ኤግዚም ባንክ ለአየር መንገድ የ1.6 ቢሊዮን ዶላር ዋስትና ሰጠ

(በቃለየሱስ በቀለ)

የአሜሪካው ኤክስፖርትና ኢምፖርት (ኤግዚም) ባንክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ለሚገዛቸው 10 ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች፣ ለአምስት ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችና ለጄነራል ኤሌክትሪክ ኩባንያ ሰራሽ የአውሮፕላን ሞተሮች መለዋወጫ መግዣ የሚውል የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የብድር ዋስትና ሰጠ፡፡