ሕወሓት በፈጠራና በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም በጎሳ ፖለቲካ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው።

ሕወሓት በፈጠራና በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም በጎሳ ፖለቲካ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Ethiopianism‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ንቅናቄ ተከትሎ የሚራገቡ የዘረኝነት ኣጀንዳዎች እየበረቱ ነው፤በስሜት የሚነዱ ጥቂቶች ፣የሕወሓትን መሰረታዊ የዘረኝነት ኣጀንዳ የሚያራግቡ ጥቂቶች፣ ታሪክ ቀመስ ምሁር ነን ባዮች የኣንድ ብሄር የበላይነት የሚያጦዙ ሹምባሾች፣በዕልህ የገቡበት ሃገር ወዳድ የዋሃን፣አንዲሁም በኦሮሞ ሕዝብ ደም ላይ ቆመው በኣንድነት ስም ተሸፍነው ሕዝብ ለሕዝብ ለማባላት ሃገር ለመበጣጠስ ያሰፈሰፉ ኣስመሳይ የፖለቲካ ሴራ ተብታቢዎች ፣በተንኮል ገብተው በተንኮል ወጥተው በተንኮል አየኖሩ ያሉ በኦሮሞ ስም የሚነግዱ የሃገር ቤት ቅጥረኞች አና የዲያስፖራ ነጭለባሽ ኣጭበርባሪዎች ዘረኝነትን በማራገብ ሃገሪቱ ለሕዝባዊ ለውጥ የምታደርገውን እመርታ ኣደናቅፈው በሕወሓት ኣምባገነን ጉያ እንደተወሸቀች እንድትኖር በጭፍን እየተራወጡ ይገኛሉ።

ይህን ሰሞን እያየን ያለነው ጉዳይ አጅግ የሚገርም እና የለውጥ ሃይል ነን የሚሉ ኣማሳኞች ሳይቀሩ አየተራወጡ ያሉበት የዘረኝነት መነባነብ በኣገሪቱ ስር አንዳይሰድ ትውልዱ እንዳይበከል የሚያስፈራ ጉዳይ መሆኑ ውሎ ኣድርዋል፥፥የሚደርሱኝ መረጃዎች አንደሚጠቁሙት ዘረኝነትን ለማስፋፋት የተለያዩ ኣካላት ገንዘብ መድበው በሃገር ቤት ያለውን ወጣት ለፍጅት እና ለኣጀንዳቸው ማስፈጸሚያ አያጩት ነው።ይህ ደግሞ የሕወሓት አጅ የለበትም ማለት ዘበት ነው። ሕወሓት ወንጀለኘ አና ኣሸባሪ ዘረኛ እና ኣስመሳይ ማፊያ እና ዘራፊ ሕገወጥ ድርጅት ነው።

በዲያስፖራው ዘንድ በስፋት አየተራገበ ያለው ይህ ወያኔ ወለድ በሽታ ዋናው ክስተቱ የገዢው ፓርቲ ሕወሓት የፈጠረበት የበታችነት ስሜት ሲሆን በሕወሓቶች ዘንድ ከበታችነት ለመላቀቅ በሚደረግ መራወጥ የሚፈጠር ጥላቻ ዘረኝነት የሰረጸባቸው ያዩት የሰሙት ሁሉ የሚያስደነብራቸው የበታች መደቦች ኣንድ ጉዳይ በተነሳ ሰኣት ሁሉ ዘር ላይ የሚንጠለጠሉ እና የስልጣን ጥማትን ለማርካት ሲባል የሃገር አና ሕዝብን ሃብት ለመበዝበዝ የነገ ትውልድ ኣደጋ የማይታያቸው ሕዝብን በዘር በመከፋፈል ለመግዛት የሚያደርጉት ደባ ነው። ቆቤ ኦሮሞ ፤ ቤተ ኣማራ ፤ ትግራዋይ ምናምን እየተባለ በወያኔ የደህንነት ተቍማት ስራ የሚደራጁ ክንፎች በነማን እንደሚመሩ በነማን በጀት እንደሚጦዙ የኣጀንዳዎቹ መነሻዎች እነማን እንደሆኑ ምስክር ኣያስፈልግም።

