የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አባላቶቹ እየታሰሩ እንደሆነ ገለጸ
ኦህኮ አባላቶቹ እየታሰሩ እንደሆነ ይገልጻል። ሰላማዊ ትግሉን አላቋርጥም ይላል
ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያ መስተዳድር በተለያዩ ጊዜያት እስካሁን ከ102 በላይ የሚሆኑ ቢሮዎቹ በኢህአዴግ መንግሥት እንደተዘጉበት የገለጠው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ፣ ከዚህ ቀደም ያጋጥሙት ከነበሩት መሰናክሎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቀድሞ የፓርላማ አባላት የነበሩና ታዋቂ አባላቱ ከየቦታው በፌደራል ፖሊስ እየተያዙ መታሠራቸው እየተነገረ ነው።
«አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ድርጅታችንን ሙሉ በሙሉ ባገር ውስጥ ለመዝጋት የሚደረግ ጥረት ይመስላል» ያሉት የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ምክትል ኀላፊ አቶ ኦልባና ለሊሣ፤ የኢትዮጵያ ህዝብና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ጉዳዩን በታዛቢነት እንዲከታተለው ጠይቀዋል።
ድሮም፤ አሁንም ወደፊትም የኦሮሞ ህዝባዊ ኮንግረስ፤ ሰላማዊ ትግሉን እንደሚቀጥል ያስታወቁትን አቶ ኦልባናን ፣ ተክሌ የኋላ በስልክ አነጋግሮአቸዋል። ያዳምጡ፤