ሱዳን ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ቤንዚን አቅራቢ ሆነች
(በኃያል ዓለማየሁ)
የኢትዮጵያና የሱዳን መንግሥት ከወር በፊት ባደረጉት ስምምነት መሠረት ሱዳን ብቸኛዋ የኢትዮጵያ የቤንዚን ፍጆታ አቅራቢ ሆነች፡፡ ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያን 80 በመቶ የቤንዚን ፍጆታ ሲያቀርብ የቆየው ባለቤትነቱ የሱዳን መንግሥት የሆነው ሱዳን ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን፣ በስምምነቱ መሠረት ከመስከረም 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያን የቤንዚን ፍጆታ ማቅረብ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ይግዛው መኮንን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