነው ጎል ስፓርት የዘገበው። ሮናልዲንሆ በአድናቂዎቹ ፉጨት እና ጩኸት ታግዞ በሚጓዝበት ወቅት ግዙፍ የሆነ የዛገ የትራፊክ መብራት ፓል ከመኪናው በቅርብ ርቀት ላይ ከፊትለፊቱ ተሰብሮ ወድቆ መኪናውን ሳያገኘው ቀርቷል። ፓሉ ሲወድቅ አድናቂዎቹ በድንጋጤ ጸጥ እንዳሉ ሲታወቅ ወዲያው … Continue reading “ሮናልዲንሆ ከሞት ተረፈ”

#Ethiopia  #‎ShareEthioHarmony‬ ‪#‎EBCDocumentary‬ ‪#‎1460DaysOfPeacefulStruggle‬ ‪#‎EthioMuslims‬ #MinilikSalsawi ‹‹ማህበራዊ መስተጋብራችንን እንካፈል!›› መንግስት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በሌሎች ወገኖቻቸው መካከል ለማ facebook.com/hashtag/shareethioharmony ንደድ የሚሞክረውን እሳት በጋራ የማጥፋት ጥሪ! ከረቡእ ጥር 18 እስከ እሁድ ጥር 22/2008 የሚቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ረቡእ ጥር 18/2008 መንግስት በኢትዮጵያውያን …

በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በሌሎች ወገኖቻቸው መካከል ለማንደድ የሚሞክረውን እሳት በጋራ የማጥፋት ጥሪ! Read more »

የአዲስ አበባንና የፊንፊኔ ዙሪያ ዞኖችን የከተሞች ማስፊፊያ እቅድ ተንተርሶከተቀሰቀሰውና በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶችተማሪዎች ሲያካሂዱ የቆዩት የተቃውሞ እንቅስቃሴ የክልሉ መንግስት እቅዱንመተዉን ካስታወቀም በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም መቀጠሉ እየተዘገበ ነው።

ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ ጊዳ ወረዳ፤ ጉደቱ አርጆ ከተማ በተከናወነ የሰርግ ሥነ ሥርዓትላይ በጭፈራው መሃል የተቃውሞ ድምጽ …

በሬክተር የምድር ንዝር መለኪያ 4.3 ያስቆጠረ የመሬት ነዉጥ ባለፈዉ እሁድ ምሽትና ሰኞ ጥዋት በሃዋሳ ከተማ መሰማቱ ተዘገበ።

የምድር ነዉጡ በሰዉ ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት አላደረሰም ተብሏል። ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮሮሬሽን ትንታኔ የሰጡ የአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከርሰ-ምድር ጥናት ምሁርን መግለጫ ተንተርሶ እስክንድር ፍሬዉ ዘግቧል።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

 

ይገረም አለሙ

Dr. Merera Gudan and Girma Seifu. ዶ/ር መረራ ጉዲና (በግራ) እና አቶ ግርማ ሰይፉ (በቀኝ)

ለዚህች ጽሑፍ መነሻ ምክንያት የሆነኝ አቶ ግርማ ሰይፉ “የዶ/ር መረራ የቡዳ ፖለቲካ እና መቀበል ያቃተው መራራ እውነት”በሚል ርዕስ ያስነበቡን ጽሑፍ ሲሆን፤ ርሳቸው ለጽሑፋቸው ምክንያት የሆናቸው ደግሞ “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” የሚለው የዶ/ር መረራ መጽሐፍ እንደሆነ ገልጸዋል። የቡዳ ፖለቲካ የሚለው ቃልም ከዚሁ መጽሐፍ የተገኘ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ ጎጃም ዞን የየስማላ ከተማ ነዋሪዎች መብራት ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን፣ በሰሜን ጎንደር ሃሙሲት ከተማ ደግሞ የከተማው ነዋሪዎች የቧንቧ ውሃ ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን ዘጋቢያችን ነዋሪዎችን አነጋግሮ የላከው ዘገባ ያሳያል። ነዋሪዎቹ ችግሮቻቸው እንዲፈቱላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ሰሚ አካል አላገኙም። በሞጣ ከተማ ደግሞ መብራት ከተቋረጠ 2 ወር …

Ethiopia Oromo students protest addis ababa plan. የኦሮሞ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ያሰሙት ተቃውሞይገረም አለሙ

በሀገር ውስጥም በውጪም ቁጥራው እጅግ የበዛ ተግባራቸው ግን ብዙም የማይታይ ፓርቲዎች አሉ። እነዚህ የሚችሉት ተዋህደው አንድ በመሆን፤ የማይችሉት ተባብረው ትብብርም ይሁን ግንባር በመፍጠር የነጻነት ቀናችንን ለማፋጠን የሚያስችል ትግል ያደርጉ ዘንድ ስንመኝ፣ ስንጠይቅ፣ ስንማጸን፣ ይህን ባለማድረጋቸውም ስንኮንን ወዘተ ዓመታት ተቆጥረዋል። እነርሱ ግን መተባበሩ ቀርቶ መከባበሩ አልሆን ብሎአቸው፣ ተደጋግፎ መቆሙ ቢቀር አንዱ ለአንዱ እንቅፋት ከመሆን መቆጠብ ተስኖአቸው ወያኔ ያሻውን እንዳሻውና ባሰኘው መንገድና ግዜ እየፈጸመ ከዚህ እንዲደርስ አድርገውታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በወያኔው ፍርድ ቤት የቀረበው የሰማያዊ ፓርቲው ዮናታን ተስፋዬ ድጋሚ በቀጠሮ ወደ እስር ቤት ተመልሷል። ፍ/ቤቱ ለ2ኛ ጊዜ 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጠ *‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› ዮናታን ተስፋየ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ማዕከል በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው …

በወያኔው ፍርድ ቤት የቀረበው የሰማያዊ ፓርቲው ዮናታን ተስፋዬ ድጋሚ በቀጠሮ ወደ እስር ቤት ተመልሷል። Read more »

በትናንትናው ዕለት በእስራኤል ሃገር ከአሜሪካ ኤምባሲ ፌት ለፊት የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እንደተካሄደና በተለያዩ ፍከራዎች ደምቆ ውሏል ከተሰሙት መፈክሮችም መካከል ” ኢትዮጵያ አትቆረስም ” አሜሪካ እርዳታሽን ለወያኔ መንግስት አቁሚ” የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የሚደርሰው ግፍ ይቁም” ወያኔ ገዳይ መንግስት ነው …

በእስራኤል ሃገር ከአሜሪካ ኤምባሲ ፌት ለፊት የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እንደተካሄደና በተለያዩ ፍከራዎች ደምቆ ውሏል Read more »

የኢትዮጵያ ሙስሊም ፈተና በ224 ደቂቃዎች (በዘላለም ክብረት) ክፍሉ ከኮሪደሩ ላይ ከተንጠለጠለ አምፖል በሚመጣ ብርሃን ፈገግ ብሏል፡፡ እኔም ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ወደክፍሉ ስገባ ከክፍሉ አንደኛው ጫፍ ላይ አንድ ቀጠን ያለ ሰው ድምፁን በትንሹ ከፍ አድርጎ ቁርዓን ‹እየቀራ› ነበር፡፡በክፍሉ ሌላኛው ጫፍ …

የኢትዮጵያ ሙስሊም ፈተና በ224 ደቂቃዎች (በዘላለም ክብረት) Read more »

ክፍል አንድ ‪#‎እውነቱን_ማወቅ_ለሚፈልግ‬ ከቀናት በፊት በፓርቲያችን ውስጣዊ ጉዳይ ለመነጋገር ከኢ/ር ይልቃል ጋር ከቢሮ ውጪ ተገናኝተን ለመነጋገር ችለናል፡፡በዚህ አጋጣሚ እየሆነ ያለወ ነገር ዳር ቆሞ ከመመልከት ይልቅ በመነጋገር መፍትሔ ማምጣት ይቻላል የሚል ጽኑ እምነት ያለው፣በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተሳትፎ እረጅም እድሜ የስቆጠረው ምርጥ ጓዳችን …

