ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በቀጣዩቹ አምስት ዓመታት የልማት ዕቅድ ዕርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ገለጹ
(በኃይሌ ሙሉ)
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግስት በቀጣዩቹ አምስት ዓመታት የያዘው የልማትና የዕድገት ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል ብሎ በእርግጠኛነት መናገር እንደማይቻል ገለጹ፡፡
አቶ መለስ ዛሬ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፣ መንግስት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በየአመቱ 15 በመቶ እድገት አስመዘግባለሁ ብሎ የያዘው ዕቅድ በመንግስትና በሌሎች አካላት ከፍተኛ ጥረት ካልተደረገ በስተቀር ተግባራዊ ይሆናል ብሎ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