የዩጋንዳ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ
በምስራቅ አፍሪቃዊቱ ሀገር ዩጋንዳ ትናንት ምክር ቤታዊ እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተካሄደ። በፕሬዚደንታዊው ምርጫ ሰባት የተቃዋሚ ወገን ዕጩዎች ዩጋንዳን ላለፉት ሀያ አምስት ዓመት በመሩት የስድሳ ስድስት ዓመቱ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ አንጻር ተወዳድረዋል።
በምስራቅ አፍሪቃዊቱ ሀገር ዩጋንዳ ትናንት ምክር ቤታዊ እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተካሄደ። በፕሬዚደንታዊው ምርጫ ሰባት የተቃዋሚ ወገን ዕጩዎች ዩጋንዳን ላለፉት ሀያ አምስት ዓመት በመሩት የስድሳ ስድስት ዓመቱ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ አንጻር ተወዳድረዋል።
በሰሜን አፍጋኒስታን በሚገኝ የጀርመን የጦር ሰፈር ትናንት አንድ የአፍጋኒስታን ወታደር መለዪ የለበሰ ግለሰብ ባስነሳዉ ተኩስ ሶስት የጀርመን ወታደርን ገድሎ ስድስት ወታደርን አቆሰለ።
የአዋሳ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ የአርሶ አደር መሬት ገዝተው መኖሪ ቤትና የተለያዩ ግንባታዎችን ያከናወኑ ናቸው ባላቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ገልጿል። ከ1985 ጀምሮ በተለይ ዳቶ በተሰኘው አከባቢ መኖሪያ ቤት ሰርተው እየኖሩ እንደሆኑ የሚገልጹት ነዋሪዎች መንግስት ያለምንም አማራጭ ሊያፈናቅለን …
ታዋቂው ኢትዮጵያዊ አርቲስት ጌትነት እንየው የዛሬው የወጣቶች መድረክ እንግዳችን ነው። ጌትነት በውብ ብዕሩ የዘመኑን ወጣት እሳቤ ሽሙጣዊ በሆነ መልኩ ያስቃኘናል።
የግብጹ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከሥልጣን ከወረዱ በኃላ ወታደራዊው አመራር የአገሪቱን የወደፊት እጣ በተመለከተ ወሳኝ መመሪያዎቹን አስታውቋል
ከአገራችን ባህል አኳያ በዳይና ተበዳይ ይቅር መባባል ይቅርታን መቀበል መስጠት የተለመደ ጥንታዊ ባህላችን ነዉ። ተበዳይ ለዘለቄታ አብሮ ለመኖር ቂም በቀልን ትቶ በዳይን ይቅር ብሎ በሽምግልና ችግርንም መፍታት ለአገር ልማት በጋራ ለመኖር እና ለመስራት ታላቅ መፍትሄ መሆኑ የሚታወቅ ነዉ።
የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ሥራ አመራር ለፈረንሳይ ቴሌኮም ከተሰጠና ኢትዮ ቴሌኮም ተብሎ ከተሰየመ በኋላ የተጀመረው የሰራተኛ ምደባ ና ድልደላ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የድርጅቱ ሰራተኞች ይናገራሉ ።
በዘውድ አገዛዝ የምትመራዋ ንዑሷ የባህረ ሰላጤ ሀገር ባህሬን ለዘብተኛ አመራር በመከተልዋ ለብዙ ጊዜ ባካባቢው በአርአያነት የምትታይ ሀገር ሆና ቆይታለች።
በሥነ ቴክኒክ የመገናኛ አውታሮች መስፋፋት ረገድ፣ ከሁሉም ክፍላተ ዓለም በአዝጋሚነት የሚጠቀሰው የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ነው።
የኒውዮርክና የፍራንክፉርት የፊናንስ ገበዮች ትናንት ታሪካዊ ግምት የሚሰጠው ውሕደት ለማስፈን ተስማምተዋል።
ህዝባዊ አመጽ በግብፅና ቱኒዚያ ከተቀጣጠለበት ጊዜ አንስቶ ሁኔታዎች በቻይናም ሊገነፍሉ የደረሱ ይመስላል። አንድ ቻይናዊ ፖለቲከኛ ነገሮች በኛም ሀገር በቋፍ ላይ ነው ያሉት ሲሉ ገልፀዋል። በእርግጥ በግብፅና ቱኒዚያ የተከናወነው አይነት ህዝባዊ አመፅ በቻይናም ቢቀጣጠል ምን ይከሰት ይሆን?