እውነቱን ማወቅ ለሚፈልግ‬ – Yidnekachew Kebede – ሰማያዊ ፓርቲ Read more »

በኢትዮጵያ፥ በኦሮሞ ተቃዋሚዎችና በመንግሥቱ የፀጥታ ኃይሎች መካከል ለሁለት ወራት ግድም ግጭቶች ከተካሄዱ በኋላ፥ ባለሥልጣናቱ የአዲስ አበባን ግዛት ለማስፋት የኦሮሞ ገበሬዎችን ያፈናቅላል የተባለውን ማስተር ፕላን መሠረዛቸውን አስታውቀዋል።

ታዛቢዎች ግን፥ የመንግሥቱ ባለሥልጣናት የማስተር ፕላኑን ለመሰረዝ በወሰዱት እርምጃ ላይ ጥርጣሬ አላቸው።

እርምጃው በእርግጥ የፖሊሲ ለውጥ መደረጉን ያመለክታል? ወይስ ለቀረቡበት ተቃውሞዎች ማስታገሻ  ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ።

ባልደረባችን ሳሌም ሰለሞን ያጠናቀረችው ዘገባ አለ። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል።

ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

 

ከይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ኣሰጣጥ ጋር በተያያዘ በኣዲስ ኣበባ ከፍተኛ ተቃውሞ ይነሳል የሚል ስጋት ኣይሏል። የኦሮሞ ገበሬዎችን ለማፈናቀል ሲነሳ በተቃውሞ ምክንያት መግቢያ መውጫ ያጣው የሕወሓት ኣገዛዝ ፊቱን በማዞር የኣዲስ ኣበባ ነባር ነዋሪዎችን ኣፈናቅሎ በምትካቸው በሕወሓት ስር ያሉትን የኣንድ ብሄር ትግሬ ካድሬዎችና …

ከይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ኣሰጣጥ ጋር በተያያዘ በኣዲስ ኣበባ ከፍተኛ ተቃውሞ ይነሳል የሚል ስጋት ኣይሏል። Read more »

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን ከቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሰናበተ! ዘገባ፡- በናታ በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በነበረው ፕሮፌሽናል ተጫዋቾችን በማያካትተው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ዋሊያዎቹ ከምድባቸው ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል። ጠባብ የማለፍ እድል ይዘው ወደ ሶስተኛው የምድብ ጫወታ ቢያቀኑም ከምድቡ ደካማ በሆነችው አንጎላ 2-1 ተረተዋል። ወደ ጫወታው ስናመራ በማግባት ቅድሚያውን የወሰዱት አንጎላዎች ሲሆኑ በ54 ኛው ደቂቃ ላይ የመሃል ሜድ … Continue reading “የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን ከቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሰናበተ!”

የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ምክትል ኣዘጋጅ ታሰረ ፤ ኣዘጋጁን ማእከላዊ ማሰቃያ እንዳለ ይታወቃል።(ምንሊክ ሳልሳዊ) በላይ ማናየ የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የነገረ ኢትዮጵያ ምክትል አዘጋጅ ከአራዳ ፍርድ ቤት ወደ ማዕከላዊ መወሰዱን ማረጋገጥ ተችሏል።በላይ ማናዬ የታሰሩ የሰማያዊ ኣባላትን ጉዳይ ተከታትሎ ለመዘገብ ፍርድ ቤት በተገኘበት …

የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ምክትል ኣዘጋጅ ታሰረ ፤ ኣዘጋጁም ማእከላዊ ማሰቃያ እንዳለ ይታወቃል።(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

አዲስ መረጃ የቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም በተመለከተ:- የመጨረሻውን አልበም ካወጣ አራት አመት የሆነው ዝነኛው ቴዲ አፍሮ ቀጣዩን አልበም ኒዮርክ ስትዲዮ ለመስራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታወቀ። ቴዲ ከአዲሱ አልበም ውስጥ አምስት ዘፈኖቹን የሚያቀናብርለት ታዋቂውና የሶስት ግራሚ ተሸላሚ የሆነው ዝነኛው አሜሪካዊ አቀናባሪ ጎርደን …

የቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም የሚያቀናብርለት የ3 ግራሚ ተሸላሚ የሆነው ዝነኛው አሜሪካዊ አቀናባሪ ጎርደን ዊሊያምስ ነው። Read more »

በገድለ ወለተ ጴጥሮስ ላይ እንዲህ የሚል ታሪክ አለ፡፡ እምነ ወለተ ጴጥሮስ ወደ ዋልድባ ገዳም በገባች ጊዜ ለአንዲት እናት ረድእ ሆነች፡፡ እኒህ እናት ፈጽሞ ጠባይ የሚባል ያልፈጠረባቸው ነበሩ፡፡ አሁን የተናገሩትን አሁን ይሽሩታል፣ በሆነው ባልሆነው ይቆጣሉ፤ ከእርጅናቸው ብዛት የተነሣ ይነጫነጫሉ፤ ትእዛዛቸው ሁሉ ውኃ ቀጠነ ነው፡፡ በዚህ ዐመላቸው የተነሣ ማንም ከእርሳቸው ጋር ለመኖር ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ከእርሳቸው ጋር ለመኖር ፈቃደኛ ሆና ለረዥም ጊዜ ያገለገለቻቸው ወለተ ጴጥሮስ ነበረች፡፡
አንድ ቀን መነከሳዪያቱ ተሰባስበው ‹እንዴት ከእኒህ እማሆይ ጋር ለዚህን ያህል ዘመን አብረሽ ለመኖር ቻልሽ? እንዴትስ ታገሥሻቸው? እንዴትስ መሮሽ ጥለሽ አልወጣሽም? ሲሉ ጠየቋት፡፡ ወለተ ጴጥሮስም ‹ንብ ታውቃላችሁ? እኒህ እናት ንብ ናቸው፡፡ ከእርሳቸው የሚገኝ ብዙ ዕውቀት፣ ብዙ ጥበብ፣ ብዙ ልምድ፣ ብዙ ታሪክ፣ ብዙም ጸጋ አለ፡፡ ነገር ግን እናንተ መናደፋቸውን ብቻ ነው የምታዩት፤ ስለዚህም ማሩን ከእርሳቸው ልትቆርጡ አልቻላችሁም፡፡ ንብ ትናደፋለች፣ ነገር ግን ማር የሚገኘው ከምትናደፈው ንብ ነው፡፡ የማትናደፈው ዝንብ ቆሻሻ እንጂ ማር የላትም፡፡ እኔ ግን ከንብ ጋር እንዴት እንደሚኖር ዐውቃለሁ፤ ከንብ ጋር እየኖርኩም ማሩን እቆርጣለሁ› አለቻቸው ይባላል፡፡

ትዳር ማለትም እንዲሁ ነው፡፡
‹አበባው አበበ ንቡም ገባልሽ
እንግዲህ አልማዜ ማር ትበያለሽ›
የሚለው የሠርግ ዘፈን ከዚህ ጋር ይስማማል፡፡ አፍንጅም ከጋብቻ በኋላ ያለውን ጫጉላ ‹ማር ጨረቃ› ሲለው ይኼ ታይቶት እንደሆነ እንጃ፡፡ አንዳንዶቹ የትዳር ንድፊያው ብቻ ስለሚታያቸው ወይ ትዳር ሳይመሠርቱ ወይም የመሠረቱትን ትዳር ሲፈቱ ይታያሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የትዳር በጎነቱን ብቻ ስለሚያውቁት እስኪገቡበት ሲጓጉ፣ ከገቡበት በኋላ ደግሞ
ስሳል እንዳልኖርኩኝ አስንቺን እስካገኝ
ካገኘሁሽ ወዲያ እላለሁ አውጣኝ
እያሉ ያንጎራጉራሉ፡፡
ምናልባትም ደግሞ በሠርግ ላይ የሚዘፈነው
ማን ፈርሚ አለሽ፣ ማን ፈርሚ አለሽ
በተወለወለው በአለንጋው ጣትሽ
የሚለው ዜማ ‹ትንቢት ይቀድሞ ለነገር› ዓይነት ሳይሆን አይቀርም፡፡
ትዳር ግን ሁለቱም ብቻ አይደለም፡፡ ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው፡፡ ንብ ሁለት ጠባይ አላት፡፡ አንዱ ያስደስታል፤ ሌላኛው ያስከፋል፡፡ አንዱ ጤና ይሆናል፣ ሌላኛው ግን ያማል፡፡ አንዱ ይጣፍጣል፤ ሌላው ግን ይመራል፡፡ አንዱን ይቆርጡታል፣ ሌላውን ግን ይከላከሉታል፡፡
ትዳርም እንዲሁ ነው፡፡ ሁለት ጠባይ አለው፡፡ አንደኛው ያስቃል አንዱ ያሰቅቃል፤ አንዱ ያስደስታል፣ ሌላው ያሳዝናል፡፡ አንዱ ግቡ ግቡ ሌላው ውጡ ውጡ ያሰኛል፡፡ አንዱ ይናደፋል፣ አንዱ ይጣፍጣል፤ አንዱ ጤና ሌላው ሕመም ይሰጣል፡፡ አንደኛው ግን ያለ ሌላው አይገኝም፡፡
ይኼን ለመድኃኒት፣ ለብርዝ፣ ለጠጅ፣ የምናደርገውን ማር የምትሰጠው ንብ ናት የምትናደፈው፡፡ ያቺ ስትናደፍ ፊት የምታሳብጠው፣ ውስጥን የምትመርዘው፣ የምትጠዘጥዘው፣ ንብ ናት ማሩን የምትሰጠው፡፡ በትዳርም ውስጥ ሁለቱም አሉ፡፡ ጭቅጭቁ፣ ንዝንዙ፣ ጠቡ፣ ኩርፊያው፣ አንዱ ለሌላው የግድ መታዘዙ፣ አንዱ የሌላው አገልጋይ መሆኑ፣ አንዱ ያለ ሌላው ለመወሰን አለመቻሉ፤ የሌላውን ጠባይ፣ የሌላውን ዐመል የግድ መታገሡ፤ ከሚታገሡት ሰው ጋር አብሮ መኖሩ፤ ይኼ ነው የንቧ ንድፊያ፡፡
ሰው የወለደውን አያገባም፡፡ ያሳደገውን አያገባም፣ የተዛመደውን አያገባም፡፡ የቤቱን ሰው አያገባም፡፡ ሰው ደግሞ በዐመልም፣ በፍላጎትም፣ በአመለካከትም ይበልጥ የሚቀራረበው አብሮት ከኖረና ካደገ ሰው ጋር ነበር፡፡ እምነቱና ባሕሉ ግን ጋብቻን እስከ ሰባት ቤት አርቆ ለባዕድ ይሰጠዋል፡፡ አብረነው ላልኖርነው፣ አብረን ላላደግነው አብረን ላልተወለድነው፣ ላልተዛመድነው ሰው፡፡ ከሌላ ተወልዶ፣ ሃያ ሠላሳ ዓመት ሌላ ቦታ ኖሮ፣ ከሌላ ጋር አድጎ፣ ሌላ ጠባይ ነሥቶ፣ በሌላ መንገድ መጥቶ ያገኘነውን ሰው ነው የምናገባው፡፡ ይኼንን ሰው ወይም ይህችን ሴትዮ በዕውቅ አላሠራናትም፣ አላሠራነውም፡፡ ዐመሉ እንዲህ፣ ሐሳቡ እንዲያ፣ መንገዱ እንዲህ፣ እምነቱ እንዲያ፣ ዕውቀቱ እንዲህ፣ ምግባሩ እንዲያ ብለን ዝርዝር ሰጥተን አላስመረትነውም፡፡ ‹ሬድ ሜድ› ነው ያገኘነው፡፡ ዓይተን እንመርጣለን እንጂ፣ መርጠን አናሠራም፡፡
ንብን እኛ ብናሠራት ኖሮ የርሷን መናደፍ ለዝንብ ሰጥተን የዝንብን ጠባይ ለንብ በመለስንላት ነበር፡፡ ግን ንብን እንዲሁ ሆና አገኘናት፣ አላመድናት፣ ወደ ቀፏችን አስገባናት እንጂ አንድም አልፈጠርናት፣ አንድም አላስፈጠርናት፡፡ ንቧን ማርና ንድፊያ እንደያዘች ነው ያገኘናት፡፡ ሰው በውስጡ ማርና ንድፊያ አለው፡፡ የተገዛ የሱፐር ማርኬት ማር የሚበላ ልጅ ንብ የምትባለውን የሚያውቃት በጣሳው ላይ ባለው ሥዕል ነው፡፡ መልኳን እንጂ ንድፊያዋን አያውቀውም፡፡ እርሱ እድሜ ልን በንብ እየተነደፈ ለጌቶቹ ማር ቆርጦ የሚሰጥ ገባርም ንብ እንደምትናደፍ እንጂ ማር እንደምትሰጥ አያውቅም፡፡ ‹ጌቶች ምን ምን ቢላቸው ነው ይህን የቀፎ እንጀራ የሚያስገፈግፉኝ› አለ የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡
አንዳንዶች በሠርግ ዘፈን፣ በተረት፣ በሠርግ ሥነ ሥርዓት፣ በስብከት፣ በድራማና በፊልም ትዳርን ሲያዩ ምናልባት ማሩ ይሆናል የሚታያቸው፡፡ ያገኛቸውም ሰው ሁሉ ‹ምነው አንተ አታገባም እንዴ› ይላቸዋል እንጂ ተገብቶ ምን እንዳለ አይነግራቸውም፡፡ ‹የዛሬ ዓመት፣ የዛሬ ዓመት፣
የእንትናዬ አባት
ሲወለድ ማሞ፣ ሲወለድ ማሞ
እንመጣለን ደግሞ፤
ያሉት ሰዎች ደግመው ላይመጡ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶችም ማሞ ሲወለድ እንደማይመጡ እያወቁት የሚዘፍኑት ዘፈን ነው፡፡ ‹የዛሬ ዓመት የእንትናዬ አባት› መሆን ለሁሉ ያልተሰጠ መሆኑን የሚናገርም የለም፡፡ ይኼ ያልተነገራቸው የዋሐንም ናቸው ልጅ የለም ብለው የሚፋቱት፡፡
ሌሎች ደግሞ ትዳር ሲባል የንቧ ንድፊያ ነው ትዝ የሚላቸው፡፡
‹ታሠረች አሉ በትዳር፣
ከንግዲህ ቀረ መሽርቀር› የሚለው ዘፈንም ውስጠ ዘ አለበት፡፡
ትዳር ምን ዕዳ ነው ትዳር ምን ዕዳ ነው
ጉልቻው ስሙኒ ምጣዱ ብር ነው
የሚለው ባሕላዊ ዜማ የምጣዱና የጉልቻው ዋጋ ዛሬ ሰማይ በነካበት ጊዜ ቀርቶ ትናንትም በርካሹ ዘመን ትዳርን ‹ዕዳ› ነው እያለ የንቧን መናደፍ እየነገረን ነው፡፡
ትዳር ግን ሁለቱም ብቻ አይደለም፡፡ ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው፡፡ ለማሩ ስንል ንድፊያውን መታገሥ፡፡ ቆይተህ ደግሞ ንድፊያውን መልመድ፡፡ ገበሬ ቀፎ ሰቅሎ ንብ ሲያንብ ንብ እንደምትናደፍ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም፡፡ የማትናደፍ ንብ ከፈለገ በየደጁ ቆሻሻ ፍለጋ የምትጓዘው ዝንብ ነበረችለት፡፡ ዝንብ ምን ጠባይዋ ሸጋ ቢሆን፤ ጠብ የሚላት ግን ሌላ ነገር ነው፡፡ ይህን ያውቃል ገበሬው፡፡ እያወቀም ንብ ያንባል፡፡ ማነብ ብቻ ሳይሆን ከንብ ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻልም ያውቃል፡፡ ንብ ትናደፋለች፤ ግን እንዳትናደፍ ማድረግም ይችላል፡፡ የምትወደውና የማትወደው ሽታ አለ፡፡ ስትቀርብህ ምን ማድረግ እና ምን አለማድረግ እንዳለብህ ገበሬው ያውቃል፡፡ በሀገራችን ንብ አትገደልም፡፡ ነውር ነው፡፡ ብትነድፍም አትገደልም፡፡ የንቧን ማር ለመውሰድም ንቧን ገድሎ፣ አጥፍቶ፣ ጎድቶ ወይም አሰቃይቶ ሳይሆን በጭስ ራሱን እየተከላከለ፣ ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ፣ ወደ ንቧ ቀፎ ገብቶ ነው ማሩን የሚቆርጠው፡፡ ንቧም ሳትጎዳ፣ ማሩም ሳይጠፋ፣ እርሷም ሳትናደፍ፡፡
ትዳርም እንዲህ ነው፡፡ አኗኗሩን ነው ማወቅ፡፤ የንቧን ንድፊያ የመቀነሻውን መንገድ ነው ማወቅ፣ የማሩን አቆራረጥ መንገድ ነው ማወቅ፡፡ ደግሞምኮ አስገራሚው ገበሬው የሚከባከበው ይህቺኑ የምትናደፈውን ንብ መሆኑ ነው፡፡ የምትቀስመው አበባ ትፈልጋለች፣ ንጹሕ አካባቢ ትፈልጋለች፣ ከጉንዳንና ከአውሬ ነጻ የሆነ ቀፎ ትፈልጋለች፡፡ ግን ትናደፋለች፡፡ ደግሞም ማር ትሰጣለች፡፡ ትዳር አስደሳች ነገር ብቻ ሳይሆን አስመራሪ፣ አንገብጋቢ፣ አስጠሊታ፣ ጨጓራ አንዳጅ፣ አንጀት ቆራጭ፣ ልብ አቃጣይም ክፍል አለው፡፡ ይናደፋል፡፡ ግን ደግሞ ክብካቤም ይፈልጋል፡፡ ንጹሕ ልብ፣ ታማኝ ኅሊና፣ ቻይ አንጀት፣ ታጋሽ ሆድ፣ ጠቢብ አእምሮ፣ አሳላፊ ልቡና ይፈልጋል፡፡ ለምን ቢሉ? ማር ይሰጣልና፡፡
አንዳንዶች ቤት ካለችው ወይም ካለው ንብ ይልቅ ውጭ ያቺውን ወይም ያለው ዝንብ ሲያደንቁ ይሰማል፡፡ መቼም ከቀፎ ውጭ ምን እንደሚኖር የታወቀ ነው፡፡ ንብ ትናደፋለች ብሎ ንብ የማያነባ ገበሬ ስንፍናውን እንጂ የንቢቱን ክፋት ማንም አይረዳለትም፡፡ ጥበብ አልባ መሆኑን፣ ትዕግሥት አልባ መሆኑን፣ ተሸናፊነቱን እየተናገረ እንጂ የንቧን ጠባይ እየተናገረ አለመሆኑን ሁሉም ያውቅለታል፡፡ የትዳርን ችግር ብቻ የሚያወራ፣ በትዳር ተመርሮ ከቀፎው ውጭ የሚሄድም ስንፍናውንና ዐቅመ ቢስነቱን እንጂ የቀፎውን ችግር እየተናገረ አይምሰለው፡፡ ቀፈ ውስጥ ማር የምትሠራው ን እንዳለች ሁሉም ያውቃልና፡፡ ሌላው ቀርቶ ውጭ ያለቺው ዝንብም ይኼንን ታውቃለች፡፡   
አንዳንዶች ከንብ ጋር የመኖር ጥበብ ሲያንሳቸው የማትናደፍ ንብ ፍለጋ ይኳትናሉ፡፡ የማትናደፍ ንብ መፈለግ ከመረቁ አወጡልኝ ከሥጋው ጦመኛ ነኝ እንደማለት ነው፡፡ ወይም የማትዞር መሬት እንደመፈለግ፡፡ የመትናደፍ ንብ ከፈለግክ ከዝንብ ጋር ተጋባ፡፡ 
ይህ ጽሑፍ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የወጣ ነው፡፡

