በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በሌሎች ወገኖቻቸው መካከል ለማንደድ የሚሞክረውን እሳት በጋራ የማጥፋት ጥሪ!

#Ethiopia  #‎ShareEthioHarmony‬ ‪#‎EBCDocumentary‬ ‪#‎1460DaysOfPeacefulStruggle‬ ‪#‎EthioMuslims‬ #MinilikSalsawi
‹‹ማህበራዊ መስተጋብራችንን እንካፈል!››
መንግስት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በሌሎች ወገኖቻቸው መካከል ለማ

ንደድ የሚሞክረውን እሳት በጋራ የማጥፋት ጥሪ!
ከረቡእ ጥር 18 እስከ እሁድ ጥር 22/2008 የሚቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ
ረቡእ ጥር 18/2008

መንግስት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በሌላ ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻቸው መካከል እሳት ለመለኮስ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ካሁን ቀደም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በደህንነቶቹ የሚፈጽማቸውን ስውር ጥቃቶች ተገን በማድረግ የመቃቃር ስሜት ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን የእምነት ቦታዎች ላይ ጥቃት በማድረስም ሴራ ለመጎንጎን ሞክሯል፡፡ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ደግሞ በሊባኖስ በእምነቶች መካከል ቀውስ በማስከተል የሚታወቀውን ‹‹አህባሽ›› የተባለ አንጃ በማምጣት ህዝበ ሙስሊሙን በግድ ለመጋት ሲሞክር ቆይቷል፡፡ ይህም አልሳካ በማለቱ እና ህዝበ ሙስሊሙ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን በጽናት በመቀጠሉ የተለያዩ ‹‹ጥናታዊ›› ፊልሞችን በመስራት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለአገሪቱ ስጋት እንደሆኑ ለማሳየት ሞክሯል፡፡ አልሐምዱሊላህ መላው ኢትዮጵያውያን ይህንን እኩይ ፕሮፓጋንዳ ጆሮ በመንፈግ ለዘመናት የኖረ መልካም የህዝብ ለህዝብ መስተጋብራችን በማይረባ ሴራ እንደማይናድ በተግባር አስመስክረዋል፡፡

ከሰሞኑ መንግስት በኢቲቪ ያቀረበው ‹‹የማንቂያ ደወል›› የተሰኘ ‹‹ጥናታዊ›› ፊልምም ቢሆን የዚሁ የመንግስት ክብሪት የመጫር ሙከራ አንዱ አካል መሆኑን ካሁን ቀደም የገለጽን ሲሆን ይህን እኩይ የመንግስት ሴራ ለማክሸፍ ሁላችንም መተጋገዝ እንደሚገባን ማስታወሳችንም አይዘነጋም፡፡ ይህንን የማድረጉ ሃላፊነት ደግሞ በመላው አገሩን በሚወድ ኢትዮጵያዊ ጫንቃ ላይ የወደቀ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ሳምንት ከምናደርጋቸው ሌሎች እንቅስቃሴዎች ጎን ለጎን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር የምንኗኗርባቸውን መልካም ማህበራዊ መሰረቶች እና ድንቅ መስተጋብሮች በማህበራዊ ሚዲያ የምንካፈልበት (ሼር የምንደራረግበት) አነስተኛ መርሃ ግብር ይኖረናል፡፡

ከዛሬ ረቡእ ጥር 18 ጀምሮ እስከ እሁድ ጥር 22/2008 በሚቆየው በዚሁ ዘመቻችን በእለት ተእለት ኑሯችን በጎረቤታችን፣ በሰፈራችን እና በስራ ቦታችን ከሚገኙ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወንድም እና እህቶቻችን ጋር ያለንን መልካም ቅርርብ እና መተሳሰብ የሚያሳዩ ገጠመኞቻችንን፣ አኗኗራችንን እና ትብብራችንን በቻልነው ያክል በጽሁፍ (ወይም በሌላ አመቺ በሆነ መንገድ ሁሉ) በማስፈር #ShareEthioHarmony የሚለውን ሐሽታግ በመጠቀም በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻችን ሼር እናደርጋለን፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሃይማኖታዊ ማንነታችንን ሳንለቅ እና እሴቶቻችንን ሳናፈርስ ከሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ጋር መልካም ጉርብትና እና ወዳጅነት መስርተን የምንኖር መሆኑን፣ ይህም በመንግስት እኩይ ሴራ ሊናድ የማይችል መለያ ባህሪያችን መሆኑን በተግባር እናስመሰክራለን፡፡ ‹‹ሙስሊሞች መጡልህ!›› እያለ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ወገኖቻችንን ሊያስፈራራ የሚሞክረውን መንግስታዊ ሴራ እና የዶኩመንታሪ ፊልም ጋጋታ የማንቀበለው መሆኑን በተግባር እናሳያለን፡፡ ሌሎች ወገኖቻችንም ትስስራችንን እና መስተጋብራችንን በምንካፈልበት በዚህ ታላቅ ሳምንታዊ ድግስ በመሳተፍ ድምቀት ያለውን መልካም ጉርብትናችንን ለዓለም እናሳይ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናደርጋለን፡፡

