በመንገድ ምልክቶች ላይ ባለሥልጣን መሥርያ ቤቶቹ እየተወዛገቡ ነው
‹‹የመንገዶችን ምልክት ማድረግ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ሥራ ነው›› የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን
‹‹ምልክት የመትከል ኃላፊነት ያለበት የመንገዶች ባለሥልጣን ነው›› የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን
(በብርቱካን ፈንታ)
በቅርብ ጊዜ በተገነባው ከጎተራ እስከ ሳሪስ የአስፋልት መንገድ ላይ ምንም አይነት ምልክት ባለመቀመጡና በነዋሪዎች ዘንድ እያስከተለ ባለው አደጋ ምክንያት፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣንና የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ምልክት ማን ምልክት ያድርግ በሚለው ላይ እየተወዛገቡ ነው፡፡