በአዲስ አበባ : የተለያዩ አካባቢዎች በግራቪቲ ፅሁፎች አሸብርቀው አደሩ ! ምሽቱን ተፅፈው ካደሩ ፅሁፎች መካከል ድምፃችን ይሰማ ! ግድያው ይቁም በቃ ! አምባገነናዊ ፍርድ አንቀበልም ! ብሔራዊ ጭቆናው ይብቃ ! የታሰሩት ይፈቱ ፣ ዋ ዋ ዋ ፣ ና ሌሎች መፈክሮች …

በአዲስ አበባ : የተለያዩ አካባቢዎች በግራቪቲ ፅሁፎች አሸብርቀው አደሩ ! Read more »

ሕወሓት በፈጠራና በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም በጎሳ ፖለቲካ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Ethiopianism‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ንቅናቄ ተከትሎ የሚራገቡ የዘረኝነት ኣጀንዳዎች እየበረቱ ነው፤በስሜት የሚነዱ ጥቂቶች ፣የሕወሓትን መሰረታዊ የዘረኝነት ኣጀንዳ …

ሕወሓት በፈጠራና በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም በጎሳ ፖለቲካ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው። Read more »

መልዓከ መንክራት መምሕር ግርማ ወንድሙ ለሁለት ወራት እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በዋስ መፈታታቸውን በሰበር ዜና መዘገባችን ይታወሳል። በዚህም መሠረት መምሕር ግርማ ከእስር ከተፈቱ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ይቅርታንና ምሕረትን የዳሰሰ እንዲሁም በሐይማኖት መጽናትን አጽንዖት የሰጠ ልብ የሚነካ ትምህርት በስልክ ሰጥተዋል። ይህ …

መምሕር ግርማ ወንድንሙ ከእስር ከተፈቱ ወዲህ የሰጡት ትምህርት Read more »

ማስተር ፕላኑ ይቁም ከተባለ፤የታሰሩት ይፈቱ፣ገዳዮችም ለፍርድ ይቅረቡ! (ይድነቃቸው ከበደ) “….የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ንጹሃና ዜጎች በመንግሥት ታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን አስመልክቶ፣ መጽናናትን ለቤተሰቦቻቸው ከመመኘት ባለፈ ምንም አይነት ውሳኔ አለማሳለፉ ፣በእርግጥም ውሳኔው የኦህዴድ እንዳልነበረ የሚያሳብቅ ነው፡፡” “የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ …

ማስተር ፕላኑ ይቁም ከተባለ፤የታሰሩት ይፈቱ፣ገዳዮችም ለፍርድ ይቅረቡ! (ይድነቃቸው ከበደ) Read more »

ማለቴ ለማኝነት ( ሄኖክ የሺጥላ ) ቋር ላይ የተነጣጠረ ምስማር ቢጣመም ጥፋቱ የምስማሩ ፣ ወይም የቋሩ ወይም የመዶሻው አይደለም ። ጥፋቱ ያናጢው ነው ። በግብርና መር ኢኮኖሚ የሚመራ ስርዓት፣ ህዝቡ በድርቅ ምክንያት ለረሃብ ወይም ረሃቡ ገፍቶ ለቸነፈር ‘ና ለጠኔ ቢዳረግ …

ማለቴ ለማኝነት ( ሄኖክ የሺጥላ ) Read more »