አዎን! የመንግስት እኩይ ሴራዎች በየጊዜው ሊጭሩ የሚሞክሩትን አገር አጥፊ ሰደድ እሳት እንደወንዝ በሚፈስሰው መልካም ጉርብትናችን እና ወገናዊ ትስስራችን ለማጥፋት ጊዜው አሁን ነው! ወደጥርጣሬ እና በዓይነ ቁራኛ ወደመተያየት በመግፋት ርካሽ ፖለቲካዊ ጥቅም ለማትረፍ የከጀለውን መንግስት አሳፍሮ መመለስ የሚኖርብን ዛሬ ነው! እኛ ኢትዮጵያውያን መካከላችን ለመግባት ለሚፈልጉ እኩያን ቀዳዳ የማያስከፍት መልካም አኗኗር እና ወገናዊ ህብር እንዳለን የምናስመሰክረው ዛሬ ነው! በዚህ ሳምንት መልካም ጉርብትናችንን ለዓለም ይፋ እናደርጋለን…. እጃችሁ ከምን???

‹‹ማህበራዊ መስተጋብራችንን እንካፈል!››
‹‹ትግላችን አብሮነትን የሚያጎለብት፣ የውድ አገራችንን ሰላም እና ደህንነት ታሳቢ ያደረገ ነው!››
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!

Like ☑ Comment ☑ Share ☑

ድምፃችን ይሰማ's photo.

23 Comments on “በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በሌሎች ወገኖቻቸው መካከል ለማንደድ የሚሞክረውን እሳት በጋራ የማጥፋት ጥሪ!”

  1. Mn-netu yaltaweqe tgl wois siera? Ere lemehonu mndn new chgrachuh? Mn felgachuh tekelkelachuh?
    Wois wahhabism anqebelm aluachuh ye ethiopia islamoch?

  2. የሚገርመው ወያኔ ዳግም መካ ብሎ በራሡ ሊሰይም ያሠበውን የመቀሌውን አል ነጋሽ መሥኪድን ትግራይን በመገንጠል ከአለም እንደሣውዲ የቪዛ ገቢና ቱሪዝምን ያለመ ድብቅ አጀንዳም እንዳለ ልናውቅ ይገባናል።

  3. እሥላምና ክርሥቲያንን እንዲለያዩ እየጣረ ያለውን ወያኔ ልናሥወግድ ይገባል።

  4. Attention, wahhabi islam is a recent terrorist islamic sect, founded by saudi wahhabi who became arabia king and he called the country saud arabia in 1932. This sect is the saudi kings’ religion. But many ancient islamic sects (from sunni, shia, hamadya) donot accept wahhabi islam because it forces to convert everyone to wahhabi islam and it (wahabism) rejects many of the traditional islamic practices. The saudi kings with their oil money try to spread wahabism by force using alqaida, isis, buko haram etc.

  5. One of the good memories from my childhood is the close-knit friendship i had with Yimer, who happened to be a muslim. We went to school together, played together and grew up together in a relatively large conservative Christian community. We used to sneak in into each other house to eat together. Our parents did everything together, be it griefing, idir, iqub, lending & borrow stuff except, eating. I don’t remember any occasion when that happened. In fact, both Yimer & I weren’t allowed to share food but, who cares, we both had our ways to violate this foolish taboo. I never forget the annual festival that used to be organized and set up by the scouting association in the school premises. Dignitaries and parents used to be invited. There were speeches, plenty of food, shows like acrobat, music, poems etc. Even though food for muslim parents and their kids was set up in a separate tent, I was always curious and never missed to surreptitiously enter that tent and taste my friend’s food and so did he. This is the Muslim-Christian relationship that is etched into my mind & heart forever. It is sad to realize today that we failed to nurture those connections and became succumbed to a devisive temptations. In this forum alone, it is not unusual to see spinning and exaggeration of our differences as a means to create a wedge among religions and ethnic lines. In my time, it was the other way around. Our common values and shared intetests shaped our relationships. Cheers!

