ኢትዮጵያ ሆቴል ያረፉ እንግዳ ባልታወቁ ሰዎች ተዘረፉ

– ጉዳዩን ፖሊስ እየመረመረው ነው

(በታምሩ ጽጌ)

በኢትዮጵያ ቀደምት ከሆኑት የመንግሥት ሆቴሎች መካከል አንዱ የሆነውና እስካሁንም ድረስ መንግሥት በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ኢትዮጵያ ሆቴል ውስጥ አልጋ ይዘው ከአንድ ወር በላይ ተቀምጠው የሚገኙ አንድ ፕሮፌሰርና ሌላ ማንነታቸው ያልታወቁ አንድ ግለሰብ ሐምሌ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. የያዙትን ንብረት መዘረፋቸውን በተለይ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