“ተቆርቋሪ ነን” ባዮች ለረዥም ዓመታት በሰላምና በፍቅር ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ምዕመናን ስታገለግልና ለብዙዎች አለኝታና መጠጊያ የነበረችውን የዋሽንግተን ዲሲን ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን በመበጥበጥና ህጋዊና ምዕመና የመረጡትን ቦርድ በአመጽና በተንኮል ከስልጣኑ በማውረድ ከፍተኛ ወንጀል ፈጽመዋል። እነዚህ “ተቆርቋሪ ነን” ባዮች ከጀርባቸው …

በዲሲ ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመው ረብሻና ብጥበጣ Read more »

በሕወሓት የደሕንነት ሹሞች ትእዛዝ ኣራት እስረኞች መገደላቸው ታወቀ። የኦሮሞ ንቅናቄ ኣሁንም ከወያኔ ኣገዛዝ ኣቅም በላይ መሆኑ አየተነገረ ነው። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከኬንያ ናይሮቢ ታፍነው ከሶስት ኣመት በፊት ወደ ኣዲስ ኣበባ ኣሮጌው ኣይሮፕላን ማረፊያ የጨለማ …

በሕወሓት የደሕንነት ሹሞች ትእዛዝ ኣራት እስረኞች መገደላቸው ታወቀ። የኦሮሞ ንቅናቄ ኣሁንም ከወያኔ ኣገዛዝ ኣቅም በላይ መሆኑ አየተነገረ ነው። ‪ Read more »

እነ ጌታቸው ሺፈራው ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው *‹‹ከቤተሰቦቻችን ጋር እንዳንገናኝ ተደርገናል›› ተጠርጣሪዎች *‹‹6 ቀን ደንበኛየን ለማግኘት ተመላልሼ ተከልክያለሁ›› የጋዜጠኛ ጌታቸው ጠበቃ አምሃ መኮንን በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከታህሳስ 15/2008 ዓ.ም ጀምሮ በማዕካለዊ ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የሚገኙት እነ …

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማዕካለዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙት እነ ጌታቸው ሺፈራው ፍርድ ቤት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡ Read more »

ህግ እና ደንብ የጣሰው ማነው? ———– ሞልቶ ሲንተረከክ እንሸሽገው ቢባል በየት በኩል; ሰብቶ ደልቦ እራፊ ሰውነቱን አልሸፍን ሲል አደባባይ ወጥቶ በሰው አይን መመታቱ አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አልፅፍም ብዬ ነበር….ለማን ነው የምፅፈው; ማንስ ምን አግብቶት ነው የምንፅፍለት; እያልኩ፡፡ …

ህግ እና ደንብ የጣሰው ማነው? -Eyasped Tesfaye – ከሰማያዊ ፓርቲ Read more »

ሃሰትና ክህደት የማይታክተው ዘረኛው የህወኃት አገዛዝ በስኳር ኮርፖሬሽን- ያስከተለው መዘዝ፤ መቼም በተመራጫችን ሚዲያ /ኢሳት/ መታፈን ጾማችን ቀርቶ የኢቢሲ/ኢቲቪ/የአየር ጊዜኣችን በመጨመሩ የማንሰማው ጉድ የለም፣ ይህ ሃፍረትና ይሉኝታ የማያውቅ መንግስት በራሱ ዓይን እያየን በራሱ ሚዛን እየመዘነን አያስታውሱም በሚል እሳቤ እስከሚሰለቸን ውሸቱን እያቀረሸብን …

ሃሰትና ክህደት የማይታክተው ዘረኛው የህወኃት አገዛዝ በስኳር ኮርፖሬሽን- ያስከተለው መዘዝ፤ Read more »

@semayawiParty #Ethiopia ሰማያዊ ፓርቲዎች የሕዝብን ትግል መምራት ሲገባቸው በውስጥ የፓርቲ ሽኩቻ ተጠምደዋል። (ብር ኣምባር) በኦሮሚያ ክልል በሕዝብ ተነሳሽነት በተለያዩ ኣከባቢዎች የሕወሓት መራሹን ኣገዛዝ በመቃወም ታላላቅ የሕዝብ እምቢተኝነቶች አና ተቃውሞዎች እየተካሄዱ ይገኛል።እንዲሁም በጎንደር ኣከባቢ ከፍተኛ የሕዝብ ተነሳሽነት ለለውጥ እና የኢትዮ ሱዳን …

ሰማያዊ ፓርቲዎች የሕዝብን ትግል መምራት ሲገባቸው በውስጥ የፓርቲ ሽኩቻ ተጠምደዋል። (ብር ኣምባር) Read more »

7ቱ ዋና ዋና የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያን በተመለከተ የቀረበውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽድቀዋል። አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የቀኝ አክራሪዎች ብቻ ውሳኔውን ተቃውመውታል። ለህጉ መጽደቅ ከፍተኛ ትግል ሲያካሂዱ የሰነበቱት የህብረቱ የፓርላማ አባል ሚስ አና ጎሜዝ በውሳኔው መደሰታቸውን ተናግረዋል። በጣምጠቃሚ የሆነ ሰነድ …

ከአውሮፓ ለእኛ ለኢትዮጵያን የተሰማ መልካም ዜና‬ – የፓርላማ አባላቱ ውሳኔ Read more »

በሃረርጌና ወለጋ ተቃውሞዎች የቀጠሉ ሲሆን በኣርሲ ተማሪዎች በስለት ተወግተዋል። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Harerge‬ ‪#‎Wellega‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Arsi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)– የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች አና ተማሪዎች በሕወሓት መራሹ መንግስት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ኣጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን በዛሬው እለት በወለጋ ጃርሶ አና ነቀምት እንዲሁም …

በሃረርጌና ወለጋ ተቃውሞዎች የቀጠሉ ሲሆን በኣርሲ ተማሪዎች በስለት ተወግተዋል። Read more »

ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2008) በሆሳዕና ከተማ ከመንጃ ፈቃድ ቅጣት እና አስተዳደር ብልሹነት ጋር በተያያዘ የህዝብ የትራስፖርት ማመላለሻ አገልግሎት ለሁለት ቀን ተቋርጦ መዋሉት ዛሬ ሰኞ ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ። አንድ ሆሳዕና ወደሌላ ወረዳ ወይም ከወደ ዋና ዋና ከተሞች የሚያጓጉዙ የትራንስፖት መገናኛ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ህዝቡ ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ውስጥ ላይ እንደሆነ አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ በሆሳዕና …

በባ/ዳር ከተማ በትናንትናው አለት ምሽት ላይ አንድ ጎይቶም ተወልደ የተባለ የወያኔ ደህንነት በባህርዳር ከተማ ወጣቶች ተደብድቦ ቀበሌ 12 ዲሽ ቦይ ውሰጥ ተከቶ በመገኘቱ የተበሳጩት የወያኔ ደህንነቶች ታጣቂወችን እና ፖሊሶችን በማሰማራት እና በመስተባበር ዛሬ ረፋዱ 4 ሰአት ገደማ ላይ ከ300 በላይ በመንገድ ላይ በገሩፕ ሲሄዱ ያገኞቸውን ወጣቶች እየደበደቡ በመኪና እየጫኑ ወደ ተለያ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ እንዳሰሮቸው […]

ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 7ቱ ዋና ዋና የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያን በተመለከተ የቀረበውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽድቀዋል። አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የቀኝ አክራሪዎች ብቻ ውሳኔውን ተቃውመውታል። ለህጉ መጽደቅ ከፍተኛ ትግል ሲያካሂዱ የሰነበቱት የህብረቱ የፓርላማ አባል ሚስ አና ጎሜዝ በውሳኔው መደሰታቸውን ተናግረዋል። “በጣም ጠቃሚ የሆነ ሰነድ ነው፣ በተለይ ዋና ዋና …

