ተወዳጁ እና አንጋፋዉ የባህል ሙዚቃ አንባሳደር የይርጋ ዱባለ የዜና እረፍት ትናንት ተሰምቶአል። ድምጻዊ ይርጋ ዱባለ የኢትዮጽያን ባህል በተለያዩ የአለም ክፍሎች በመዘዋወር ያሳዩ እና ያስተዋወቁ አንጋፋ ተወዳጅ የጥበብ ሰዉ ነበሩ። ይርጋ ዱባለ ዛሪ ግባተ መሪታቸዉ ተፈጽሞአል። በቦታዉ ላይ የነበረዉ ወኪላችን ታደሰ …

የይርጋ ዱባለ የዜና እረፍት Read more »

የኢትዮዽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከጅቡቲ በመጀመር ከመጪው ሀምሌ ወር አንስቶ ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል የመሸጥ ዕቅድ አለው። ህዝቡ ግን በኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ችግር ውስጥ እንደሆነ ይናገራል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኢትዮዽያ መንግስት የኤሌክትሪክ ሃይል ለጎረቤት ሀገራት የመሽጥ እቅድ እንዳለው በተደጋጋሚ ይገልጻል። …

የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ዕቅድና የህዝብ ቅሬታ Read more »

ዛሬ አዲስ አበባ በበርካታ አከባቢዎች ታክሲዎች ስራ አቁመው ውለዋል። አዲሱ የስምሪት መመሪያ ጥቂቶችን ለመጥቀም የወጣ ነው ሲሉ ባለታክሲዎቹ አማረዋል። የዛሬ ሳምንት ሰኞ የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ፤ የአዲስ አበባ ታክሲዎችን ስምሪትና የዋጋ ተመን የሚያሳይ አዲስ መመሪያ አዋጣ። መመሪያው አርብ ዕለት …

በአዲስ አበባ የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ Read more »

የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ፣ ለ 4ኛ ጊዜ የስልጣን ዘመናቸው የሚራዘምበትንም ሆነ በፕሬዚዳንትነት አገሪቱን መግዛት የሚቀጥሉበትን ሁኔታ ፣ በዛ ያሉ መሰል አፍሪቃውያን መሪዎች በተገኙበት ልዩ ሥነ ሥርዓት፣ ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል።

በሚያዝያ ወር መዳረሻ ጀምሮ ያሉት ሶስት እና አራት ወራቶች ጀርመናዉያን በጉጉት የሚጠብቋቸዉ የሚወዱዋቸዉ ወራቶች ናቸዉ። በሚያዝያ ወር ሲዳረስ የሚያንዘፈዝፈዉ ብርድ ተጠናቆ ጸሃይ የሙቀት ጮራዋን የምትፈነጥቅበት

በኃይለኛ የባህር ወለል ነውጥና የውቅያኖስ ማዕበል ሳቢያ፤ ጃፓን ውስጥ በአቶም ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ አደጋ ከደረሰ ወዲህ፤ ሰዎች የገነቡትና የሚገነቡት ማንኛውም አውታር ከተፈጥሮ አደጋ ሊጠበቅ እንደማይችል ፤

ይህ በጀርመናዊው ጋዜጠኛና ደራሲ ማርኩስ ፍሬንሰል ተደርሶ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ስለ አፍሪቃ በተለይም ስለኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ በዝርዝር ያትታል። መጽሐፉ «ሬሳ ከምድር ቤቱ» ወይንም «ከወለሉ ስር» የሚል ትርጓሜ ይይዛል። በጀርመንኛ Leichen im Keller የሚል ርዕስ ይዞ ነው የወጣው።

የአፋር ህዝብ የሀይማኖት እና የፖለቲካ መሪ የነበሩት ታላቁ ዐሊ ሚራህ ሀንፍሬ አረፉ። በዘጠና ዓመታቸው ያረፉት ሱልጣን ዐሊ ሚራህ በስልጣን ዘመናቸው ሁሉ ለአፋር ህዝብ ኢትዮጵያዊነት እና ለአፋር ህዝብ አንድነት ሳያሰልሱ በመታገላቸው ነው የሚታወቁት። ያዳምጡ

ሊቢያ ፤ ሶሪያና የመን ፤ የህዝቡ የለውጥ ፍላጎትና የገዥዎቹ ሥልጣንን የሙጥኝ ማለት ፣ ከሞላ ጎደል በየዕለቱ የሰው ነፍስ በማስገበር ላይ ነው። በየመን ከ 32 ዓመት በላይ በሥልጣን ላይ የሚገኙትን አሊ አብደላ ሳሌህ የሚቃወሙት ወገኞች እየተጠናከረ ነው የመጣው።

