የሶማልያው ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድን ዐል ሸባብ ባለፈው ቅዳሜ ከሞቕድሹ እንደወጣ ይታወሳል። የሶማልያው ፕረዚዳንት ሼኽ ሸሪፍ አሕመድ አማጽያኑ መሸነፋቸውን ገልጸዋል። ዐል-ሻባባ ግን ወታደራዊ ማፈግፈግ ነው ያደረግኩት ይላል። ስለ ጉዳዩ እንዲያብራሩልን የጋበዝናቸው የአፍሪቃ ጥናትና ምርምር ምሁር ዶክተር አለም ሃይሉ በበኩላቸው ዐል-ሻባብ ከሞቕድሾ …

አል-ሻባብ ከሞቕድሾ የወጣሁት ለወታደራዊ ታክቲክ ነው አለ Read more »

የሶማሊያው እሥላማዊ የዓመጽ ቡድን አሸባብ በሞቃዲሾ ይገኝ የነበረ ሃይሉን ቅዳሜ እለት ከስፍራው ማስወጣቱ ተገልጿል። ይሁንና በትናንትናው እለት በሞቃዲሾ በአሸባብ እና በመንግስት ወታደሮች መካከል ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ውስጥ በረራዎች በክረምቱ ጭጋጋማና ደመናማ የአየር ፀባይ ምክንያት በሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረጉ በረራዎች ለመሰረዝና ለማዘግየት መገደዱን አስታወቀ፡፡

መሬት ከሰዎች አሠፋፈር፤ ከሰብዓዊ፣ የዜግነትና የንብረት መብቶች፣ ከተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃና ልማት ጋር በጥብቅ የተቆራኘና የተሣሰረ በመሆኑ በየደረጃው የሚሰጠው ትርጉም የዚያኑ ያህል ጠበቅ ያለ ነው፡፡ የመሬት ይዞታን ሥሪት ከሚደነግገው መንግሥት በስንዝር መሬት ሙግት ሙሉ ዕድሜአቸውን እስከሚፈጁ ግለሰቦች አንገብጋቢና ትርጉም ያለው የሃብት …

የመሬት ቅርምትና ኪራይ እሰጥ አገባ Read more »

ይህ World Heritage Committee የሚባለው የዩኔስኮ አካል ባሕላዊና አካላዊም እሴትና ትርጉም ያላቸውን አካባቢዎች እየመዘገበ የሚይዝ ተቋም ሲሆን ግዙፉ ግቤ ሦስት ግድብ እየተገነባ ያለበት ኦሞ ወንዝ የሚገባበትን በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር ላይ ያለውን ቱርካና ሐይቅም በዓለም ቅርስነት መዝግቦታል፡፡ የተቋሙ ቃል አቀባይ ነፃ …

የግቤ ሦስት ግንባታ እንዲቆም ተጠየቀ Read more »

አቶ ሽመልስ አዱኛ፣  የቀድሞ የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን፣ ኮሚሽነርየዛሬው የቆይታ አምድ እንግዳችን አቶ ሽመልስ አዱኛ ናቸው፡፡ አቶ ሽመልስ የተወለዱት በጅጅጋ ከተማ ጥቅምት 2 ቀን 1928 ዓ.ም. ነው፡፡ እርሳቸው የተወለዱት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ ስለነበር ከእናታቸው ጋር ወደ ኬንያ ሄደው ለአምስት …

‹‹ግለሰብም ሆነ መንግሥት የራሱን ሕዝብ መመገብ እስካልቻለ ድረስ አንገቱን ቀና አድርጐ መሄድ አይችልም›› Read more »

ቲፎዞነት የጋርዮሽ ስርዓትን ይመስለኛል፡፡ ሰዎች በቡድን ሆነው አንድን ነገር ብቻ በፍጹም ልቦና ለመደገፍ የመቁርባቸው ነገር – ካሰቡት ያስቃል፡፡ ሰዉ ሁሉ በየፊናው የሚደግፈው የእግር ኳስ ቡድን፣ የፖለቲካ ቡድን፣ የሃይማኖት ቡድን፣ የፆታ ቡድን ራሱ ሳይቀር ያበጃል፡፡ማንቸስተር ዩናይትድ (ብልጫ አወዛጋቢ ቢሆንም) በጨዋታ ብልጫ …

ለመደገፍ መደገፍ፤ ለመቃወም መቃወም Read more »

በረሃብ እጅግ የተጎዱ ህፃናት እና እናቶች በየሠፈሩ ይታያሉ። በቂ እርዳታ አላገኘንም የሚሉም አሉ። የመለስካቸው አምሃ ሪፖርት ይቀጥላል፡፡ ዶሎ ኦዶ ከተማ በደቡባዊ ምሥራቅ ኢትዮጵያ አገሪቱን ከሶማሊያ ጋር ከሚያገናኙ ትናንሽ ከተሞች አንዷ ናት። በዶሎ ኦዶ ከተማና በሶማሊያ ድንበር መካከል ያለው ልዩነት 2 …

