በኣዋሳ የመሬት መንቀጥቀጡ ኣሰጋን ያሉ ተማሪዎች ላይ ተኩስ ተከፈተ።

በኣዋሳ የመሬት መንቀጥቀጡ ኣሰጋን ያሉ ተማሪዎች ላይ ተኩስ ተከፈተ።

የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው እንዲዘጋ እና ወደየቤታቸው እንዲበተኑ ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበረ። ፌደራል ፓሊስ እንደተለመደው በዱላ እና ወደ ሰማይ በመተኮስ ሰልፉን ለመበተን የሞከረ ቢሆንም አልተሳካም። ሰልፉን ተከትሎም የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከመሸ ወደ ግቢው በመምጣት ትምህርት ለ፩፭ ቀን መዘጋቱን እና ተማሪዎች ወደየቤታቸው መሄድ እንደሚችሉ ገልፆላቸዋል።

መንግስት በሚዲያ በህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ቢልም ከትናንት በስቲያ ብሎክ ፴፮ በመሬት መንቀጥቀጡ ወቅት በተፈጠረ የኤሌክትሪክ መስመር ችግር በእሳት ሲያያዝ ህይወቷን ለማትረፍ ከ፫ኛ ፎቅ የዘለለች ተማሪ እንዲሁም የመሬት መንቀጥቀጡ በተከሰተ የመጀመሪያ ቀን የላይብረሪው ኮርኒስ ከወደቀባቸው እና በህክምና ይረዱ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል የጋምቤላ ክልል ተወላጅ የሆነ ተማሪ መሞታቸውን ተማሪዎቹ ይናገራሉ።

10 Comments on “በኣዋሳ የመሬት መንቀጥቀጡ ኣሰጋን ያሉ ተማሪዎች ላይ ተኩስ ተከፈተ።”

  1. Mereja or information and ewqet or knowledge betegbar lay kewale Teqami new.
    tgrai woyanien mawdemiya merejana ewqetochn betegbar bnawlachew yiTeqmunal, neTa yaweTunal.
    QoraT Jegna meriwech ena qoraT jegna tewagi Tor serawit Tru yewgiya slt azegajtew tgrai woyanien lemedemses betegbarawi wgiya biselefu tgrai woyanie ydemesesal.
    Tru Tere-woyanie yewgiya eqd beqoraT jegna drjt betegbar siwl bcha ye tgrai woyanie ydemesesal.

  2. እቺ የወያኔ ጥላቻ ህዝብን ከ ጤፍ አትቆጥርምና ራሣችሁን አድኑ

  3. ወያኔ የተፈጥሮን አደጋ የመቆጣጠር አቅምም እውቀትም የለውም ራሣችሁን አድኑ።

  4. ከእሁድ ጅምሮ እሥካሁን ንዝረቱ አላቆመም መንግሥት
    እያድበሰበሰ ነው በቂ ወገንን የመታደግያ የአደጋ ዝግጁነት
    አላሳየም ለህዝባችን ከፍተኛ ንቀት ያለው ህወሀት ወያኔ ይህን
    በታወቁ የውጭ ጂኦሎጂሥቶች እየሰጡት ያለውን ማሥጠንቀቅያ
    ወደጎን በመተው እንዲያውም የመሬት መናወጡ ከአዋሣ የተነሣ
    አይደለም ሥጋት አይግባችሁ እያለ ህዝብን ሊያሥጨርሥ መሆኑ
    ግልፅ ነው ይህ The great rift vally ታልቁ ሥምጥ ሸለቆ ከቀይ
    ባህር አንሥቶ ሞዛምቢክ የሚያቋርጥ ሲሆን በዚህ ክሥተት የመሬት
    መከፈል ሥለሚኖር ኢትዬጵያም በወያኔ ያጣችውን ወደብ ከ200
    ኪሎሜትሮች ባልበለጠ የተፈጥሮው ክሥተት እናገኘዋለን “ዝኮነ
    ኮይኑ” ትግራይ ሪፐብሊክ ምሥረታ በሀላ የባህር ወደብ ለማሣጣት
    የታሰበው እቅድም በእግዚያብሄር ሀይል እንዳኛለን ማለት ነው።

  5. ለመሆኑ ፡ ፀረ ፡ ልማት ሀይሎች ፡ ፀረዴሞክራሲ፡ ሀይሎች ፡ ለመሬት ፡ መንቀጥቀጡ ፡ አልተከሰሱም ???

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*