የመኢአድ አባል ገዳዮች ወደ ፍትሕ አልቀረቡም የሚል አቤቱታ ቀረበ

– የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ተጠርጣሪዎች መታሰራቸውን ገልጻል

(በኃይሌ ሙሉ)

 

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አባል ነበሩ የተባሉትን ግለሰብ ምሥራቅ ጎጃም ውስጥ ግንቦት 10 ቀን 2002 ዓ.ም. የገደሉ ግለሰቦች እስካሁን ድረስ ለፍትሕ አለመቅረባቸውን የሟች ቤተሰቦች ገለጹ፡፡ መኢአድ ጉዳዩ በኮሚቴ እየተጣራ ነው ብሏል፡፡