ሕዝባዊ ሠላማዊ አመፅ ወደ ጠመንጃ ዉጊያ ከተቀየረ ወዲሕ ግን ሕዝባዊዉ ድል በመጀመሪያ ፍጥነቱ አልቀጠለም።ኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊም የአመፁባቸዉን ሐይላት በሐል ከመደፍለቅ አላመነቱም።ታንክ፥ መድፍ፥ ተዋጊ ጄት፥ ሔሊኮብተር፥ የታጠቀዉ የቃዛፊ ታማኝ ጦር አማፂያኑ የሚቆጣጠሯቸዉን ከተሞች እያጠቃ ነዉ።

የ16 ሰዎች ህይወት የጠፋበት፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች የተቃጠሉበት ግጭት በደቡብ ኢትዮዽያ ተቀስቅሷል። በአርባ ምንጭ ዞን በምትገኘው ካምባ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች በተፈጠረው የድንበር ይገባኛል ጥያቄ የተፈጠረው ግጭት እንዳልበረደ አንድ የአይን እማኝ ተናግረዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው ካለፈው የካቲት ሶስት ጀምሮም እንደሆነ ተገልጿል። ዮሀንስ …

የ16 ሰዎች ህይወት የጠፋበት በአርባምንጭ የተከሰተ ግጭት Read more »

መገናኛ ዘዴዉ ለሕዝባዊዉ አመፅ መሠረት አይሁን እንጂ የኑሮ ዉድነት፥ ሥራ አጥነት፥ የዲሞክራሲ እጦት፥ የመናገር፥ የመሰብሰብ መብት የተነፈገዉ ሕዝብ በጣሙን ወጣቱ የየገዢዎቹን ጠንካራ አፈና ተጋፍጦ እንዲያምፅና አመፁን ለማቀጣጠል ቤን ዓሊን ከቱኒዝ፣ ሙባረክን ከካይሮ አብያተ-መንግስታት ያሽቀነጠረዉ፣ የቃዛፊን እና የሳሌሕን በትረ-ሥልጣን የሚገዘግዘዉ፣ከአልጀርስ እስከ …

ሕዝባዊ አመፅና የመገናኛ ዘዴዎች ሚና Read more »

በሊቢያ ምስራቃዊ እና ምዕራባዊ ክፍል በሞአማር ጋዳፊ ደጋፊ ወታደሮችና በሕዝባዊው ዓማጺያን መካከል የሚካሄደው ውጊያ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው። በዉግያዉ ሁለቱም ወገኖች በአገሪቷ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎችን በእጃቸዉ ለማስገባት በመጣር መሆኑ ተመልክቶአል።

ዓለም በ 2008 ዓ.ም. ከደረሰበት ከባድ የፊናንስና የኤኮኖሚ ቀውስ እርግጥ ቀስ በቀስ እያገገመ መሄዱ አልቀረም። ይሁን እንጂ ቀውሱ በተለይም በዓለምአቀፉ የምንዛሪ ስርዓት ላይ ጥሎት የሄደው ችግር በቀላሉ የሚገመት አይደለም።

«መታወቅ ያለበት ሞቃዲሾ ዉስጥ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት መመሥረት በሶማሊያ ሁኔታ አይሠራም።የሚያስፈልገዉ ሥልጣኑን ለአካባቢ መስተዳድሮች የሚያጋራ መንግሥት ነዉ።የሽግግር መንግሥቱ ማድረግ ያለበትም ይሕንን ነዉ

ቦን የሚገኘው በምህጻሩ ቢክ በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ኮንቨርሽን ማዕከል የተባለው መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት እአአ ለ 2009 ዓም የዓለም ሀገሮች ለጦሩ ዘርፍ ያዋሉትን ወጪ የተመለከተበትን መዘርዝር ሰሞኑን አወጣ።

ሊቢያ ውስጥ በተቀጣጠለው ሕዝባዊ ዓመጽ የተነሳ በርካታ አፍሪቃውያን በከፍተኛ ሁኔታ መቸገራቸው ተገለፀ። የችግሩ ገፈት ቀማሾች በተለይ ጥቁር አፍሪቃውያን እንደሆኑም ለማወቅ ተችሏል። አፍሪቃውያኑ ከሀዲ በሚል ተፈርጀው የጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው።