  6. Ye ethiopia orthodox beqrbu, ahmed negash yembal ethiopia negso ayawqm alech. Be ziyan zemen mohamed islmna siyasfafa ye aksum ngusoch krstian neberu.
    Ke meka wede ethiopia yemetu ye mohamed teketayochn yeteqebelachew ena yaqoyachew ye afaru sultan (ngus) ahmed neber, yemejemeriya smu ashishi neber.

  7. Lemeketle yemimokerut selit bemulu
    ye ISIS ayenet neaw ahun Christianu
    ayinun geltoal yfelekewun betmoker
    afetetin inayachehoalin .
    yante genzib kitehin teregbt genzeb
    amelaki hulla .

  8. The fabricated name – negash mesgid/mosque is false. It is a false woyane’s promotion to make tgrai a muslim tourist center.
    The rality is that afar and harar were the first ethiopians who knew and converted to islam.
    But al negash (najasi) was not a tgrai aksumite christian king. He was a leader or ngus of afar.

  9. Habash islam sect has a full right to practice its religion. It is a very modernized islam which doesnot support forced conversion to islam and it supports isolation of the the state and religion. But dmtachn ysema opposes habesh islam because dmtachn ysema are wahabi sect which doesnot allow any religion except wahabism.

  10. Juhar Mohamed he stands for Muslims,he doesn’t care of Christians . You are lier,many years ago Christmas and Muslims the live together and cope rates every day social activities,now day you support JUHAR Mohamed activities . TPLF tell us the truth. To be honest I don’t like Juhar Mohamed 99% messages.

  11. እኔ እጅግ የበዙ ሙስሊም ጓደኞች አሉኝ።በሚገርም ሁኔታ አንዳቸውም ጋር ተጋጭተን አናቅም። ቤተሰቦቸም ሙስሊሞች ጨዋዎች፣ሰው አክባሪዎች፣ከሌብነትና ከስካር የጸዱ እንደሆኑ በተደጋጋሚ ነግረውኛል።እኔ አሁንም ቢሆን ስለ ሙስሊሞች መጥፎነት ከቲቪ ከመስማት በስተቀር በመሬት ላይ ይህ ነው የሚባል መጥፎ ሙስሊም አላጋጠመኝም።አሁን ቢሆን ለሙስሊሞቹም ሆነ ለከርስቲያኖቹ እንድሁም የትኛውንም ሃይማኖት ላማይከተሉ የምመክረው መንግስት በመገናኛ ብዙሃን የሚለቀውን ዘጋቢ ፊልም ብቻ እንደ እውነት ከመቁጠር በመሬት ላይ ያለውን እውነታ መመልከትና አብረን ተያይዘን እና ተቻችለን እንድንኖር ነው።አጥፊዎች እዛም እዚህም ሊኖሩ ይችላሉ።ነገርግን እነኝህን እጅግ ባጣም ውሱን የሆኑ ግለሰቦች በመመልከት ብዙሃኑን በነዚህ ልክ መመልከቱ ተገቢ አደለም።ልብ እንበል፦ መንግስት በመንግስት ይተካል ነገር ግን አገር እንዴ አገር፣ህዝብ እንደ ህዝብ ቀጣይ ናቸው። Please Ethiopians let’s strengthen our social bond.

  12. እርስ በርሳችን እንድንጋጭ ሌት ተቀን እየጣረ ያለው ይሄ ሰውበላ ማፊያ መንግስት እንጅ እኛማ ተከባብሮ በአንድነት በመኖር ለአለም ምሳሌ አደለንም እነዴ።እስቲ ቆም ብለን እናስብ ይሄ መንግስት ነኝ ባይ በጎሳ እና በሃይማኖት ተከፋፍለን እንድንጫረስ የማይፈነቅለው ድንጋይ አለ እንዴ።ኧረ ጎበዝ እባካችሁን ችግራችን ለይተን እንወቅ!እውነት እንነጋገር ከተባለ ለሃገር ስጋት የሆነ ከዚህ መንግስት በላይ ማን አለ? ኧረ እባካችሁ እውነታውን አንደብቅ። በቃ የእኛ ጥላታችን አንድ እና አንድ ብቻ ነው፦ወያኔ። በበበበበበበበበበበበ…………………….ቃን!!!!!!!

  13. Please be ware
    You are absolutely
    Un thurstworty killers who in the
    believes you Jawar + Dimtsachin Yisema = Radical Jihhadist

  14. በአካባቢያችን አንድ መስጊድ ሲመረቅ የቤተ ክህነት ከፍተኛ ሹማምንቶች ተጋብዘው በምረቃው ላይ በመገኘት የሙስሊም ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው የደስታ ተካፋይ መሆናቸውን አስታውሳለሁ ። እኛ አንድ ነን።
    የሚለየን አንዳንች ነገር የለም።

  15. Ageren indetigoda ketelat gar kenina
    lelit iyedolete ande nin yilale .
    tadia ye abay werie sisema lemin
    tedenegitaleh agerun yiyazchehut
    inante melesachehu yetelat banda
    hunachehu yaderegachehut betarik
    temezgeboal kahadi hulla demo ande
    nene yilal .