ቸነፈር ያበረራቸው የሶማሊያ ስደተኞች በዶሎ ኦዶ Read more »

የዛሬው «ኢትዮጵያ በጋዜጦች» ዝግጅታችን የሚከተሉትን ርዕሶች ይዟል -ኢትዮጵያ አርብቶ-አደሮችን በዘለቄታ ለማስፈር አቀደች -ኢትዮጵያ ለካሩቱሪ ኩባንያ የተመደበውን መሬት ቀነሰች -ኢትዮጵያ በስድስት አመታት ውስጥ ጋዝ ልታመርት እንደምትችል አስታወቀች

እንደ አል-ሸባብ ያሉ አሸባሪ ድርጅቶች ከረድዔት ድርጅቶች ምንም አይነት ክፍያም ሆነ እርዳታ እንዳያገኙ የሚከለክሉ የጸረ-ሽብር አሰራሮችን ዩናይትድ ስቴይትስ አላልታለች።

ለአንድ ወር ያህል የዩናይትድ ስቴትስን የህግ መምሪያና የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላትን ሲያከራክር የቆየውና በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ውሳኔ ያገኘው የአሜሪካን የእዳ ጣራን የወሰነው ህግ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም ሲሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ገለጹ ።

በኢትዮጵያ የበቆሎ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ተጠቃሚዎችና የችርቻሮ ነጋዴዎች መማረራቸውን ይናገራሉ። ዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬው ገበያ ወጥቶ ሸማቾችንና ነጋዴዎችን አነጋግሮ የላከው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ያዳምጡት።

በአሁኑ ጊዜ በአፍሪቃ፤ በተለይም በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ላይ ላተኮረ በዓይን ላይ የሚደቀነው የተለመደው የረሃብ አስከፊ ገጽታ ነው። የአካባቢው 12 ሚሊዮን ሕዝብ በወቅቱ የረሃብ ሞት አደጋ ተደቅኖበት የሚገኝ ሲሆን የኢትዮጵያም የድርቅ መለያነት ባለበት ቀጥሏል።

እስክንድር ነጋ – (አዲስ አበባ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሰሞኑን ተወጥረው ሰነባብተዋል፡፡ የመንግሥታቸው ወጪ ከገቢው መንጥቆ ማምለጡ አዲስ ዜና አይደለም፡፡ ትንሹ ቡሽ እንደ እ.ኤ.አ. በ2ዐዐዐ ዓ.ም ከክሊንተን ስልጣን ሲረከቡ፣ የአሜሪካ መንግሥት በካዝናው ትርፍ ገንዘብ ነበረው፡፡ ገቢው ከወጪው ይበልጥ ነበር፡፡ በ2ዐ1ዐ፣ …

ሶሪያ፣ አሜሪካ፣ አውሮፓና ኢትዮጵያ Read more »

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 26 ቀን 2003 ዓ.ም August 3, 2011):- በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የብጹእ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ክቡር ሥጋ የሚያርፍበት ቦታ ለማዘጋጀት ባወጣው እቅድ መሰረት በስማቸው በተሰየመውና …

የብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ የቀብር ስነ ስርአት በሲያትል ይፈጸማል Read more »

እግረ መንገድ . . . የበጋው ሐሩር ከሚያንቀለቅላት ከአረባዊቷ  ገር ከሳውዲ አረቢያ የከበረ ሰላምታየ ይድረሳችሁ ! ገና ከማለዳው ከ30 ዲግሪ ይ ምርና እኩለ ቀን ላይ ወደ 47 ዲግሪ የሚደርሰው የዘንድሮው የሳውዲ አረቢያ የሙቀት መጠን ዘግየት ብሎ ቢመጣም ትንፋሽን መቁረጥ  ምሯል ! …

ሳውዲ አረቢያ እየገቡ ያሉት ኢትዮጵያውያን አበሳ . . .! (ክፍል 11) Read more »

ከንጉሤ ጋማ በአሁኑ ወቅት በአፍሪቃ ቀንድ አገሮች በሶማሊያ፣ በኬንያ፣ በጂቡቲና በኢትዮጵያ በ60 አመት ታሪክ ዉስጥ ያልታየ በአይነቱ አስከፊ የሆነ የድርቅ አደጋ ተከስቷል። በዚህም 4.5 ሚሊዮን በሚሆኑ ወገኖቻችን ላይ የሞት አደጋ አንዣቧል።