በጣሊያንና በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መሀል ስደተኞችን በተመለከተ ውዝግቡ ተካሯል። ጣሊያን ስደተኞቹን ተካፈሉኝ ብትልም ከህብረቱ ሀገራት በኩል የተሰጣት ምላሽ እዚያው እያሉ እናግዝሻለን እንጂ ወደ ሌሎች ሀገራት ስደተኞችን መላክ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።

ባለፈው ቅዳሜ በናይጄሪያ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፤ ጉድላክ ዮናታን 57% ከመቶ ያህል የድምፅ ብልጫ በማግኘት ሲያሸንፉ፤ ተፎካካሪያቸው መሪ ሙሐመድ ቡሐሪ 31% ከመቶ ያህል ብቻ ነበር ያገኙት።

እስከ ቀዝቃዛዉ ጦርነት ፍፃሜ ድረስ ከሰሜን ጫፍ ቱኒስ፥ እስከ ማዕከላዊ አፍሪቃ ጥግ ኪንሻሳ፥ ከአፍሪቃ ቀንድ ጠርዝ ጅቡቲ፥ እስከ ምዕራብ አፍሪቃ ጥግ ያምሱኩሩ፥ የአፍሪቃ ፖለቲካ የሚዘወረዉ በፓሪስ ይሁንታና ፍቃድ ነበ

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ወያኔ/ኢሕአዴግ ለሕዝብ የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ተገቢዉን መልስ እንዲሰጥ ተቃዋሚዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት ባጭሩ) ከፍተኛ ባለሥልጣን ጠየቁ። የፓርቲዉ ሥራ አሥፈፃሚ አባል አቶ ስዬ አብረሐ እንደሚሉት ኢሕአዴግ አሁን የሚከተለዉ መርሕ ከጭንቀት የመነጨ ነዉ።አንድነትን በአባልነት የሚያስተናብረዉ ትልቁ ተቃዋሚ …

ወያኔ አባይን ለመገደብ ብቃት የለውም – ሰዬ አብረሃ Read more »

ዶቸ ቨለ (የጀርመን ድምፅ) ራዲዮ ከአንድ ሳምንት ገደማ ወዲህ አንስቶ የማሠራጫ ሞገዶቹ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያውክም ሆነ የሚያፍን ድምፅ እንዳገጠማቸው በመጥቀስ የራዲዮ ጣቢያው ባለሥልጣናት፣ ሥርጭቱ፤ ከእውካ ነጻ ስለሚሆንበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግሥት ይተባበር ዘንድ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ …

“የጀርመን ራዲዮ አድማጭ 1 ከመቶ ብቻ ነው” – በረከት ስምኦን Read more »

በሰሜን አፍሪቃና በአንዳንድ የአረብ ሀገራት ህዝባዊ ንቅናቄዎች ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ወደ አውሮጳ የሚፈልሱ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው። በጣሊያኗ የላምፔዱዛ ደሴት ብቻ እስካሁን ከ22,000 በላይ ስደተኞች መድረሳቸው ተዘግቧል።

ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት የልዑካን ቡድን በዩኤስ አሜሪካ እና በካናዳ በርካታ ስብሰባዎች አካሄደ። የትምህርት፡ የመከላከያ እና የፍትህን ጨምሮ አርባ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ሚንስትሮች፡ ከፍተኛ ባለስልጣናትን እና የክልል መስተዳድር ፕሬዚደንቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋ ስብሰባዎች ባካሄዱባቸው ከተሞች፡ ወኪላችን አበበ …

የወያኔ ልዑካን ቡድን ያሜሪካ ውይይት Read more »

በምርጫ አልተሸንፍኩም በማለት ዓለም ዓቀፍ እውቅና ከተሰጣቸው ከአላሳን ዋታራ ኃይሎች ጋር ሲዋጉ የከረሙት የአይቮሪ ኮስት ፕሬዝዳንት ሎሮን ባግቦ ተያዙ። የተቀናቃኛቸውን የአላሳን ዋታራን ቃል አቀባይ ጠቅሶ የጀርመን ዜና አገልግሎት DPA እንደዘገበው ባግቦ አቢዣን ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከቤተሰባቸው ጋር መያዛቸውን ቃል …

ባግቦ ተያዘ Read more »