ይህ ወያኔ ወለድ የሆነ የዘረኝነት በሽታ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ያህል ባይስፋፋም በዲያስፖራው ዘንድ ግን ስር የሰደደ በሽታ ከሆነ ሰነባብዋል።ጥቂት ዲያስፖራዎች በሃገር ቤት ያሉትን ወጣቶች በገንዘብ በመግዛት ዘረኝነትን ለማስፋፍት ሲጣጣሩ ይስተዋላል።ኣለም በኣንድ የእድገት መሰረት ላይ ለመመስረት በቴክኖሎጂ እና ትልልቅ ግኝቶች ላይ ባተኮረበት በዚህ ዘመን ጥቂቶች የሚፈጥሩት የድህረገጽ የዘረኝነት ወከባ አጅግ ኣሳዛኝ እና ኣስደንጋኝ ነው።ሕወሓት አነዚህን በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍሎ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው።በዲያስፖራው ጉያ ስር ተወኅቀው የወያኔን የዘረኝነት ኣጀንዳ ለመፈጸው አያወቁም ሳያውቁ ደፋ ቀና የሚሉ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሊያስቡ ይገባቸዋል።የማያዘልቅ ጸሎት ለቅጽፈት መሆኑን ተረድተው ከዘረኝነት በሽታ ሊላቀቁ ይገባቸዋል። በጥቅም ላይ የተመሰረተ ወጣቱ ያላመነበት የዘረኝነት መስፋፋት ውጤቱ በእኩይ ተግባር ላይ ለተሰማሩ ዘረኞች ኣደጋ ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

17 Comments on “ሕወሓት በፈጠራና በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም በጎሳ ፖለቲካ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው።”

  1. what are you talking about? – Anything in the diaspora is reflected in Paltalk rooms

    The only new paltalk room that emerged recently is “United Ethiopian ende zega” room – majority of supporters are from oromo ethnic groups.

    old Eprdf supporter room -diaspora room is crumbling… they have lost it….so why do you talk about Bete amara and tigraway???

    your article is confused and confusing.

    don’t scare people

    whatever is happening in ethiopia today is the result of whatever has been going on in ethiopia.

    The real struggle is there. Focus on that!

  2. The author should have given examples and names. It was a big mistake not to do that. So the article is “job half done”.

    Tribalism must be strictly rejected.

    Use of tribalist language (killil names, tribal names, TPLF names for places like Nazret, Debre Zeyit and Alemaya) should be strictly banned.

    The struggle against TPLF should be viewed as a struggle against a ferenji puppet, as part of the global struggle blacks versus ferenji and as a struggle to defend the existence of the historical country Ethiopia that TPLF and its masters attempt to destroy.
    In the past millions of Ethiopians have sacrified their lives and limbs to defend Ethiopia, their sacrifices should not be in vain.

    Former USA foreign minister Henry Kissinger and leading USA politician calls to break up “dissenting” countries.

    ” Kissinger has commented previously on the desirability of breaking up dissenting nations into smaller fragments, after which the emerging chaos may facilitate their introduction into a global order. This, in essence, is the rule of divide and conquer. These recent comments by Kissinger are in step with previous statements in which he promulgates the idea that social upheaval and mass civil unrest are to be used as a means of merging nations (including, by the way, the United States) into an “international system”. ”

  3. Every body has the right to support or to oppose any party in a peaceful way your problem you need everybody to support you that’s your right u have to respect also your opposition party.we don’t support you EPRDF

  4. Le arba amet le and lafta sayaqom
    Telatachn yetgrai woyanie eñan
    eyegedele ena agerachn eyaTefat
    ygeñal.
    Lemedan and bcha mrcha alen.
    Esum: woyanien megdel new.
    Jegnoch, beyalenbet beyegiziew
    wedaj meslen bemeqreb, lemanm
    sanasawq bedbq yetgrai
    woyanien engdel.
    woyaniewochn sngelachew
    yeterefut sisheshu weym siyalqu
    bcha neTanet ygeñal.

