የብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ የቀብር ስነ ስርአት በሲያትል ይፈጸማል
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 26 ቀን 2003 ዓ.ም August 3, 2011):- በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የብጹእ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ክቡር ሥጋ የሚያርፍበት ቦታ ለማዘጋጀት ባወጣው እቅድ መሰረት በስማቸው በተሰየመውና ቴክሳስ – ሂውስተን በተመሰረተው ገዳም ለማሳረፍ ያደረጋቸው ሙከራዎች ጊዜ በመውሰዱ ለጊዜው ብጹእነታቸው ብርታት ከእዳ ነጻ አድርገው በሲያትል ከተማ ባቋቋሙት መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቴድራል የቀብር ስነስርአታቸው እንዲፈጸም ወሰነ።