የግንቦት 7 ተከሳሾች ለመጨረሻ ውሳኔ ተቀጠሩ
(በታምሩ ጽጌ)
በህቡዕ በመሰባሰብ፣ መንግሥትንና ሕገ መንግሥቱን በኃይልና በአመጽ ለመጣል በመስማማት ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል በሚል በሞት፣ በዕድሜ ልክ፣ በአሥር ዓመት እሥራት ቅጣትና በነፃ የተሰናበቱት የግንቦት 7 ፍርደኞችና ዓቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ባለፈው ዓርብ ለመጨረሻ ውሳኔ ለጥቅምት 23 ቀን 2003 ዓ.ም. ተቀጠረ፡፡