    MiTeqmun mesariyana sltoch.
    Tyt, bomb, slu mesariya (goradie,
    seyf, meTrebiya, bilawa, Tor,
    ankasie), bebox, qomeT, dngay,
    merz, maqaTel, maneq, mafen,
    wede gedel, gudguad megefter,
    kewha masmeT, bebeshta
    maslekef etc new.
    Zm blen mawelawel lemaleq new.
    Saichersun qedmen megdel alebn.

  5. ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ግዛታቸውን በአንቀፅ 39 ያሥጠብቁ የጋንቤላና የሲዳማ ህዝቦች ንቅናቄ በወያኔ የእጅ አዙር የመሬት ግዢ ከኛው ካዝና ተበድሮ የሀሰት ሰነድ በመፈራረም ከ500ኪ.ሜ በላይ የሆነ የእርሻ መሬት ሽጦ ገቢውን ለትግራይ ሪፐብሊክ ለማዋል እየተደረገ ያለው እንቅሥቃሴዎች ለመግታት ኦሮምያ የጀመረው ጅማሬ ከዚህ ጥቃት ለመዳን ራሱን እየተከላከለ ይገኛል ጎበዝ ንቁ የሚታመን መንግሥት በጃንዌ ግብአተ መሬት አብቅቷል ሌባውን ወረበላ የወያኔን ሥርአት ከዝርፊያ ነጠቃ እንዲሁም መሬታችንን በእጃዙር ሽያጭ ለ99 አመት እዳ ውሥጥ እንዳንገባ ብርቱውን ጥንቃቄ ከተቃውሞ ጋር አሥቀጥሉ ይህ የሀገር ሀላፊነት ሁሉንም ክልል ያማከለ ንቅናቄ እንዲሆን ያሥፈልጋል።

    ሞት ለወያኔ

    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

  6. ትክክል ወድሜ ኦሮሞ ትክክል መንገድ ጀምሯል
    ልንቀላቅለው ይገባል ወሳኝ ወቅት ነው!

  7. ሁሉም ክልል ወሰኑን ከወያኔ በጃዙር ወረራ ይጠብቅ በልማት ሥም ክልሎች ምንነታቸውን በመንደር ማሰባሰብ (ሰፈራ) ደርግ ጅምሬት የነበረውን እቅድ ለተንኮል ህዝቡ መሬቱን ለማሥለቀቅ እየተደረገ ያለውን እንቅሥቃሴ መግታትና ዳርድንበራችንን እናሥከብር እንጠብቅ አንቀፅ 39 አሁን ላጋጠመን ወረራ ወሳኝ መፍትሄ ሰጭና ወያኔን ወደመጣበት ጉድጓድ ለመቅበር ትልቅ ፋይዳ ይሰጠናል።

  8. Nektenal awra breaking news alwayas the same old story keep talking cry u don’t get nothing Semayawi and ginbot7 are deid week opposition is good for TPLF

  9. የካቲት 11 ፣ 1967 ታጋዮቹ ደደቢት በረሃ እንደገቡና የትጥቅ ትግሉ እንደተጀመረ፣ ግንባር ቀደም ተግባራቸው ሶስት ነጥቦች ላይ ነበር ትኩረት ይሰጠው። 1ኛ፣ የድርጅቱን ስም ማውጣት፣ 2 ኛ፣ ለወደፊቱ ለምትመሰረተው የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የግዛት ስፋት ከውጭ ሃገር፣ ሱዳን በሚገኘው መልኩ ማዘጋጀት፤ 3 ኛ፣ ፕሮግራሙን ለመጨረሻው ዝግጅቱ ታማኝ ታጋዮችን በማሰባሰብ ለሚከተሉት ሰዎች፣ ማለትም፣ አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር፣ ሥዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ስየ አብርሃ፣ ግደይ ዘርአጽዮን ወዘተ ሃላፊነቱ ተሰጠ። ለዚህ መሰናዶ ከበጌምድር ጠቅላይ ግዛት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ፣ ወልቃይት እንዲሁም ከወሎ ጠ / ግዛት፣ ራያና ቆቦ፣ ወልድያ፣ አላማጣ እስከ ላይኛው ሃሸንጌ ሃይቅ ድረስ በማጠቃለል የትግራይ መሬት ነው ተብሎ በመወሰን የፕሮግራሙን አቋም ደመደመ። ይህ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ በእጅ ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ወደ 30 ገጽ የሚሆን ተባዝቶ በመጽሓፍ መልክ ተጠርዞ በብዛት ተያዘ።በሃላፊነት የጻፉት አረጋዊ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሥዩም መስፍን፣ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየ ናቸው። በየቦታው እንዲሰራጭም ተደረገ።

