የሶዶ ወረዳ ነዋሪዎች በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠልንን መብት ተነፈግን አሉ
– ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ በፖሊስ ኃይል ተበተነ
(በታምሩ ጽጌ)በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ሥር የሚገኙ የ27 ቀበሌዎች ነዋሪዎች በሕገ መንግሥቱ የተፈቀደልንን የመሰብሰብ፣ የመደራጀት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የመቃወምና የመደገፍ መብቶቻቸውን በወረዳውና በዞኑ ኃላፊዎች መነፈጋቸውን በተለይ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