በሊቢያ የቤንጋዚ ወደብ ከተማ መንግስትን በመቃወም ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች፡ በፖሊስ እና በመንግስት ደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አስራ አራት ሰዎች ቆሰሉ።
የምርምር ጋዜጠኞችን በመጨቆን አፍሪቃ ቀዳሚዉን ስፍራ እንደያዘች ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ CPJ አስታወቀ።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን ትናት ሰኞ (08. 06.2003 ዓ.ም.) አደባባይ መውጣታቸው ተዘገበ። ሰልፈኞቹ የኢራን መንግስትን ሲቃወሙ በአንፃሩ ለግብፅና ቱኒዚያ የዲሞክራሲ ንቅናቄ ድጋፋቸውን አሳይተውበታል። የኢራን የፀጥታ ሀይላት በሰልፈኛው ላይ ምህረት አልባ ርምጃ መውሰዳቸውም ተጠቅሷል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን በግብፅና ቱኒዚያ የተከናወኑ …
የአየር ንብረት ለዉጥ ከእለታዊ የአየር ሁኔታ መለዋወጥ ጋ የሚያገናኘዉ መሠረታዊ መገለጫ ቢኖርም አንድ ናቸዉ ማለት ግን አይደፈርም።
በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በዛሬው ዕለት 1485 ኛውን የነቢዩ መሀመድ የልደት በዓልን በማክበር ላይ ይገኛሉ።
ካላፉት 3 ቀናት አንስቶ የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ በቱኒዝያ ስደተኞች ተጥለቅልቃለች ። እነዚህ ቁጥራቸው ከነዋሪዎቿ በላይ የሆነው በጀልባ ወደ ደሴቲቱ የጎረፉና የሚጎርፉ ስደተኞች ኢጣልያን በእጅጉ አስጨንቀዋል ።
ማሳሰቢያ የዶቸ ቬለ የፕሮግራም ሥርጭቶች ሆን ተብሎ መታወክ ደረሰባቸው፣ መታወክ የደረሰባቸው የሞገድ መስመሮች፤ Hotbird 8 ሳተላይት በኩል የሚሰራጩት ናቸው ። ሞገዶቹ ሆን ተብሎ በአዋኪ ድምፅ መሰናክል ገጥሟቸዋል ። ቀደም ባለው ጊዜ ይህ ዓይነቱ የሚያውክ ድምፅ ያጋጥም የነበረው ከኢራን በኩል ነው …
ቱኒዚውያን መሪያቸውን ካባረሩ በኋላ እስከአሁን አልተረጋጉም። ወጣቱ በጀልባ ውደ አውሮፓ ስደትን ጀመረ። ላምፔዱሳ ሰሞኑን የሰሜን አፍሪካው አብዮት መዓት ይዞባት መጥቷል።
የቱኒዝያ ስደተኞች በባህር በኩል ወደ ኢጣልያ ጠረፍ መጉረፋቸዉ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። በዚህም ጣልያን የአስቸኳይ ጊዜ ደምብ አስፍሮአል። በኢጣልያ ጠረፍ ጥበቃ ሃይል መግለጫ መሰረት ባለፈዉ ሌሊት ብቻ አንድ ሺህ ገደማ የሚጠጉ ስደተኞች ላፓዱዛ ደሴት ደርሰዋል። ቀደም ባሉት ቀናት ቢያንስ ሶስት ሹህ …
ማንተጋፍቶት ስለሺ የግብፅ ጦር በቀድሞ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሞባረክ 20 ታማኞች ላይ የጉዞ እገዳ አስቀመጠ። የጎዞ እገዳውን ያስተላለፈው የግብፅ ጦር ሲሆን፤ ባለስልጣናቱ ሀገር ለቀው እንዳይሸሹ በሚል ያስተላለፈው ውሳኔ እንደሆነም ተጠቅሷል። ባለስልጣናቱ መጓዝ ከፈለጉም ከጦሩ ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ተጠቁሟል። ይህ በእንዲህ እንዳለ …
በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ በትልቅ ጉጉት የጠበቀው እና ፕሬዚደንት ሙባራክ ከስልጣን እንደሚወርዱ ያስታውቁበታል ያለው ዲስኩራቸው ህዝቡ የጠበቀውን ውጤት አላስገኘለትም ነበር፤ ግን የህዝብ ተቃውሞ ተጠናክሮ በመቀጠሉ ፕሬዚደንት ሙባራክ ትናንት ስልጣናቸውን መልቀቅ ተገደዋል። ይህም በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ደስታና ፈንጠዝያ ፈጥሮዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ቀደም ሲል 1.8 ሚልዮን ሄክታር መሬት፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም (የዚያኑ እጥፍ) 3.6 ሚልዮን ሄክታር ለም መሬት ፣ ለውጭ ሀገር ኩባንያዎች ከ 40-99 ዓመት ገደማ በኪራይ ይሁን በሽያጭ እንዲቀራመቱ ፈቅዷል። ቻይናውያን ፣ ህንዳውያን፣ ዐረቦችና ኮሪያውያን በሽሚያ ላይ ናቸው። አውሮፓውያንም …