  10. Woyane make crazy gondere neftegna ginbot7 what’s the problem Amara u finished ur time no body need u go to demonstration every day

  11. ስለ ኦሮሞ ጉዳይ ካልገባችሁ ታሪክን ረጋ ብላችሁ አንብቡ:: ዝም ብላችሁ ከመጻፋችሁ በፊት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኦሮሞን እንደ ጭራቅ (የሌለ አውሬ) ከመሳላችሁ በፊት ቆም ብላችሁ አስቡ:: ኦሮሞ ማለት ኦነግ: ኦሮሞ ማለት ገላሳ ዲልቦ: ኦሮሞ ማለት ጁሃር መሃመድ: ኦሮሞ ማለት ኦፒዲኦ: ወዘተ … አድርጋቸሁ መውሰድ ትልቅ ስህተት ይመስለኛል::

    አንጋፋው (ትልቁ) የኦሮሞ ልጅ በሆነው ቦረና ኑና ጠይቁ ቦረና = ሰው የሚል አባባል ታገኛላችሁ:: ኦሮሚያ ወይም ቦረና ውስጥ ለመኖር ሰው መሆን ብቻ በቂ መሆኑን ትረዳላችሁ:: ይህ የኦሮሞ (ቦረና) ምልከታ ነው::

    ስለዚህ የኦሮሞን ጉዳይ ወሳኝ ከኦነግ: ከገላሳ ዲልቦ: ከጁሃር መሃመድ: ከኦፒዲኦ ጋር በማያያዝ አታሳንሱት:: ኦሮሞ በሃገሪቱ ውስጥ በቁመቴ ልክ መብቴና ጥቅሜ አልተጠበቀልኝም ብሎ ቢነሳ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ ለምን ይወርድበታል:: ትግሉ ራሱን ከጭቆና ለማውጣት ስለሆነ ከተቻለ ማገዝ ካልሆነ ዝም ማለት ይገባል ባይ ነኝ:: በሃረሪቱ ያልተበደለ ስለሌለ ሁሉም በሚያዋጣው መንገድ መታገል እንጅ የኦሮሞን ትግል የግድ በዚህ ወይም በዚያ መንገድ ካልሆነ ብሎ ጥላሸት መቀባት የአዛዙን ስርዓት ማራዘም እንጅ ለማንም አይጠቅምም::

    በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ትግል ሌላውን ለመበደል ከሆነ የትም አይደርስም:: ትግሉ ህዝቡን ከዘረኛ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ከሆነ ደግሞ ሌሎችም በራሳቸው መንገድ በመታገል ነጻ ይውጡ:: ከዚያ በመቀጠል ሁላችንም እኩል መብታችን በተከበረባት ሃገር በአንድነት መኖር እንችላለን:: ስለዚህ ሁሉም በያለበት የራሱን የቤት ስራ ይስራ:: ኦሮሞው በራሱ ለብቻው ቢታገል እንደ ወንጀል ባይቆጠር መልካም ነው እላለሁኝ::

    የኦሮሞ ጉዳይ በተነሳ ቁጥር ኦነግንና ጁሃር መሃመድን ማጥላላት የኦሮሞን ጉዳይ ከማሳነስ አልፎ የኦሮሞን ጉዳይ ወሳኞች ኦነግና ጁሃር መሃመድ የሆኑ ያስመስላል:: ህዝቡ ሎጂካል አይደለም የሚል ያስመስላለና ህዝብ ደግሞ የሚበጀውን ያውቃል:: ቦረና = ሰው የሚለውን ብሂል ኦነግና ጁሃር አይደለም ኦሮሞን ያስተማሩት:: በመጨረሻም የኦሮሞን ትግል ለመደገፍ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ባይ ነኝ::

    ገመዳ ቦና – ከቦረና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*