ፖሊስ አምስት ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያካሔደ ነው ከደረጃቸው ዝቅ የተደረጉት የሀገረ ስብከቱ ሓላፊ ይገኙበታል አማሳኞች፣ ጠንቋይ አስጠንቋዮችና መናፍቃን ፈተና ኾነዋል (ሰንደቅ፤ ረቡዕ፤ ጥር ፲፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የደብረ ብርሃን መኖርያ ቤታቸው፣ ታኅሣሥ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ምሽት ቦምብ መፈንዳቱ ተገለጸ፡፡ በመንበረ …

ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ምንጮች እንደገለጹት ጥር 11 ፣ 2008 ዓም 11 ሰዓት አካባቢ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ በተነሳው ግጭት በርካታ ተማሪዎች ተጎድተዋል።ግጭቱ ወደ ከተማው በመስፋፋቱ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ ፣ መኪኖችም ተሰባብረዋል። የግጭቱ መንስኤ በትክክል አልታወቀም። የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የፈደራል አባላት ከተማዋን መቆጣጠራቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ …

ድግሥ በቤተ-መንግሥት ‪#‎በአዲስ_ገጽ_መጽሔት‬ በባለፈው ሳምንት ለንባብ የበቃ “በኢሉባቡር መቱ በመንግሥት ቅጥረኞች ሙሽራ ይገደላል፤በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በቤተ-መንግሥት ደግሞ የአቶ ኃይለማርያም ልጅ ዶ/ር ሶስና እና ከእጮኛዋ አቶ አቤል ድል ባለ ድግስ ይጋባሉ” ————————————- እንደ መንደርደሪያ ፣ በስታዲዮም አካባቢ የሚነገር አንድ የአራዳ …

ድግሥ በቤተ-መንግሥት = ይድነቃቸው ከበደ Read more »

በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የሆነ ግጭት መኖሩን የኖርዌይ ኤምባሲ በኣዲስ ኣበባ ኣስታወቀ። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Gambela‬ ‪#‎Norway‬ ‪#‎ClashsinGambela‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ በክልሉ በሚደረገው የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት መከሰቱን ከቦታው የሚሰሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።አንደ ኤምባሲው የመረጃ ጥቆማ መሰረት። Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) Sist oppdatert: …

በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የሆነ ግጭት መኖሩን የኖርዌይ ኤምባሲ በኣዲስ ኣበባ ኣስታወቀ። Read more »

መንግስት ኮሚቴዎቻችንና ቤተሰቦቻቸውን በቃሊቲ ማወከብ መቀጠሉ ታወቀ ። ሬዲዮ ዳንዲ ሀቃ ጥር 11 /2008 የህዝበ ሙስሊሙን የመብትጥያቄ : ይዘው መፍትሄ ለማፈላለግ በመንቀሳቀሳቸው ብቻ በአምባገነኑ ስርአት እጅ ወድቀውና : በመንግስታዊው የካንጋሮ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው : ከሰባት አመት እስከ ሀያ ሁለት …

መንግስት የህዝበ ሙስሊሙን ኮሚቴዎችንና ቤተሰቦቻቸውን በቃሊቲ ማወከብ መቀጠሉ ታወቀ ። Read more »

ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2008) ዳግም በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ረቡዕ በጥምቀት በዓል አከባበር ወቅትም በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሎ መዋሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ከቀናት በፊት በምስራቅ ሃረርጌና በምስራቅ ወለጋ አካባቢዎች ሲካሄድ የሰነበተው ተቃውሞ አልባት አለማግኘቱንና የጸጥታ ሃይሎች በስፍራው እርምጃ መውሰድ መቀጠላቸውም ታውቋል። የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት ትምህርት ያቋረጡ ዩኒቨርስቲዎች ትምህራትቸውን እንዲቀጥሉ ጥረታቸውን …

አፈንዲ ሙተቂ

የስራ ግዴታዬ ሆኖ ከህዳር ወር 2007 (November 2014) ጀምሮ በመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ የተጻፉ ሰነዶችን እየመረመርኩ ነው፡፡ በዚህም ድሮ የማላውቃቸውን አስደናቂና አስገራሚ ታሪኮች ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ለረጅም ጊዜ እንቆቅልሽ ሆነው ሲያስቸግሩኝ ለነበሩት ጉዳዮችም ምላሽ አግኝቻለሁ፡፡ ለብዙ ዓመታት ስፈልጋቸው የነበሩትን ምርጥ መጻሕፍትንም አግኝቼ ይዘታቸውን በቅርበት ለማወቅ ችያለሁ፡፡

 

ታዲያ በዚህ ምርመራዬ ያስተዋልኳቸው ሌሎች ጉዳዮችም አሉ፡፡ ከነርሱም አንዱ አንዳንድ ጮሌዎች ታሪክን በመጻፍ ስም ፖለቲካን የሚያሸከረክሩበት ጥበብ ነው፡፡ ለዚህ ዋቢ ይሆነኝ ዘንድ የአንድ ሀገር ዜጋ የሆኑ ሁለት ምሁራንን ልጥቀስ፡፡

—-

ሞርዴኻይ አቢር (Mordechai Abir) የሚባል ስም ታውቃላችሁ?…. አዎን! ስለ “ዘመነ መሳፍንት” የተጻፉ ጽሑፎችን ያነበበ ሰው “አቢር” የሚለውን ስም በደንብ ያስታውሳል፡፡ እኝህ ሰው የቀድሞው “ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ዩኒቨርሲቲ” (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) የታሪክ ፕሮፌሰር ነበሩ፡፡ ደርግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ደግሞ ወደ እስራኤል በመጓዝ በኢየሩሳሌም በሚገኘው የሂብሩ ዩኒቨርሲቲ መምህርነት አገልግለዋል፡፡ አቢር “The Era of Princes” በሚል ርዕስ የጻፉት መጽሐፍ በምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው፡፡ እኔም በአንድ ወቅት (የዛሬ አስር ዓመት ገደማ) መጽሐፉን አንብቤው ነበር፡፡

 አቢር በጣም ዝነኛ የሆነ ሌላ መጽሐፍም አላቸው፡፡ ርዕሱ “Ethiopia and the Red Sea” ይሰኛል፡፡ በየትኛውም ወገን ሆኖ ስለኢትዮጵያ ታሪክ የሚጽፍ ሰው ይህንን መጽሐፍ እየደጋገመ ይጠቅሳል፡፡ ታደሰ ታምራት፣ ሪቻርድ ፓንክረስት፣ ነጋሶ ጊዳዳ፣ መርዕድ ወልደ አረጋይ፣ ሙሐመድ ሐሠን፣ ላጵሶ ድሌቦ፣ ኡልሪች ብራውኬምፐር፣ አባስ ሐጂ ገነሞ፣ አሌሳንድሮ ጎሪ እና ሌሎችም ፕሮፌሰሮች የአቢርን መጽሐፍ እንደ ምንጭ ይጠቀሙበታል፡፡ ሰለሰሜን ኢትዮጵያም ሆነ ስለደቡቡ ክፍል በተጻፈ መጽሐፍ ውስጥ “Abir” የሚለውን ስም በግርጌ ማስታወሻ እና በመጽሐፉ ማጣቀሻ ክፍል ውስጥ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን “Ethiopia and the Red Sea”ን ለረጅም ጊዜ አይቼው ስለማላውቅ በምሁራን ዘንድ ተመራጭ የሆነበትን ምክንያት ለመረዳት ስቸገር ቆይቻለሁ፡፡ ዘንድሮ ግን ፈጣሪ ብሎልኝ  አግኝቼዋለሁ፡፡  ብዙ ጊዜ እየመላለስኩ ካየሁት በኋላም መጽሐፉ በምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘበትን ምክንያት ለመረዳት ችያለሁ!!