የግብፅ ፕሬዝደት ሆስኒ ሙባረክ ከ18ቀናት ዉዝግብ በኋላ ስልጣን ለቀቁ። ለቀናት አደባባይ ወጥቶ ስንብታቸዉን ሲጠይቅ የከመዉ ህዝብ ደስታዉን እየገለፀ ነዉ። ሙባረክ፤ ትናንት ማታ በተስፋ ሲጠብቃቸዉ ለነበረዉ ህዝብ ከፊል ሥልጣናቸውን ለምክትል ፕሪዚዳንትነት ለመረጧቸው ዖማር ሱሌይማን ማስተላለፋቸውን ከመጠቆም በስተቀር ከሥልጣን እንደሚወርዱ ሳይገልጹ ነበረ …
የጀርመን መዲና በርሊን ዛሪ ስድሳ አንደኛዉን አለም አቀፍ የፊልም ትዕይንት ማስተናገድ ይጀምራል። ለአስር ቀናት የሚዘልቀዉ ይህ የፊልም ትዕይንት በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ የፊልም ስራ አዋቂዎችን የፖለቲካ ሰዎችን እና ታዋቂ የህብረተሰብ አባላትን በመጋበዝ በተለያየ አለም አገሮች የተሰሩ ፊልሞችን በማወዳደር ሽልማት …
የካይሮዉ ተሕሪር ወይም የነፃነት-አደባባይ ዛሬም እንደ መሰንበቻዉ መብት ነፃነቱን በሚጠይቀዉ የግብፅ ሕዝብ እንደተጨናነቀ ነዉ።የአሌክሳንዴሪያ፥ የስዌዝና የሌሎችም ትላልቅ ከተሞች አዉራ ጎዳኖች የሙባረክ ተቃዋሚች ይርመሰመሱባቸዋል
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን የስርጭት አገልግሎት በምህፃሩ ኢሳት በመባል የሚታወቀዉ ፤
አዉቶሞቢል የዛሬ 125ዓመት የተፈበረከባት ጀርመን የሚደርሰዉ ጉዳት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚከሰተዉ ጋር አይወዳደርም።
አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባ ነዳጅ ማደያዎች ዛሬ ለደንበኞቻቸው የተለመደውን የነዳጅ ሽያጭ አገልግሎት ማስጠት ማቆማቸውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ታደሰ እንግዳው ዘግቧል ። ምክንያታቸውም ኢታኖል የተደባለቀበት ነዳጅ የለም የሚል ነው ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት በበኩሉ ምንም ዓይነት የነዳጅ ዕጥረት የለም ባይ ነው ። …
በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ እጅግ የገሠገሡ አገሮችም ሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለታዳጊ አገሮች ተማሪዎች ሊያበረክቱ የሚችሉት ድርሻም ሆነ ጠቀሜታ የሚያጠያይቅ አይደለም።
በቱኒዚያና በግብፅ የተቀጣጠለዉን ህዝባዊ አመፅ ተከትሎ በየመንም ተቃዋሚዉ ወገን ወደ20ሺ የተገመተ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ድምፁን እንዲያሰማ ማድረግ ተሳክቶለታል።
የምግብ ዋጋ ባለፉት ስድሥት ወራት ያላማቋረጥ እያደገ መምጣቱ የኤኮኖሚ ጠበብትን እንደገና እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው።
በኢትዮዽያ በመጪው የካቲት ወር መጨረሻ ላይ የሟሟያ ምርጫ ይካሄዳል። በዚህ ምርጫ ተቃዋሚዎች አይሳተፉም። ምርጫ ቦርድ ይህ የኔ ችግር አይደለም ይላል።
የደቡብ ሱዳን ህዝበ ውሳኔ ውጤት ከሰሜኑ መነጠል መሆኑ ከታወቀ ወዲህ የደቡብ ሱዳን የወደፊት ዕጣ ማነጋገር ይዟል ።
ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት የሆነዉ የሴት ልጅ ግርዛት ወትሮ ተንሰራፍቶ ከኖረበት ከሶስተኛዉ ዓለም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወደምዕራባዊዉና ወደበለጸገዉ ዓለምም መዝለቁ እየተነገረ ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘንድሮ 2.8 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ ርዳታ ያስፈልገዋል።ለችግረኛዉ ሕዝብ የስድስት ወር ቀለብ ለመግዢያ ደግሞ 227 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል
የግብፅ ወታደሮች ዛሬም በታህሪር አደባባይ የተሰበሰበውን ተቃዋሚ ህዝብ ለመበተን ያደረጉት ሙከራ ከሽፏል።
እዚህ ጀርመን ሙኒክ ከተማ በየዓመቱ የሚካሄደዉ የዓለም የፀጥታ ጉባኤ ካለፈዉ ዓርብ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ተካሂዷል።
በፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባራክ ላይ የተነሣው ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። በሌላ በኩል ፕሪዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ለጤና ምርመራ ወደ ጀርመን ሊሄዱ እንደሚችሉ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል።
አስራ አንደኛ ቀኑን የያዘውና የማግሬብ ሀገራትን እያተራመሰ ያለው የህዝብ አመጽ በዓለም ዙሪያ ቀዳሚ የመነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል።
የግብፅ ህዝባዊ አመፅ ወደግጭት ከተሸጋገረ ወዲህ ዉጥረት ነግሷል።
ሙስና ጭቆና እና የኑሮ ውድነት የወለደው የግብፅ ህዝባዊ አመፅ ከትናንት አንስቶ አዲስ መልክ ይዟል ።
በኢትዮጽያን የሚያዉቁ በኢትዮጽያ የኖሩ የዉጭ አገር ዜጎች በተለይ ኢትዮጽያን ጥለዉ ሲወጡ ስለ አገሪቷ ዉበት በአገሪቷ ስላለዉ ብሄር ብሄረሰብ ስለ ህዝቧ ፍቅር፣ ስለወንዝ ተራራ እና ሜዳዉ በአጠቃላይ በአኢትዮጽያ ስላገኙት ተመክሮአቸዉ ተናግረዉ አይጨርሱም።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄ መልስ ሰጡ።
አስር ቀናትን የደፈነዉ በግብፅ የተቀጣጠለዉ ህዝባዊ አመፅ ከትናንት ቀትር በኋላ አንስቶ ወደግጭት ተሸጋግሯል።
የድሬደዋ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት መምህራን የኑሮ ዉድነትን በማገናዘብ የተደረገልን የደሞዝ ጭማሪና የቤት ድጎማ ከእጃችን አልገባም ሲሉ ትናንት ስራ አቁመዉ ተቃዉሞ አሰሙ።
ከሥልጣን እንዲወርዱ ለአንድ ሳምንት በአደባባይ ተቀውሞ የተጠየቁት የግብፁ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ በሚቀጥለው ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ ።
በማግሬብ አካባቢ በቱኒዚያ የጀመረው የሕዝብ ዓመጽ አሁን ደግሞ ግብጽን እየናጠ ሲሆን ውጥረቱ በጠቅላላው በአረቡ ዓለም እንዳይስፋፋ በተለይም ገዢዎቹን እያሰጋ ነው።
ፕሪቶሪያ የሚገኘው የአለም አቀፍ ስልታዊ ጥናት ተቋም ሀላፊ፤ ዶክተር ጃኪ ቺለርስ በአፍሪቃ የመሪዎች ጉባዬ ላይ የሰጡት አስተያየት
ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባራክ እንዲወርዱ በመጠየቅ በተለያዩ የግብጽ ከተሞች የተጀመረው የህዝብ ተቃውሞ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። አዲሱ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዚደንት ኦማር ሱሌይማን ከተቃዋሚ ቡድኖች ጋ ለመወያየት ትናንት ሀሳብ አቅርበዋል።