በሰሜናዊ ሶማልያ የምትገኘው ሶማሊላንድ ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ በሱስ አስያዥ ዕጽ እና በወንጀል አንጻር በሚታገለው የተመድ መስሪያ ቤት ርዳታ በአንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ዩሮ ወጪ በርዕሰ ከተማ ሀርጌሳ የተሰራ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት ወህኒ ቤት ከፈተች።

ማየት የተሳነው የ26 ዓመት ወጣት ስደተኛ ነው። ገና ዕውቅና ባላገኘችው ግን ራሷን ሐገር ብላ በሰየመችው ጎረቤት ሶማሊላንድ ውስጥ በስደት ሲባትት አራት ዓመታትን አስቆጥሯል። ታዲያ ተስፋ ያጣች መንፈሱን ዘወትር በብዕሩ ጠብታ በሚያፈልቃቸው የግጥም ሰንኞቹ ለማፅናናት ይሞክራል። በስደት ዓለም መከራ፦ ከአብራኩ የተከፈሉት …

ማየት የተሳነው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ በሶማሊላንድ Read more »

ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ሂዉማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ መንግስት ካለ ክስ በጅምላ ያሰራቸዉን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እንዲለቅ ጠይቋል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ ሎንዶን የሚገኘዉ የድርጅቱ ጽህፈት ቤት የአፍሪቃ ጉዳይ ተወካይ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ ረገድ ጥሩ ስም እንደሌለዉ በመግለፅ …

ሂዉማን ራይትስ ዎች እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቀ Read more »

የዶቸ ቬለ የፕሮግራሞች የበላይ ሐላፊ ክርስቲያን ግራምሽ የኢትዮጵያ መንግሥት የዶቸ ቬለ ሥርጭት ከእወካ ነፃ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል። የዶቼ ቬለ የአማርኛ ሥርጭት ባለፉት ጥቂት ቀናት ዉስጥ አልፎ አልፎ ግን ሆን ተብሎ እየታፈነ ወይም ጃም እየተደረገ መሆኑንን የጣቢያዉ የቴክኒክ ባለሙያዎች አስታወቁ።የሥርጭቱን አድማስና …

የዶቼ ቬለ መታፈን በኢትዮጵያ Read more »

የብርሀንና ሠላም ማተሚያ ከትናንትና ጀምሮ በጋዜጦች የማተሚያ ዋጋ ላይ እስከ ሀምሳ በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ማድረጉ ተገለፀ። ጭማሪውን ተከትሎ የጋዜጣ አሳታሚዎች በማማረር ላይ ናቸው። ድርጊቱ በተለይ የግሉን ፕሬስ መቀጠል ወደማይችልበት ሁኔታ ውስጥ እየከተተው እንደሆነ የጋዜጣ አሳታሚዎቹ ጠቅሰዋል።

የዛሬ አስራ አምስት ቀን በወጣቶች መድረክ ዝግጅታችን የሰሐራ በረሀን ጨምሮ ሱዳን፣ ሊቢያና ቱኒዝያ ውስጥ መከራ ፍዳውን ሲበላ የነበረ አንድ ወጣት ማቅረባችን ይታወሳል። ይህን ዝግጅት ከተከታተሉ አድማጮቻችን መካከል በፅሁፍም በስልክም መልዕክታቸውን ያደረሱን አድማጮች በተለይ ሊቢያ ውስጥ ኢትዮጵያውያኑ እየደረሰባቸው ያለውን መከራ

በሊቢያ የመንግስቱ ጦር ኃይላት በሀገራቸው የተቃዋሙ ቡድኖች አንጻር ግዙፍ የኃይል ርምጃ ከወሰዱ በኋላ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሊቢያ ላይ የበረራ ዕገዳ ማዕቀብ በመጣል ካለፈው ሳምንት ወዲህ ይህችኑ ሀገር በመደብደብ ላይ ይገኛል።

አንካራ ላይ በሚንስትሮች፥ ብራስልስ ደግሞ በአምባሳደሮች ደረጃ ዉይይቱ በሚደረግበት መሐል የዩናይትድ ስቴትስዋ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ወይዘሮ ሒላሪ ክሊንተን የፈረንሳይ፥የብሪታንያና የቱርክ መሪዎች እንዲስማሙ በስልክ አግባብተዋቸዉ ነበር

የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ ለቀየሰዉ የትምሕርት መርሕ ማስፈፀሚያ የተዘጋጁ የማስመተማሪያ መፅሐፍት በወቅቱ ለየትምሕርት ቤቶቹ አለመድረስ የመማር ማስተማሩን ሒደት እንዳጎለዉ አንዳድ የደቡብ ኢትዮጵያ ተማሪዎችና አስተማሪዎች አስታወቁ።

የተባበሩት መንግስታት በሊቢያ ላይ የበረራ ዕገዳ እንዲከበር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የተከፋፈል አቓም መያዛቸው ታውቓል። በሊቢያው መሪ ሙዓማር ጋዳፊ ላይ ጥቃት አንዲጀመር ፈረንሳይ በዋና አቀንቃኝነት ተንቀሳቅሳለች። ጀርመን ግን በሊቢያ ላይ የተጀመረውን ርምጃ ተቃውማለች።

የምዕራባዉያን መንግስታት እና የአረብ ሊጋዉ ትናንት ፓሪስ ላይ የሞአመር ጋዳፊን ሃይል ለማምከን ከተስማ በኳላ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በተለይ የፈረንሳይ የእንግሊዝ እና የዪናይትስ ስቴትስ የጦር ሃይሎች የኮነሪል ጋዳፊን ቁልፍ የጦር ሰፈሮች እየደበደቡ ነዉ።

በምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ኮት ዲቯር ባለፈው ህዳር ወር ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊው ምርጫ በኋላ በአሸናፊው እና በተሸናፊው ፕሬዚደንቶች አላሳ ዋታራ እና ሎውሮ ባግቦ ደጋፊዎች መካከል የቀጠለው ግጭት አሁን ሀገሪቱን ወደርስበርሱ ጦርነት እያመራት ይገኛል።

ኦህኮ አባላቶቹ እየታሰሩ እንደሆነ ይገልጻል። ሰላማዊ ትግሉን አላቋርጥም ይላል ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያ መስተዳድር በተለያዩ ጊዜያት እስካሁን ከ102 በላይ የሚሆኑ ቢሮዎቹ በኢህአዴግ መንግሥት እንደተዘጉበት የገለጠው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ፣ ከዚህ ቀደም ያጋጥሙት ከነበሩት መሰናክሎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቀድሞ የፓርላማ አባላት የነበሩና …

የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አባላቶቹ እየታሰሩ እንደሆነ ገለጸ Read more »

የምስር የሽሮ ወጥ፣ የተልባ የሱፍ ፍትፍት፣ የሽንብራ አሳዉ፣ እልበት ስልጆ፣ አዚፋ፣ ቡጥጫ፣ ቃርያ ስንግ፣ ብቻ ስጋን ወተትን እና የወተት ተዋጽኦን ሳይጨምር ጥሩ ጣዕም ያለዉ ለጤና በጣም ተስማሚ የሆነ ምግብ በአገራችን በጾም ወራት በተለይ በከተማዉ አካባቢ ይገኛል።

የዓለም መገናኛ ብዙኀን ፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ፤ ሰሜን ምሥራቅ ጃፓንን ክፉኛ የናጠውንና እጅግ ኃይለኛ የውቅያኖስ ማዕበል አስነስቶም በህዝብ ላይ ብርቱ ጥፋት በንብረት ላይም ሰፊ ውድመት ስላደረሰው የተፈጥሮ አደጋ በሰፊው ሲያትቱ ሰንብተዋል።

ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር እና ዶክተር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ህዝቦች ኮንግረስ መሪና የኢትዮጵያ የፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አባል በርሊን ውስጥ ዛሬ ከጀርመን ባለሥልጣናት ጋር እየተነጋገሩ ነው

ቻይና የኑክሊየር ተቓሟን የበለጠ እንደምታስፋፋ አስታወቀች። ይህ የተገለፀውም ለአስር ቀናት የቆየው የቻይና ሕዝባዊ ጉባኤ ባሳለፍነው ሰኞ ሲጠናቀቅ እንደነበር ተጠቅሷል። በርካቶች የጃፓኑ አይነት የኑክሊየር አደጋ እንዳይከሰት ከወዲሁ ፍራቻቸውን ገልፀዋል።

የዚምባቡዌ ፕሬዝዳት ሮበርት ሙጋቤ ከጥቂት ወራት በሕዋላ አዲስ ምርጫ እንደሚደረግ በቅርቡ አስታዉቀዋል።የምርጫዉ ትክክለኛ ቀን በዉል ሳይወሰን ግን የሐገሪቱ ፀጥታ አስከባሪዎች የሙጋቤ ተቃዋሚዎችን፥ የተቃዋሚዎቹን ደጋፊዎችና የመብት ተሟጋቾችን እያሰሩና እየደበደቡ ነዉ።

ዩሮ-ዶላር የሚዛቅበት ነዳጅ ዘይት እዚያዉ እየከሰለ ነዉ።ከሁለት ሳምንት በፊት በየአዉራ ጎዳናዉ የሚሰማዉ የመኪና ጥሩምባ፥ የከበሮ ድምድምታ በቦምብ ግምግምታ ተለዉጧል።የሰዎቹ-ዉካታ በጣር ጩኸት።እና ጥፋት።

በጅማ ዞን ፤ አሰንዳቦ አካባቢ የተቀሰቀሰ የሃይማኖት ግጭት መንስኤ አሁንም በሃይማኖት መሪዎችና በህግ እየተጣራ ይገኛል። በኢትዮጵያ እስልምና ምክር ቤት የፅህፈት ቤት ኃላፊ ሀጅ ጀማል መሀመድ ሳልህንና የኢትዮጵያ ሃይማኖት መሪዎች የጋራ መድረክ አስተባባሪ እንዲሁም የመካነ እየሱስ ቄስ የሆኑት ፤ ቄስ ኢተፋ …

በጅማ አካባቢ የተከሰተዉ ግጭትና የመፍትሄ ሂደት Read more »

የኬንያ መንግስት ደግሞ የባለስልጣናቱ ጉዳይ በአገር ዉስጥ ፍርድ ቤት እንዲታይ እየጠየቀ ነዉ። ምዕራባዉያን አገራት የኬንያ መንግስት ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም እያሉ ነዉ። ዓለም ዓቀፉ የወንጀል ችሎት ICC ኬንያ ዉስጥ ከአዉሮፓዉያኑ 2007 ምርጫ በኋላ ለተነሳዉ ግጭት ተጠያቂ ያላቸዉን የከፍተኛ ባለስልጣናት ስም ይፋ …

ኬንያና የዓለም ዓቀፍ ወንጀል ችሎት Read more »