‹‹ማንም ተሳተፈም አልተሳተፈ ሠልፉ አይቀርም›› የኢትዮጵያ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢአዴድ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲዎች በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሠልፍ በጋራ ለመጥራት ያቀረቡለትን ጥሪ አለመቀበሉን ለሪፖርተር አስታወቀ፡፡

‹‹በቅርቡ ዕጣ እናወጣላቸዋለን›› የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙና ዕጣ ያልወጣላቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሕገወጥ ደላሎች የኪራይ ገንዘብ እየተቀበሉባቸው እንደሚጠፉ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ድርቅ በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደ ረሃብ እንደማይሸጋገር የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ አስታወቁ፡፡ መንግሥት እያደረገ ባለው ጥረት ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ እንዳልሆነ አቶ ምትኩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የአሁኑ በአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ ከአሜሪካ ለንግድና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሥልጠና ከመጡት አምባሳደሮች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ አጭር ቆይታ ከሪፖርተር ጋር አድርገዋል፡፡

በአፍሪካ አኅጉር ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 19ኛው የዓለም ዋንጫ ከኢትዮጵያ ተመልካቾችን ለመላክ ተብሎ በተፈጠረ ማጭበርበር ምክንያት፣ ከህዳር 3 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በጀርመን ፖሊስ ቁጥጥር ሥር የነበሩት የአስካሉካን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤት ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጡ፡፡

– የ121 ሚሊዮን ብር ቦንድ በወለድ ለመግዛት ወስነዋል በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሪል ስቴት ኩባንያዎች በዓባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው የህዳሴ ግድብ ሊያዋጡ የነበረው 200 ሚሊዮን ብር ሊሟላላቸው አለመቻሉን ገልጸው፣ ቦንድ በወለድ ለመግዛት 121 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻላቸውን ገለጹ፡፡

በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ በንግድና በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መስክ በተባበሩት መንግሥታት የሥልጠናና የምርምር ተቋም (ዩኒታር) የሚሰጠውን የስድስት ቀን ሥልጠና ከነገ ጀምሮ ይከታተላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣንና የሐረርና በደሌ ቢራ ፋብሪካዎችን ለመሸጥ ያወጣውን ጨረታ ያሸነፈው ታዋቂው የሆላንዱ ሄኒከን ኩባንያ ኃላፊዎች ነሐሴ 4 ቀን 2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን ስምምነቱ ሊያደርጉ ነው፡፡

የአፍሪካ ኅብረት የዚህ ዓመቱን የመሪዎች ጠቅላላጉባዔ አዲስ አበባ ላይ ጠርቶ በነበረ ጊዜ የኤርትራ መንግሥት መጠነ ሰፊ ጥቃት ለማድረስ አቅዶ እንደነበረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ፡፡ ጥቃቱ በታቀደው መሠረት ተፈፅሞ ቢሆን ኖሮ በሲቪሎች ላይ ጉዳት መድረሱ አይቀር እንደነበር የመንግሥታቱ ድርጅት የሰየመው የሶማሊያና …

‘አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ’?! Read more »

«ኢትዮጵያ በጋዜጦች» የተሰኘው  ፕሮግራማችን ሶስት ርዕሶችን ይዞ ቀርቧል። – ኤርትራ አዲስ አበባን ባግዳድ የማድረግ እቅድ እንደነበራት ተገለጸ -የአፍሪቃ ቀንድ ረሀብ የምዕተ-አመቱ ቅሌት ሊሆን ይችላል ተባለ -የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጊቤ ሶስት ግድብ ግንባታ እንዲቆም ጠየቅ የሚሉት ናቸው

አንድን ስርዓት አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ሲደግፈው ያ ስርዓት ጠንካራ ሆኖ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ነገር ግን አንድን ስርዓት ለረጅም ጊዜ የሚያቆየው ይህ ብቻ አይደለም፤ ለምሳሌ ሕዝብ ጠልቶት ነገር ግን ካልተቃወመው ወይም ደግሞ ሕዝብ ተቃውሞት ግን ሕዝቡ ሙሉ ለሙሉ ያልተሳተፈበት ተቃውሞ …

ለውጥ ሲመጣ እኛ ግን …! ሶሎሞን አ. Read more »

የግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ራዕይ ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጎች፤ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች እና ሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ታስቦ የተቀረፀ ነው። የግንቦት 7 ተልዕኮ በሃገራችን ውስጥ አካባቢ ለይቶ፤ ዘውግንና ሃይማኖትን አማርጦ ተግባራዊ እንዲሆን የተቀረፀ አይደለም። ግንቦት 7፣ “ህዝብ የስልጣን ባለቤት መሆን …

ለዴሞክራሲና ለእኩልነት መረጋገጥ በጋራ የምናደረገውን ትግል የአንድነታችን መሠረት እናድርግ Read more »