አዎን! ፕሮፌሰር አቢር ከልቡ ምሁር ናቸው፡፡ እውነተኛ ምሁር! መጽሐፋቸውን ያጠናቀሩት በእውነተኛ ምሁራዊ መንገድ ነው፡፡ ብዙዎችን እንቅ አድርጎ ሊያሰምጣቸው የሚታገላቸው ኢ-ምሁራዊ ሸፍጥና ውንብድና በመጽሐፋቸው ውስጥ የለም፡፡ አድሎ፣ መረጃ ማምታታት፣ የተወላገደ እይታ፣ ማስመሰል፣ መሸፈጥ ጂንኒ ጀቡቲ በመጽሐፉ ውስጥ አይታዩም፡፡ በመሆኑም “Ethiopia and the Red Sea” በህይወቴ ከገጠሙኝ አጃዒበኛ መጻሕፍት መካከል አንዱ አድርጌ መዝግቤዋለሁ፡፡ እውቀትን መገብየት ለሚሻ ሰው ግሩም መማሪያ ነው፡፡ ለተመራማሪዎችና ለተማሪዎች እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ማጣቀሻ ነው፡፡

ፕሮፌሰር አቢር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ስድስት መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡ ሁሉም መጻሕፍት በምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ አላቸው፡፡ ከነርሱ መካከል ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለት መጻሕፍት የዓለማችን ቁጥር አንድ ኢንሳይክሎፒዲያ በሆነው “ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ” ቀዳሚ የማጣቀሻ ምንጮች በመሆን recommend ተደርገዋል፡፡

                       

ፕሮፌሰር አቢር እስራኤላዊ ናቸው፡፡ ታዲያ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ምርምር ሲያደርጉ የነበሩት እስራኤላዊ እሳቸው ብቻ አልነበሩም፡፡ ሌሎችም በዘርፉ ብዙ ስራዎችን አቅርበዋል፡፡ ከነርሱም አንዱ ሀጋይ ኤልሪክ ነው፡፡ “ሐጋይ ኤርሊክ” የሚለውን ስም ካወቅኩ አስራ አምስት ዓመታት አልፏል፡፡ ነገር ግን ከመጽሐፎቹ ያነበብኩት Ethiopia and the Middle East የሚል ርዕስ ያለውን ብቻ ነው፡፡ ሀጋይ ከመጽሐፎቹ ይልቅ በሴሚናሮችና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ የሚያቀርባቸውን በርካታ አጫጭር ጽሑፎችን ነው ያነበብኩት፡፡ ከህዳር 2007 ወዲህ ባለው ጊዜ ውስጥ ግን ሶስት ያህል መጽሐፎቹን አይቼለታለሁ፡፡ እናም አጃዒብ አልኩ!!

  ይገርማል!! ፕሮፌሰር ሃጋይ አወዛጋቢ ሰው ሆኖ ብቅ ያለው በቅርብ ዘመናት በሚጽፋቸው ጽሑፎቹ ይመስለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰውየው ከመነሻው ጀምሮ የተወላገደ እይታ ያለው መሆኑን ነው ያስተዋልኩት፡፡ ምሁራዊ ውንብድና በመጽሐፎቹ ውስጥ እግሩን አንሰራፍቷል፡፡ ከሀጋይ መጽሐፍ ፖለቲካ እንጂ አንዳች የታሪክ እውቀት አይጨበጥም፡፡ ደግሞም የብዙዎቹ መጻሕፍት ጭብጥ “ኢትዮጵያ ራሷን ካልጠበቀች በሙስሊም አክራሪዎች ልትዋጥ ትችላለች” የሚል ነው፡፡ ባጭሩ “ሃጋይ” የእስራኤሉ ሞሳድ በኛ ላይ የተከለው የማስፈራሪያ ሳይኮሎጂስት እንጂ የታሪክ ምሁር ሆኖ አልተገኘም፡፡

በጣም የሚገርመው ደግሞ ሃጋይ ሌሎች ፀሐፊዎችን የሚፈርጅበት ድፍረቱ ነው፡፡ አንድን ክስተት ከርሱ በተለየ አኳኋን ለጻፉ የታሪክ ምሁራን በቶሎ ስም ያወጣላቸዋል፡፡ ሰውዬው ክርስቲያን ከሆነ “ኮሚኒስታዊ አስተሳሰብ ስላለው ነው” ይለዋል፡፡ ሙስሊም ምሁራንን ደግሞ ሁለት ሰሞችን ይሸልማቸዋል፡፡ ጸሐፊው የመካከለኛው ዘመን ሰው ከሆነ “Fanatic writer” ይለዋል፡፡ ፀሐፊው የዘመናችን ሰው ከሆነ ግን “Radical Islamist writer” ይለዋል፡፡ ከርሱ የሚቃረን ትርክት የጻፉ ሰዎችን እንዲህ ብሎ በሚፈርጅ ሰው የተጻፈ መጽሐፍ የታሪክ ማጣቀሻ የሚሆንበት አግባብ በጭራሽ የለም፡፡

የሀጋይ የላሸቀ ምሁራዊ በዚህ ብቻ የተገታ አይደለም፡፡ የታሪክ መረጃዎችን ለራሱ እንደሚመቸው እየገለባበጠ ይጽፋል፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ቁርኣን የአማርኛ ትርጉም በብዙ ምሁራን ተሳትፎ የተከወነ ሆኖ ሳለ (ዋነኞቹ ተርጓሚዎች ሼኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሃጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ ቢሆኑም) እርሱ ግን “ትርጉሙን ያከናወኑት ሃጂ ዩሱፍ ዐብዱራሕማን ነው” ይለናል፡፡ ሀጋይ እንዲህ የሚለው ሃጂ ዩሱፍን ለማድነቅ እንዳልሆነ ልብ በሉ፡፡ ይህንንም ትረካ የፈጠረው እርሱ በአድናቆት አቅሉን የሚስትላቸው ሼኽ ዐብዱላሂ ሙሐመድ (ዐብዱላሂ አል-ሐበሺ) በ1948 ከኢትዮጵያ የተባረሩት ሃጂ ዩሱፍ ዐብዱራሕማን በዶለቱት ሴራ ነው በሚል ለሚዘበዝበው ትረካ እንደማስረጃ ለመጠቀም ፈልጎ ነው፡፡ አንባቢያን “ሃጂ ዩሱፍ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤን አባብለው ሼኽ ዐብዱላሂ ከሀገር እንዲጠፉ የማድረግ አቅም ነበራቸው እንዴ” ብለው ሲጠይቁ የሃጋይ ኤርሊክ ጽሑፍ “ሰውዬው እንዲያ ማድረግ ይቅርና በቅቤ ምላሳቸው ንጉሡን በማሳመን ቅዱስ ቁርኣን እንዲተረጎም ያደረጉ ሼኽ ነበሩ” የሚል መልስ ይሰጣቸዋል ማለት ነው፡፡ ይህቺ ነች ዘዴ!! ይህቺ ነች ሸፍጥ!!

በሌላ በኩል ሃጋይ ኤርሊክ በቀጥታ ጠብ ጫሪነትን የሚያንጸባርቁ ጽሑፎችንም ይጽፋል፡፡ ለምሳሌ የሃጋይ አንዱ ጽሑፍ “The Grandchildren of Abraha” የሚል ርዕስ አለው፡፡ አብረሃ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በተወለዱበት ዘመን የመንን ሲገዛ የነበረው የአክሱም ንጉሥ እንደራሴ ነው፡፡ ታዲያ ሀጋይ በዚህ ጽሑፍ የአሁኖቹን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሪዎች “የአብረሃ የልጅ ልጆች ናቸው” ይላቸውና “እነዚህ ጀግኖች የተስፋፊውን የአክራሪውን የእስልምና ጂሃዲስቶች ድባቅ መምታት ይችላሉ” የሚል እድምታ ያለው ትረካ ይተረትራል፡፡ አብረሃ የጥንቱ የአክሱም ንጉሣዊ ግዛት ተወላጅ እንደነበረ ማንም አይክድም፡፡ ይሁን እንጂ የዛሬዎቹን የኢትዮጵያ ገዥዎች የአብረሃ ዝርያዎች ማለትም ሆነ የጥንቷ አክሱም ሌጋሲ አስቀጣይ አድርጎ ማቅረብ ስህተት ነው፡፡ የጥንቷ አክሱም በማህበራዊ ስብጥሯ ህብረ-ብሄር እንጂ የአንድ ብሄር ሀገር አልነበረችም፡፡ ግዛቷ ደግሞ ከትግራይ ባሻገር ኤርትራን፣ ሰሜን ምስራቃዊ ሱዳንና አብዛኞቹን የሰሜን ኢትዮጵያ ክልሎች ይጠቅላል፡፡  አብረሃ ከነዚህ ሁሉ ግዛቶች በየትኛው እንደተወለደ በትክክል አይታወቅም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የዘመናችን የኢትዮጵያ መሪዎች የጥንቱ አብረሃ ሌጋሲ ወራሾች ናቸው የሚያስብል የታሪክና የአንትሮፖሎጂ ማስረጃ የለም፡፡

