ከአምስት ዓመቱ ዕቅድ ውይይት በኋላ የባለሥልጣናት ግምገማ ይጀመራል
(በውድነህ ዘነበ)
ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በአገሪቱ ተግባራዊ በሚደረገው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ሕዝቡን በማወያየት ሥራ የተጠመዱት የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የማወያየቱትን ሥራ ከጨረሱ በኋላ የፓርቲ ግምገማ እንደሚጀምሩ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የሚፈልጉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