ሶማሊላንድ እና ጸረ የባህር ላይ ውንብድና

በሰሜናዊ ሶማልያ የምትገኘው ሶማሊላንድ ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ በሱስ አስያዥ ዕጽ እና በወንጀል አንጻር በሚታገለው የተመድ መስሪያ ቤት ርዳታ በአንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ዩሮ ወጪ በርዕሰ ከተማ ሀርጌሳ የተሰራ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት ወህኒ ቤት ከፈተች።