በወያኔው ፍርድ ቤት የቀረበው የሰማያዊ ፓርቲው ዮናታን ተስፋዬ ድጋሚ በቀጠሮ ወደ እስር ቤት ተመልሷል።

በወያኔው ፍርድ ቤት የቀረበው የሰማያዊ ፓርቲው ዮናታን ተስፋዬ ድጋሚ በቀጠሮ ወደ እስር ቤት ተመልሷል።

Negere Ethiopia's photo.

ፍ/ቤቱ ለ2ኛ ጊዜ 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጠ

*‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› ዮናታን ተስፋየ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ማዕከል በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለ2ኛ ጊዜ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡

ዛሬ ጥር 17/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት የቀረበው አቶ ዮናታን ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም በሚል የጠየቀበትን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለየካቲት 15/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋየ የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡

ፖሊስ በአቶ ዮናታን ላይ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ ‹‹የቴክኒክ መረጃዎችን መሰብሰብ ይቀረናል፤ ያልተያዙ ግብረ አበሮችንም አሉ›› የሚል ምክንያት ማቅረቡን የተጠርጣሪ ጠበቃ ገልጸዋል፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋየ በጠበቃ እና በቤተሰቦቹ እንዳይጎበኝ እንደተከለከለና ከታሰረበት ክፍል መታፈን የተነሳ የጤና እከል ቢገጥመውም ህክምና እንዳላገኘ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን አድምጦ በጠበቃውም ሆነ በቤተሰቦቹ እንዲጎበኝ እንዲፈቀድለትና ህክምናም እንዲያገኝ ትዕዛዝ መስጠቱን ከጠበቃው ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ዮናታን ከችሎት ሲወጣ በስፍራው ለነበሩት ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ያለውን ፍቅር ገልጾ ‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› በማለት ጮክ ብሎ ሲናገር ተደምጧል፡፡

5 Comments on “በወያኔው ፍርድ ቤት የቀረበው የሰማያዊ ፓርቲው ዮናታን ተስፋዬ ድጋሚ በቀጠሮ ወደ እስር ቤት ተመልሷል።”

  1. Le arba amet le and lafta sayaqom
    Telatachn yetgrai woyanie eñan
    eyegedele ena agerachn eyaTefat
    ygeñal.
    Lemedan and bcha mrcha alen.
    Esum: woyanien megdel new.
    Jegnoch, beyalenbet beyegiziew
    wedaj meslen bemeqreb, lemanm
    sanasawq bedbq yetgrai
    woyanien engdel.
    woyaniewochn sngelachew
    yeterefut sisheshu weym siyalqu
    bcha neTanet ygeñal.

    MiTeqmun mesariyana sltoch.
    Tyt, bomb, slu mesariya (goradie,
    seyf, meTrebiya, bilawa, Tor,
    ankasie), bebox, qomeT, dngay,
    merz, maqaTel, maneq, mafen,
    wede gedel, gudguad megefter,
    kewha masmeT, bebeshta
    maslekef etc new.
    Zm blen mawelawel lemaleq new.
    Saichersun qedmen megdel alebn.

  2. አዞህ ነፃነት አንድ ቀን ይመጣል ግን ድርጅትህ ደካማ ነው አንተ ስትገባ አባላችን ካልተፈታ ሁላችንንም እሰሩን ብለው ሁሉም ቢገቡ ያኔ ነፃነት በአጭር ጊዜ ይመጣል ! የወያኔ ትልቁ መድሃኒት አንድ መሆን ነው ስትባሉ እናንተ ፓለቲከኞች ጆሮ የላችሁም:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*