  

 የጽሑፉ አደገኛነት ግን ይህ አይደለም፡፡ የሃጋይ ምሁራዊ ሸፍጥ የሚያስከፋው ጥንት የተፈጸመን ታሪክ አሁን ካለው ጂኦ-ፖለቲካዊ ትርምስ ጋር እየቀላቀለ የጠብ ጫሪነት ስሜትን ለማንገሥ በመጣሩ ነው፡፡ የታሪክ ምሁር ዋነኛ ግብ የሰው ልጆች ትናንት የፈጸሟቸው ስህተቶችን እንዳይደግሙ ማስተማር እና ድሮ የነበራቸውን በጎ የአዕምሮና የማቴሪያል እሴቶችን ጠብቀው ወደ ቀጣዩ ትውልድ እንዲያስተላልፉ ማስቻል ነው፡፡ ሀጋይ ግን ታሪክን ሸርና ብጥብጥን ለማውረስ ሲል ብቻ የሚጠቀምበት ነው የሚመስለው፡፡

—-

ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለት ምሁራን (ሞርዴኻይ አቢር እና ሀጋይ ኤርሊክ) ይሁዲዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ሁለቱም የተለያየ ምሁራዊ ልቀትና ርትእ ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ምሁራን “የአቢርን መጽሐፍ ማንበብ አለብህ” እያሉ ሲናገሩ የነበሩት “በአቢር መጽሐፍ ውስጥ እውቀት አለልህ” ማለታቸው እንደሆነ ገብቶኛል፡፡  ሀጋይ ኤርሊክ ግን በታሪክ ስም ጽዮናዊ ፖለቲካውን የሚያሰራጭ ሸፍጠኛ ነው እንጂ የምሁር “ኳሊቲ” የለውም፡፡

አንድ ነገር ግን አለ፡፡ ይሁዲ በሙሉ መጥፎ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ ስህተት ነው፡፡ በጣም ስህተት!! ይህ የአዶልፍ ሒትለርና የመሰሎቹ አስተሳሰብ ነው እንጂ የጤናማ ሰው አስተሳሰብ አይደለም፡፡ አይሁድ በሙሉ መጥፎ እንዳልሆነ ለመረዳት የሚሻ ሰው የፕሮፌሰር አቢርን መጽሐፍ ብቻ ማንበብ ይበቃዋል፡፡ የህዝብን አንድነት የሚያናጉትን እንደ ሀጋይ ኤርሊክ ዓይነቶቹን መሰሪ ጸሐፊዎች ግን ጠንቀቅ በሏቸው፡፡ 

—–

First written on August 13/2015
Re-written on January 19/2016

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

Bewketu Seyoum and Yared Tibebu በእውቀቱ ሥዩም እና ያሬድ ጥበቡ

ከሁለት ቀኖች በፊት ስለበእውቀቱ ሥዩም አድናቆታቸውን በፌስቡክ ላይ የገለጹ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ለበእውቀቱ ያላቸውን አድናቆት እኔም እጋራቸዋለሁ፤ ነገር ግን የእነዚህ ሰዎች አድናቆት በእውቀቱ ራሱንና ማንነቱን እንዲከዳ ይቃጣቸዋል። አንዱን አውቀዋለሁ፤ ከፖሊቲካና ከትጥቅ ትግል ወደስደት ”ነጻነት” የተሸጋገረ ያሬድ ጥበቡ የሚል የሚያኮራ ስም ይዞ የስደት መምህር የሆነ ነው፤ ሁለተኛው ሚስተር ቴዲ ገብርኤል ይባላል። እነዚህ ሁለት ስደተኞች በእውቀቱ ሥዩምን በጣም ስለሚወድዱትና ስለሚያከብሩት በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ እንዲቀርላቸው ይፈልጋሉ፤ በዚህ ብቻ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ስሜት መገመት በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ወደዝርዝር አልገባም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ሠይፉ ማሩ

“የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” ዶ/ር መረራ ጉዲና Dr. Merera Gudinas new bookዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” በሚል አዲስ መጽሐፍ አስነብቦናል። በአንድ ጋዜጣ ላይ የዶክተር መረራ ከዩኒቨርሲቲ መሰናበት ያመጣው አንድ በጎ ጎን መሆኑን አንብቤያሁ። እኔም በዚህ እስማማለሁ። ብዙ የሀገራችን ፖለቲካኞች ጋዜጠኛ መቅረፀ ድምፅ ይዞ በሚጠይቃቸው ጥያቄ መልስ ከመስጠት የዘለለ ብዕርና ወረቀት አገናኝተው የሚያምኑበትን የፖለቲካ መስመር እና በግላቸው ያላቸውን ምልከታ ማካፈል ይቸግራቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተስፋዬ ገብረአብ

የህወሓትን የጓዳ ወግ ማወቅ አስቸጋሪ የነበረበት ዘመን እንደዋዛ አልፎአል። ዛሬ ቀዳዳቸው በዝቶ፤ ቴክኖሎጂውም አግዞ የፈፀሙት ብቻ ሳይሆን ያሰቡትም በቀላሉ ይገኛል። ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነው። መረጃ ከሌለ ምንም ነገር የለም። ለችግሮች መፍትሄም አይገኝም። ወያኔ ዛሬ በአስር ሺዎች ኦሮሞዎችን በገፍ የሚያስረው ስለ ቄሮ በቂ መረጃ ስለሌለው መሆኑ ይታወቃል። ተቃዋሚ የፖለቲካ ተንታኞች ወይም የማህበራዊ ድረገፅ ፀሐፊዎች አንዳንድ ጊዜ አስቂኝ ስህተት ይሰራሉ። ማለትም ሳያውቁ ለወያኔ የሚጠቅም መረጃና ምክር ይፅፋሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

By Eyob Dadi የቀድሞው የኤሲሚላን እና የጁቬንቱስ አማካይ የነበረው አንድሪያ ፒርሎ በእግርኳስ ቆይታው ያየው ምርጡ ወጣት ተጨዋች ተናግሯል። ፒርሎ የቡድን አጋሩ የነበረው ፓል ፓግባን ምርጡ ወጣት ተጨዋች ሲል ያወድሰዋል። ፓግባ 2012 ላይ በማንቸስተር ዩናይትድ በቂ የመሰለፍ እድል በማጣቱ ወደ ጣሊያኑ … Continue reading

በኦሮሚያ  ባሌ ክፍለሃገር ውስጥ  ጣዕመ ወልደየስ እና ቤተሰቦቹ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ንብረት የሆነው የእርሻ ማሳ በእሳት ቃጠሎ ወድሟል ። ለጥምቀት በኣል የወጡ የኦሮሞ ወጣቶች ለተቃውሞ የሚያነሳሱ ዜማዎችን ኣዜማቹሃል በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ ከኣዲስ ኣበባ ከተለያዩ ኣከባቢዎች ታፈሰው መታሰራቸው ታውቋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ …

በባሌ ክፍለሃገር የሕወሓት ባለሃብቶች ንብረት ወደመ።ለጥምቀት በኣል የወጡ የኦሮሞ ወጣቶች ከኣዲስ ኣበባ ታፈሰው ታሰሩ:: Read more »