ሂዉማን ራይትስ ዎች እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቀ

ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ሂዉማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ መንግስት ካለ ክስ በጅምላ ያሰራቸዉን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እንዲለቅ ጠይቋል።

ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ ሎንዶን የሚገኘዉ የድርጅቱ ጽህፈት ቤት የአፍሪቃ ጉዳይ ተወካይ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ ረገድ ጥሩ ስም እንደሌለዉ በመግለፅ እሳቸዉ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ በማንሳታቸዉ ከኢትዮጵያ መባረራቸዉን አመልክተዋል። የሎንዶኑ ወኪላችን ሂዉማን ራይትስ ዎች ያወጣዉን መግለጫ አስመልክቶ አነጋሯቸዉ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳ ጌታነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሠ