የአዲስ አበባ ፖሊስ አባሏ በፌዴራል ፖሊስ አባል ተደበደቡ

(በታምሩ ጽጌ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አባል የሆኑት ዋና ሳጅን ስንታየሁ አረጋ፣ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሐምሌ 28 ቀን 2002 ዓ.ም. ከመኖሪያ ቤታቸው ድረስ ሄዶ ባደረሰባቸው ድብደባ፣ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው በተለይ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