  16. Sammy don’t you know lying is the
    corner stone of their thought
    or doctrine ? This indicates their
    level of hopelessness .

  17. የዋሁ ሚሊሻ በሥጋህና በነፍሥህ ወያኔ እየነገደበት ያለውን በአፍሪካ ህብረት ሰላም አሥከባሪነት ሽፋን ከፍተኛ የዶላር ጥማታቸውን በደምህ እያወራረዱ በሱማሌ በሱዳን በሩዋንዳ ሥጋህን ለአሞራ ካሣውን ለኪሣቸው በማረግ እንዲሁም በአማራ በቤንሻንጉል ኦሮምያ የሚገኙ መርቀው የላኩህን ወገኖች በቀይ ሽብር እየረፈረፋቸው ይገኛሉ የኛ ጠላታችን ኣግአዚ መራሹ ወያኔ ነው በዘር በጎሣ የተዋቀረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአሁን በሀላ ምንም አይነት ሀገራዊ ሥሜት የሌለው መሆኑን እድታውቅ በቅርቡ ለሚፈጠረውም ወያኔን ከሥልጣን የማሥወገድ ትግል አፈሙዝህን ህዝብ ላይ ሣይሆን ወደ ዘረኛው ወያኔ እንደምታዞር ፍንጮችን አሣይተህናል ዛሬ ሀገራችን ዙሪያዋ በመንደር ማሰባሰብ ወይም ስፈራ ዳር ድንበሩን ሲጠብቅ የነበረውን አርሶ አደር ከቀዩ በማፈናቀል መሬቱን ድንበሩ እየተሸጠበት ይገኛል ታድያ ይህ ነው የአባቶችህ አደራ? መልካም ይህ እውነታ ተገንዝበህ የሀገር አድን ታጋዮችህን እንድቀላቀል ያሥፈልጋል ይህን አጠር ያለ ግንዛቤ ሁሉም ኢትዬጵያዊ ሼር በማረግ ለወገኑ እንዲያካፍል ቅሥቀሣ እንዲያረግ የዜግነት ሀላፊነት ሊኖረን ይገባል ባንዳውን ወያኔ በጋራ እናሥወግድ።

  18. Sadik Ahemmed ena Messay Mekonnin

    ande ayete nachew iwketu yelachewm

    gin indemiyawek seaw alen alen ymilu

    ayenetoch Sadik yetaweke Ye telatochachin

    telalaki mehonu yetawekal beteley ke

    ke Saudi ymilakelet ginzib igeg bizu neaw .

    Akerarinet be Ethiopia ye hilm ingera neaw .

    dekem bileh neaw . yalmokerkew yelem kewendemih

    Jihadistu Jawar Maincha .

  19. ከዚህ በላይ በክርስቲየን ስም የጻፋችሁ ሁላችሁም እስላሞች ናችሁ እሺ እንሞኝላችሁ እስላም ደግ ሰብአዊ ሰዉ የማያርድ ይሁን በየቦታዉ የተቃጠሉት የታረዱትን ክርስቲያኖች እና ቤተ ክርስቲያን ማን አቃጠለ ማን አረደ? ተዉ እባካችሁ ዝምታ ይሻላል ኢዝላሚክ ኦሮሚያንስ የት ታደርሱት ነዉ እሱም መልአክ ነዉ? የጁዋር ሜንጫስ እሱም ሺቶ ነዉ? ጠቅላላ የሚጻፈዉ ሁሉ ኦሮሚያ ኢስላሚያ ብቻ ሆነ እኮ ለድር ገጾችም ከሳዉዲ/ኢጂብት ገንዘብ ይበጠሳል እንዴ ? የሰራችሁት ግፍ እኮ ገና ትላንት ነዉ። ወያኔ ወያኔ የምትለዉን አብሮ ጠፍጥፎ የሰራልህ እኮ ኦለፍ እና ኢዝላሚክ ኦሮሚያ እነ በያን ሌንጮ /ዲማ እኮ ናቸዉ ተዉ አትጻፉ ሰዉ አታወናብዱ ሁላችሁም አንድ ናችሁ። እናንተ ዝም ሳትሉ እኛም ዝም አንልም። በዚህ ትያትር ዋናዉ ተዋንያን እራሳቸዉ ሐጂ ናጂብ ይስቁብናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*