የሊቢያው ፕሬዚዳንት ሙዓማር ቃዳፊ በሀገር ውስጥም ሆን በውጭ ጫናው እየበረታባቸው እንደሆነ ተገለፀ። ትናንት ከዋና ከተማዋ ትሪፖሊ አቅራቢያ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰልፈኛ እንደተገደለ ታውቓል። በአንፃሩ የአሜሪካ ጦር ወደ ሊቢያ እየተጠጋ እንደሆነም ተዘግቧል። ማንተጋፍቶት ስለሺ የሊቢያ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ የሚከተለውን አጠናቅሯል።

በሰሜን አፍሪካና በአንዳንድ የአረብ ሀገራት የሚገኙ ወጣቶች የመብት ጥያቄን በማንገብ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያከናውኑ ዋነኛ መሳሪያቸው አድርገው የተነሱት የመረጃ ፍሰትን ነው። እናስ ታዲያ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በሌሎች ሐገራት ስለሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ ምን ያህል ግንዛቤው አላቸው? መረጃዎችንስ በዋናነት ከየት ነው የሚያገኙት?

የሊቢያ ሶሻሊስት ጀምሕሪያ የመስከረም አንዱ ታላቅ አብዮት መሪ-የከንግዲሕ እርምጃቸዉ 6.5 ሚሊዮን ሕዝባቸዉን ማወክ፥ ተቃዋሚያቸዉን መግደል፥ ከአፍሪቃ አረተኛዋን ሰፊ፥ ሐብታም ሐገር ሊቢያን በጎሳ ጠርዝ የሚከፋፍል እንዳይሆን በርግጥ ያሰጋል።

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ም/ቤት ሊቢያ ውስጥ የሞአማር ጋዳፊ አገዛዝ የሕዝቡን እንቅስቃሴ ለመቅጨት በሲቪሉ ነዋሪ ላይ ያደረሰዉን ጥቃት በማስመልከት በሞአመር ጋዳፊ እና ተከታዮቻቸዉ ላይ ዉሳኔዉን አጸደቀ።

ብርቱ ተቃውሞ የገጠማቸው የሊቢያው ዓብዮታዊ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ ጋዳፊ በስልጣን ለመቆየት የመጨረሻ ተስፋቸውን በአፍሪቃውያን ቅጥረኛ ወታደሮች ላይ ማሳረፋቸውን የመገናኛ ብዙኃን እና የተቃዋሚ ወገኖች የሚያወጡዋቸው ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ትሪፖሊ የሚኖሩ ሌሎች ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እንደገለፁት ግን ቤንጋዚ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መገደል፥ መደብደብ መታሠራቸዉንም ሰምተዋል።እዚያዉ ትሪፖሊ ደግሞ ቢያንስ ሁለት ኢትዮጵያዉያን መገደላቸዉንም ገልፀዋል

በሊቢያ የህዝብ አመፅ ይቃጣል ተብሎ ሳይታሰብ ፤ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ፣ተጀምሮ እንደቀጠለ ነው። ይሁንና በግብፅ የታየውን ቁጥብነት ያላንጸባረቁት የአገሪቱ የጦር አኤሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች፣ ለተቃውሞ አደባባይ በወጣው ህዝባቸው ላይ መተኮሳቸው ከተዘገበ ወዲህ በዓለም ዙሪያ ፤

በሊቢያ ሰልፈኞች ላይ መንግስት የወሰደው እርምጃ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ውግዘትን አስከትሏል። የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን ይችላል እያለ ነው። ቱርክ ለሊቢያ ባለስልጣናት ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰዳለች።

ቤን አሊን፥ ከቱኒዝ፥ ሙባረክን ከካይሮ አሽቀንጥሮ የጣለዉ አዲሱ ሕዝባዊ አመፅ የአረቡን አለም እየናጠ በአዲስ ጎዳና እየዘወረዉም ነዉ። የፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽና የጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌሯ ዲሞክራሲያዊት ኢራቅም ከአዲሱ ሕዝባዊ ነዉጥ አላመለጠችም